Check out the new design

Qurani Kərimin mənaca tərcüməsi - Amhar dilinə tərcümə - Afrika Akademiyası. * - Tərcumənin mündəricatı


Mənaların tərcüməsi Surə: əl-İsra   Ayə:
وَإِمَّا تُعۡرِضَنَّ عَنۡهُمُ ٱبۡتِغَآءَ رَحۡمَةٖ مِّن رَّبِّكَ تَرۡجُوهَا فَقُل لَّهُمۡ قَوۡلٗا مَّيۡسُورٗا
28. ከጌታህም የምትከጅላትን ጸጋ ለማምጣት በማሰብ ከእነርሱ ብትዞር ለእነርሱ ልዝብን ቃል ተናገራቸው::
Ərəbcə təfsirlər:
وَلَا تَجۡعَلۡ يَدَكَ مَغۡلُولَةً إِلَىٰ عُنُقِكَ وَلَا تَبۡسُطۡهَا كُلَّ ٱلۡبَسۡطِ فَتَقۡعُدَ مَلُومٗا مَّحۡسُورًا
29. እጅህን ወደ አንገትህ ታጥፋ የታሠረች አታድርግ:: መዘርጋትንም ሁሉ አትዘርጋት:: የተወቀስክና የተቆጨህ ትሆናለህና::
Ərəbcə təfsirlər:
إِنَّ رَبَّكَ يَبۡسُطُ ٱلرِّزۡقَ لِمَن يَشَآءُ وَيَقۡدِرُۚ إِنَّهُۥ كَانَ بِعِبَادِهِۦ خَبِيرَۢا بَصِيرٗا
30. ጌታህ ሲሳይን ለሚፈልገው ሁሉ ያሰፋል። ለሚፈልገውም ያጠባል። እርሱ በባሮቹ ሁኔታ ውስጠ አዋቂና ተመልካች ነውና።
Ərəbcə təfsirlər:
وَلَا تَقۡتُلُوٓاْ أَوۡلَٰدَكُمۡ خَشۡيَةَ إِمۡلَٰقٖۖ نَّحۡنُ نَرۡزُقُهُمۡ وَإِيَّاكُمۡۚ إِنَّ قَتۡلَهُمۡ كَانَ خِطۡـٔٗا كَبِيرٗا
31. (ሰዎች ሆይ!) ልጆቻችሁንም ድህነትን በመፍራት አትግደሉ:: እኛ እንመግባቸዋለን:: እናንተንም እንመግባችኃለን:: እነርሱን መግደል ታላቅ ኃጢአት ነውና::
Ərəbcə təfsirlər:
وَلَا تَقۡرَبُواْ ٱلزِّنَىٰٓۖ إِنَّهُۥ كَانَ فَٰحِشَةٗ وَسَآءَ سَبِيلٗا
32. (ሰዎች ሆይ!) ዝሙትንም አትቅረቡ:: እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና:: መንገድነቱም ከፋ!
Ərəbcə təfsirlər:
وَلَا تَقۡتُلُواْ ٱلنَّفۡسَ ٱلَّتِي حَرَّمَ ٱللَّهُ إِلَّا بِٱلۡحَقِّۗ وَمَن قُتِلَ مَظۡلُومٗا فَقَدۡ جَعَلۡنَا لِوَلِيِّهِۦ سُلۡطَٰنٗا فَلَا يُسۡرِف فِّي ٱلۡقَتۡلِۖ إِنَّهُۥ كَانَ مَنصُورٗا
33. (ሰዎች ሆይ!) ያቺንም አላህ ያከበራትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ:: የተበደለ ሆኖ ለተገደለም ሰው ዘመዱ በገዳዩ ላይ ስልጣንን አድርገንለታል:: በመግደል ወሰንን አይለፍ:: እርሱ እገዛ ያለው ነውና::
Ərəbcə təfsirlər:
وَلَا تَقۡرَبُواْ مَالَ ٱلۡيَتِيمِ إِلَّا بِٱلَّتِي هِيَ أَحۡسَنُ حَتَّىٰ يَبۡلُغَ أَشُدَّهُۥۚ وَأَوۡفُواْ بِٱلۡعَهۡدِۖ إِنَّ ٱلۡعَهۡدَ كَانَ مَسۡـُٔولٗا
34. (ሰዎች ሆይ!) የየቲምንም ገንዘብ የብርታቱን ጊዜ እስኪደርስ ድረስ በዚያች እርሷ መልካም በሆነች ሁኔታ እንጂ አትቅረቡ:: በቃል ኪዳናችሁም ሙሉ:: ቃል ኪዳን የሚጠየቁበት ጉዳይ ነውና::
Ərəbcə təfsirlər:
وَأَوۡفُواْ ٱلۡكَيۡلَ إِذَا كِلۡتُمۡ وَزِنُواْ بِٱلۡقِسۡطَاسِ ٱلۡمُسۡتَقِيمِۚ ذَٰلِكَ خَيۡرٞ وَأَحۡسَنُ تَأۡوِيلٗا
35. (ሰዎች ሆይ!) በሰፈራችሁም ጊዜ ስፍርን ሙሉ:: በትክክለኛው ሚዛንም መዝኑ:: ይህ መልካም ነገር ነው:: መጨረሻዉም ያማረ ነው::
Ərəbcə təfsirlər:
وَلَا تَقۡفُ مَا لَيۡسَ لَكَ بِهِۦ عِلۡمٌۚ إِنَّ ٱلسَّمۡعَ وَٱلۡبَصَرَ وَٱلۡفُؤَادَ كُلُّ أُوْلَٰٓئِكَ كَانَ عَنۡهُ مَسۡـُٔولٗا
36. (የሰው ልጅ ሆይ!) ላንተ በእርሱ እውቀት የሌለህንም ነገር አትከተል:: መስሚያ፤ ማያ፤ ማሰቢያም እነዚህ ሁሉ ባለቤታቸው ከእነርሱ ተጠያቂ ነውና::
Ərəbcə təfsirlər:
وَلَا تَمۡشِ فِي ٱلۡأَرۡضِ مَرَحًاۖ إِنَّكَ لَن تَخۡرِقَ ٱلۡأَرۡضَ وَلَن تَبۡلُغَ ٱلۡجِبَالَ طُولٗا
37. (የሰው ልጅ ሆይ!) በምድር ላይ የተንበጣረርክ ሆነህም አትሂድ:: አንተ ፈጽሞ ምድርን አትሰረጉድምና:: በርዝመትም ፈጽሞ ጋራዎችን አትደርስምና::
Ərəbcə təfsirlər:
كُلُّ ذَٰلِكَ كَانَ سَيِّئُهُۥ عِندَ رَبِّكَ مَكۡرُوهٗا
38. (የሰው ልጅ ሆይ!) ይህ ሁሉ ክፋቱ ከጌታህ ዘንድ የተጠላ ነው።
Ərəbcə təfsirlər:
 
Mənaların tərcüməsi Surə: əl-İsra
Surələrin mündəricatı Səhifənin rəqəmi
 
Qurani Kərimin mənaca tərcüməsi - Amhar dilinə tərcümə - Afrika Akademiyası. - Tərcumənin mündəricatı

Tərcüməsi Məhəmməd Zeyn Zöhrəddin. Afrika Akademiyası tərəfindən nəşr olunub.

Bağlamaq