Check out the new design

Qurani Kərimin mənaca tərcüməsi - Amhar dilinə tərcümə - Afrika Akademiyası. * - Tərcumənin mündəricatı

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Mənaların tərcüməsi Surə: Yunus   Ayə:
وَإِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِمۡ ءَايَاتُنَا بَيِّنَٰتٖ قَالَ ٱلَّذِينَ لَا يَرۡجُونَ لِقَآءَنَا ٱئۡتِ بِقُرۡءَانٍ غَيۡرِ هَٰذَآ أَوۡ بَدِّلۡهُۚ قُلۡ مَا يَكُونُ لِيٓ أَنۡ أُبَدِّلَهُۥ مِن تِلۡقَآيِٕ نَفۡسِيٓۖ إِنۡ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَيَّۖ إِنِّيٓ أَخَافُ إِنۡ عَصَيۡتُ رَبِّي عَذَابَ يَوۡمٍ عَظِيمٖ
15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አናቅጻችን ግልጽ ሆነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ እነዚያ መገናኘታችንን የማይፈሩት (የማይሹት) ሰዎች «ከዚህ ሌላ የሆነን ቁርኣን አምጣልን ወይም ለውጠው።» ይላሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ ከራሴ በኩል ልለውጠው አይገባኝም:: ወደ እኔ የሚወረደውን እንጂ አልከተልም:: እኔ በጌታዬ ትዕዛዝ ላይ ባምጽ የታላቅን ቀን ቅጣት እፈራለሁ።» በላቸው::
Ərəbcə təfsirlər:
قُل لَّوۡ شَآءَ ٱللَّهُ مَا تَلَوۡتُهُۥ عَلَيۡكُمۡ وَلَآ أَدۡرَىٰكُم بِهِۦۖ فَقَدۡ لَبِثۡتُ فِيكُمۡ عُمُرٗا مِّن قَبۡلِهِۦٓۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ
16. (መልዕከተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ በሻ ኖሮ በእናንተ ላይ ባላነበብኩትና አላህ እርሱን ባላሳወቃችሁ ነበር:: በእናንተም ውስጥ ከእርሱ በፊት ምንም ሳልል ብዙን እድሜ በእርግጥ ኖሬያለሁ። አታውቁምን?» በላቸው።
Ərəbcə təfsirlər:
فَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّنِ ٱفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أَوۡ كَذَّبَ بِـَٔايَٰتِهِۦٓۚ إِنَّهُۥ لَا يُفۡلِحُ ٱلۡمُجۡرِمُونَ
17. በአላህ ላይ እብለትን ከቀጣጠፈ ወይ ከአናቅ ጹ መካከል (በአንዷ እንኳን) ካስተባበለ ይበልጥ በዳይ ማን ነው? እነሆ አመጸኞች አይድኑም::
Ərəbcə təfsirlər:
وَيَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمۡ وَلَا يَنفَعُهُمۡ وَيَقُولُونَ هَٰٓؤُلَآءِ شُفَعَٰٓؤُنَا عِندَ ٱللَّهِۚ قُلۡ أَتُنَبِّـُٔونَ ٱللَّهَ بِمَا لَا يَعۡلَمُ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَلَا فِي ٱلۡأَرۡضِۚ سُبۡحَٰنَهُۥ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشۡرِكُونَ
18. አጋሪዎች ከአላህ ሌላ የማይጎዳቸውንና የማይጠቅማቸውን ይገዛሉ:: «እነዚህ አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው።» ይላሉም። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ እናንተ ትነግሩታላችሁን?» በላቸው:: አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ:: ላቀም::
Ərəbcə təfsirlər:
وَمَا كَانَ ٱلنَّاسُ إِلَّآ أُمَّةٗ وَٰحِدَةٗ فَٱخۡتَلَفُواْۚ وَلَوۡلَا كَلِمَةٞ سَبَقَتۡ مِن رَّبِّكَ لَقُضِيَ بَيۡنَهُمۡ فِيمَا فِيهِ يَخۡتَلِفُونَ
19. ሰዎች አንድ ህዝብ እንጂ ሌላ አልነበሩም:: ከዚያ ተለያዩ:: ከጌታህ ያለፈ ቃልም ባልነበረ ኖሮ በዚያ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው በቶሎ በተፈረደ ነበር::
Ərəbcə təfsirlər:
وَيَقُولُونَ لَوۡلَآ أُنزِلَ عَلَيۡهِ ءَايَةٞ مِّن رَّبِّهِۦۖ فَقُلۡ إِنَّمَا ٱلۡغَيۡبُ لِلَّهِ فَٱنتَظِرُوٓاْ إِنِّي مَعَكُم مِّنَ ٱلۡمُنتَظِرِينَ
20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርሱ ላይም ከጌታው የሆነች ተዓምር ለምን አትወረድለትም?» ይላሉ:: «ሩቅ ነገር ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: እናንተም ተጠባበቁ እኔም ከናንተው ጋር ከሚጠባበቁት ነኝ።» በላቸው።
Ərəbcə təfsirlər:
 
Mənaların tərcüməsi Surə: Yunus
Surələrin mündəricatı Səhifənin rəqəmi
 
Qurani Kərimin mənaca tərcüməsi - Amhar dilinə tərcümə - Afrika Akademiyası. - Tərcumənin mündəricatı

Tərcüməsi Məhəmməd Zeyn Zöhrəddin. Afrika Akademiyası tərəfindən nəşr olunub.

Bağlamaq