Qurani Kərimin mənaca tərcüməsi - الترجمة الأمهرية - زين * - Tərcumənin mündəricatı


Mənaların tərcüməsi Surə: əl-Qəsəs   Ayə:

ሱረቱ አል ቀሰስ

طسٓمٓ
1.ጧ፤ ሲን፤ ሚም፤
Ərəbcə təfsirlər:
تِلۡكَ ءَايَٰتُ ٱلۡكِتَٰبِ ٱلۡمُبِينِ
2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚህ አናቅጽ ገላጭ ከሆነው መጽሐፍ አናቅጽ ናቸው::
Ərəbcə təfsirlər:
نَتۡلُواْ عَلَيۡكَ مِن نَّبَإِ مُوسَىٰ وَفِرۡعَوۡنَ بِٱلۡحَقِّ لِقَوۡمٖ يُؤۡمِنُونَ
3. ከሙሳና ከፈርዖን ዜና ለሚያምኑ ህዝቦች ሁሉ ባንተ ላይ እናነባለን::
Ərəbcə təfsirlər:
إِنَّ فِرۡعَوۡنَ عَلَا فِي ٱلۡأَرۡضِ وَجَعَلَ أَهۡلَهَا شِيَعٗا يَسۡتَضۡعِفُ طَآئِفَةٗ مِّنۡهُمۡ يُذَبِّحُ أَبۡنَآءَهُمۡ وَيَسۡتَحۡيِۦ نِسَآءَهُمۡۚ إِنَّهُۥ كَانَ مِنَ ٱلۡمُفۡسِدِينَ
4. ፈርዖን በምድር ላይ ተንበጣረረ:: ነዋሪዎቿንም የተከፋፈሉ ጓዶች አደረጋቸው:: ከእነርሱም ቡድኖችን ያዳክማል:: ወንዶች ልጆቻቸውን በብዛት ያርዳል:: ሴቶቻቸውንም ይተዋል፤ እርሱ ከሚያበላሹት ሰዎች ነበርና::
Ərəbcə təfsirlər:
وَنُرِيدُ أَن نَّمُنَّ عَلَى ٱلَّذِينَ ٱسۡتُضۡعِفُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَنَجۡعَلَهُمۡ أَئِمَّةٗ وَنَجۡعَلَهُمُ ٱلۡوَٰرِثِينَ
5. በእነዚያ በምድር ውስጥ በተጨቆኑት ህዝቦች ላይ ልንለግስና መሪዎችም ልናደርጋቸው ወራሾችም ልናደርጋቸው እንሻለን::
Ərəbcə təfsirlər:
وَنُمَكِّنَ لَهُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَنُرِيَ فِرۡعَوۡنَ وَهَٰمَٰنَ وَجُنُودَهُمَا مِنۡهُم مَّا كَانُواْ يَحۡذَرُونَ
6. ለእነርሱም በምድር ላይ ልናስመች ፈርዖንን፤ ሃማንንና ሰራዊቶቻቸውንም ከእነርሱ ይፈሩት የነበሩትን ነገር ልናሳያቸው እንሻለን::
Ərəbcə təfsirlər:
وَأَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰٓ أُمِّ مُوسَىٰٓ أَنۡ أَرۡضِعِيهِۖ فَإِذَا خِفۡتِ عَلَيۡهِ فَأَلۡقِيهِ فِي ٱلۡيَمِّ وَلَا تَخَافِي وَلَا تَحۡزَنِيٓۖ إِنَّا رَآدُّوهُ إِلَيۡكِ وَجَاعِلُوهُ مِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
7. ወደ ሙሳም እናት “አጥቢው፤ በእርሱም ላይ በፈራሽ ጊዜ በባህሩ ውስጥ ጣይው፤ አትፍሪም:: አትዘኝም:: እኛ ወዳንቺ መላሾቹና ከመልእክተኞቹም አድራጊዎቹ ነንና” ማለትን አመለከትን (አወረድን)::
Ərəbcə təfsirlər:
فَٱلۡتَقَطَهُۥٓ ءَالُ فِرۡعَوۡنَ لِيَكُونَ لَهُمۡ عَدُوّٗا وَحَزَنًاۗ إِنَّ فِرۡعَوۡنَ وَهَٰمَٰنَ وَجُنُودَهُمَا كَانُواْ خَٰطِـِٔينَ
8. የፈርዖን ቤተሰቦችም መጨረሻው ለእነርሱ ጠላት ሐዘንም ይሆን ዘንድ አነሱት:: ፈርዖንና ሃማንም ሰራዊቶቻቸዉም ኃጢአተኞች ነበሩ::
Ərəbcə təfsirlər:
وَقَالَتِ ٱمۡرَأَتُ فِرۡعَوۡنَ قُرَّتُ عَيۡنٖ لِّي وَلَكَۖ لَا تَقۡتُلُوهُ عَسَىٰٓ أَن يَنفَعَنَآ أَوۡ نَتَّخِذَهُۥ وَلَدٗا وَهُمۡ لَا يَشۡعُرُونَ
9. የፈርዖንም ሚስት “ለእኔም ሆነ ላንተ የዓይናችን መርጊያ ነው:: አትግደሉት:: ሊጠቅመን ወይም ልጅ ልናደርገው ይከጀላልና” አለች:: እነርሱም ፍጻሜውን የማያውቁ ሆነው (አነሱት)::
Ərəbcə təfsirlər:
وَأَصۡبَحَ فُؤَادُ أُمِّ مُوسَىٰ فَٰرِغًاۖ إِن كَادَتۡ لَتُبۡدِي بِهِۦ لَوۡلَآ أَن رَّبَطۡنَا عَلَىٰ قَلۡبِهَا لِتَكُونَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
10. የሙሳም እናት ልብ ባዶ ሆነ:: ከምእምናን ትሆን ዘንድ በልቧ ላይ ባላጠነከርን ኖሮ ልትገልጸው ቀርባ ነበር::
Ərəbcə təfsirlər:
وَقَالَتۡ لِأُخۡتِهِۦ قُصِّيهِۖ فَبَصُرَتۡ بِهِۦ عَن جُنُبٖ وَهُمۡ لَا يَشۡعُرُونَ
11. ለእህቱም “ተከታተይው” አለቻት:: (እርሱንም) እነርሱ የማያውቁ ሲሆኑ በሩቅ ሆና አየችው፤
Ərəbcə təfsirlər:
۞ وَحَرَّمۡنَا عَلَيۡهِ ٱلۡمَرَاضِعَ مِن قَبۡلُ فَقَالَتۡ هَلۡ أَدُلُّكُمۡ عَلَىٰٓ أَهۡلِ بَيۡتٖ يَكۡفُلُونَهُۥ لَكُمۡ وَهُمۡ لَهُۥ نَٰصِحُونَ
12. ወደ እናቱ ከመመለሱ በፊትም አጥቢዎችን መጥባትን በእርሱ ላይ እርም አደረግን:: እህቱም “ለእናንተ የሚያሳድግላችሁን እነርሱም ለእርሱ ቅን አገልጋዮች የሆኑን ቤተሰቦች ላመልክታችሁን?” አለችም።
Ərəbcə təfsirlər:
فَرَدَدۡنَٰهُ إِلَىٰٓ أُمِّهِۦ كَيۡ تَقَرَّ عَيۡنُهَا وَلَا تَحۡزَنَ وَلِتَعۡلَمَ أَنَّ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقّٞ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ
13. ወደ እናቱም ዓይኗ እንድትረጋ እንዳታዝንም የአላህም የተስፋ ቃል እርግጥ መሆኑን እንድታውቅ መለስነው:: ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም::
Ərəbcə təfsirlər:
وَلَمَّا بَلَغَ أَشُدَّهُۥ وَٱسۡتَوَىٰٓ ءَاتَيۡنَٰهُ حُكۡمٗا وَعِلۡمٗاۚ وَكَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ
14. ብርታቱንም በደረሰና በተስተካከለ ጊዜ ጥበብንና እውቀትን ሰጠነው፤ ልክ እንደዚሁም መልካም ሰሪዎችን እንመነዳለን::
Ərəbcə təfsirlər:
وَدَخَلَ ٱلۡمَدِينَةَ عَلَىٰ حِينِ غَفۡلَةٖ مِّنۡ أَهۡلِهَا فَوَجَدَ فِيهَا رَجُلَيۡنِ يَقۡتَتِلَانِ هَٰذَا مِن شِيعَتِهِۦ وَهَٰذَا مِنۡ عَدُوِّهِۦۖ فَٱسۡتَغَٰثَهُ ٱلَّذِي مِن شِيعَتِهِۦ عَلَى ٱلَّذِي مِنۡ عَدُوِّهِۦ فَوَكَزَهُۥ مُوسَىٰ فَقَضَىٰ عَلَيۡهِۖ قَالَ هَٰذَا مِنۡ عَمَلِ ٱلشَّيۡطَٰنِۖ إِنَّهُۥ عَدُوّٞ مُّضِلّٞ مُّبِينٞ
15. ሙሳ ከተማይቱንም ሰዎቿ በዝንጋቴ ላይ ሆነው ሳሉ ገባ:: በእርሷም ውስጥ የሚጋደሉን ሁለት ሰዎች አገኘ:: ይህ (አንዱ) ከወገኑ ነው፤ ይህ (ሌላው) ደግሞ ከጠላቱ ነው፤ ያ ከወገኑ የሆነው ሰው በዚያ ከጣላት በሆነው ሰው ላይ እርዳታን ጠየቀው:: ሙሳም በጡጫ መታው:: ገደለዉም:: “ይህ ከሰይጣን ስራ ነው:: እርሱ ግልጽ አሣሣች ጠላት ነውና” አለ::
Ərəbcə təfsirlər:
قَالَ رَبِّ إِنِّي ظَلَمۡتُ نَفۡسِي فَٱغۡفِرۡ لِي فَغَفَرَ لَهُۥٓۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡغَفُورُ ٱلرَّحِيمُ
16. “ጌታዬ ሆይ! እኔ ነፍሴን በደልኩ ለኔም ማር” አለ ለርሱም ምህረት አደረገለት:: እርሱ መሓሪና አዛኝ ነውና::
Ərəbcə təfsirlər:
قَالَ رَبِّ بِمَآ أَنۡعَمۡتَ عَلَيَّ فَلَنۡ أَكُونَ ظَهِيرٗا لِّلۡمُجۡرِمِينَ
17. “ጌታዬ ሆይ! በእኔ ላይ በመለገስህ ይሁንብኝ (ከስህተቴ እጸጸታለሁ):: ለአመጸኞችም ፈጽሞ ረዳት አልሆንም” አለ::
Ərəbcə təfsirlər:
فَأَصۡبَحَ فِي ٱلۡمَدِينَةِ خَآئِفٗا يَتَرَقَّبُ فَإِذَا ٱلَّذِي ٱسۡتَنصَرَهُۥ بِٱلۡأَمۡسِ يَسۡتَصۡرِخُهُۥۚ قَالَ لَهُۥ مُوسَىٰٓ إِنَّكَ لَغَوِيّٞ مُّبِينٞ
18. በከተማይቱም ውስጥ ፈሪና የሚጠባበቅ ሆኖ አደረ:: በንጋቱም ያ ትላንት እርዳታን የጠየቀው ሰው በጩኸት እርዳታን ይጠይቀዋል:: ሙሳም ለእርሱ፡- “አንተ በእርግጥ ግልጽ ጠማማ ነህ” አለው::
Ərəbcə təfsirlər:
فَلَمَّآ أَنۡ أَرَادَ أَن يَبۡطِشَ بِٱلَّذِي هُوَ عَدُوّٞ لَّهُمَا قَالَ يَٰمُوسَىٰٓ أَتُرِيدُ أَن تَقۡتُلَنِي كَمَا قَتَلۡتَ نَفۡسَۢا بِٱلۡأَمۡسِۖ إِن تُرِيدُ إِلَّآ أَن تَكُونَ جَبَّارٗا فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَا تُرِيدُ أَن تَكُونَ مِنَ ٱلۡمُصۡلِحِينَ
19. ሙሳ ያንን እርሱ ለሁለቱም ጠላት የሆነው ሰው በኃይል ሊይዘው በፈለገም ጊዜ “ሙሳ ሆይ በትላንትናው ቀን ነፍስን እንደ ገደልክ ልትገድለኝ ትፈልጋለህን? በምድር ላይ ጨካኝ መሆንን እንጂ ሌላ አትፈልግም ከመልካም ሰሪዎች መሆንን አትፈልግም” አለው።
Ərəbcə təfsirlər:
وَجَآءَ رَجُلٞ مِّنۡ أَقۡصَا ٱلۡمَدِينَةِ يَسۡعَىٰ قَالَ يَٰمُوسَىٰٓ إِنَّ ٱلۡمَلَأَ يَأۡتَمِرُونَ بِكَ لِيَقۡتُلُوكَ فَٱخۡرُجۡ إِنِّي لَكَ مِنَ ٱلنَّٰصِحِينَ
20. ከከተማይቱም ዳርቻ አንድ ሰው እየሮጠ መጣ “ሙሳ ሆይ! ሹማምንቶቹ ሊገድሉህ ባንተ ይመካከራሉና ውጣ እኔ ላንተ ከመካሪዎች ነኝና” አለው::
Ərəbcə təfsirlər:
فَخَرَجَ مِنۡهَا خَآئِفٗا يَتَرَقَّبُۖ قَالَ رَبِّ نَجِّنِي مِنَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ
21. የፈራና የሚጠባበቅ ሆኖም ከእርሷ ወጣ:: “ጌታዬ ሆይ! ከበደለኞች ህዝቦች አድነኝ” አለ::
Ərəbcə təfsirlər:
وَلَمَّا تَوَجَّهَ تِلۡقَآءَ مَدۡيَنَ قَالَ عَسَىٰ رَبِّيٓ أَن يَهۡدِيَنِي سَوَآءَ ٱلسَّبِيلِ
22. ወደ መድየን አቅጣጫ ፊቱን ባዞረ ጊዜም “ጌታዬ ቀጥተኛውን መንገድ ሊመራኝ እከጅላለሁ” አለ::
Ərəbcə təfsirlər:
وَلَمَّا وَرَدَ مَآءَ مَدۡيَنَ وَجَدَ عَلَيۡهِ أُمَّةٗ مِّنَ ٱلنَّاسِ يَسۡقُونَ وَوَجَدَ مِن دُونِهِمُ ٱمۡرَأَتَيۡنِ تَذُودَانِۖ قَالَ مَا خَطۡبُكُمَاۖ قَالَتَا لَا نَسۡقِي حَتَّىٰ يُصۡدِرَ ٱلرِّعَآءُۖ وَأَبُونَا شَيۡخٞ كَبِيرٞ
23. ወደ መድየንም ውሃ በመጣ ጊዜ እርሱ ላይ ከሰዎች ቡድኖችን መንጋዎቻቸውን የሚያጠጡ ሆነው አገኘ:: ከእነርሱ በታችም ከውሃው መንጎቻቸውን የሚከለክሉ ሁለት ሴቶች ልጆችን አገኘ። “ነገራችሁ ምንድን ነው?” አላቸው። “እረኞች ሁሉ መንጋዎቻቸውን እስከሚመልሱ አናጠጣም። አባታችንም ትልቅ ሽማግሌ ነው።” አሉት::
Ərəbcə təfsirlər:
فَسَقَىٰ لَهُمَا ثُمَّ تَوَلَّىٰٓ إِلَى ٱلظِّلِّ فَقَالَ رَبِّ إِنِّي لِمَآ أَنزَلۡتَ إِلَيَّ مِنۡ خَيۡرٖ فَقِيرٞ
24. ለሁለቱም አጠጣላቸው ከዚያ ወደ ጥላው ዘወር አለና “ጌታዬ ሆይ! እኔ ከመልካም ነገር ወደ እኔ ለምታወርደው ፈላጊ ነኝ” አለ::
Ərəbcə təfsirlər:
فَجَآءَتۡهُ إِحۡدَىٰهُمَا تَمۡشِي عَلَى ٱسۡتِحۡيَآءٖ قَالَتۡ إِنَّ أَبِي يَدۡعُوكَ لِيَجۡزِيَكَ أَجۡرَ مَا سَقَيۡتَ لَنَاۚ فَلَمَّا جَآءَهُۥ وَقَصَّ عَلَيۡهِ ٱلۡقَصَصَ قَالَ لَا تَخَفۡۖ نَجَوۡتَ مِنَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ
25. ከሁለቱ አንደኛይቱም ከሀፍረት ጋር የምትሄድ ሆና ወደ እርሱ መጣች፤ “አባቴ ለእኛ ያጠጣህልንን ዋጋ ሊሰጥህ ይጠራሃል” አለችው፤ ወደ እርሱ በመጣና ወሬውን በእርሱ ላይ በተረከለትም ጊዜ “አትፍራ:: ከበደለኞች ህዝቦች ድነሃል” አለው::
Ərəbcə təfsirlər:
قَالَتۡ إِحۡدَىٰهُمَا يَٰٓأَبَتِ ٱسۡتَـٔۡجِرۡهُۖ إِنَّ خَيۡرَ مَنِ ٱسۡتَـٔۡجَرۡتَ ٱلۡقَوِيُّ ٱلۡأَمِينُ
26. ከሁለቱ አንደኛይቱም “አባቴ ሆይ ቅጠረው ከቀጠርከው ሰው ሁሉ በላጩ፤ ብርቱው፤ ታማኙ ነውና” አለችው።
Ərəbcə təfsirlər:
قَالَ إِنِّيٓ أُرِيدُ أَنۡ أُنكِحَكَ إِحۡدَى ٱبۡنَتَيَّ هَٰتَيۡنِ عَلَىٰٓ أَن تَأۡجُرَنِي ثَمَٰنِيَ حِجَجٖۖ فَإِنۡ أَتۡمَمۡتَ عَشۡرٗا فَمِنۡ عِندِكَۖ وَمَآ أُرِيدُ أَنۡ أَشُقَّ عَلَيۡكَۚ سَتَجِدُنِيٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
27. “ስምንትን ዓመታት ልታገለግለኝ እኔ ከእነዚህ ሁለት ሴቶች ልጆቼ አንዲቷን ላጋባህ እሻለሁ፤ ዐስርን ብትሞላም ካንተ ነው:: ባንተ ላይ ማስቸገርንም አልሻም:: አላህ የሻ እንደሆነ ከመልካም ሰዎች ሆኜ ታገኘኛለህ” አለው::
Ərəbcə təfsirlər:
قَالَ ذَٰلِكَ بَيۡنِي وَبَيۡنَكَۖ أَيَّمَا ٱلۡأَجَلَيۡنِ قَضَيۡتُ فَلَا عُدۡوَٰنَ عَلَيَّۖ وَٱللَّهُ عَلَىٰ مَا نَقُولُ وَكِيلٞ
28. ሙሳም "ይህ ውለታ በእኔና ባንተ መካከል ረጊ ነው:: ከሁለት ጊዜያቶች ማንኛውንም ብፈጽም በእኔ ላይ ወሰን ማለፍ የለም:: አላህ በምንለው ላይ ሁሉ ምስክር ነው" አለ።
Ərəbcə təfsirlər:
۞ فَلَمَّا قَضَىٰ مُوسَى ٱلۡأَجَلَ وَسَارَ بِأَهۡلِهِۦٓ ءَانَسَ مِن جَانِبِ ٱلطُّورِ نَارٗاۖ قَالَ لِأَهۡلِهِ ٱمۡكُثُوٓاْ إِنِّيٓ ءَانَسۡتُ نَارٗا لَّعَلِّيٓ ءَاتِيكُم مِّنۡهَا بِخَبَرٍ أَوۡ جَذۡوَةٖ مِّنَ ٱلنَّارِ لَعَلَّكُمۡ تَصۡطَلُونَ
29. ሙሳም ጊዜውን በጨረሰና ከቤተሰቦቹ ጋር በሄደ ጊዜ ከጡር ተራራ ጎን እሳትን አየ:: ለቤተሰቡም “እዚህ ቆዩ:: እኔ እሳትን አየሁ:: ከእርሷ አጠገብ ወሬ ወይም ትሞቁ ዘንድ ከእሳት ትንታግን (ችቦን) አመጣላችኋለሁ” አለ::
Ərəbcə təfsirlər:
فَلَمَّآ أَتَىٰهَا نُودِيَ مِن شَٰطِيِٕ ٱلۡوَادِ ٱلۡأَيۡمَنِ فِي ٱلۡبُقۡعَةِ ٱلۡمُبَٰرَكَةِ مِنَ ٱلشَّجَرَةِ أَن يَٰمُوسَىٰٓ إِنِّيٓ أَنَا ٱللَّهُ رَبُّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
30. ወደ እርሷ በመጣም ጊዜ ከሸለቆው ቀኝ ዳርቻ ከዛፊቱ በኩል በተባረከችው ስፍራ ውስጥ “ሙሳ ሆይ! እኔ የዓለማት ጌታ አላህ ነኝ” በማለት ተጠራ።
Ərəbcə təfsirlər:
وَأَنۡ أَلۡقِ عَصَاكَۚ فَلَمَّا رَءَاهَا تَهۡتَزُّ كَأَنَّهَا جَآنّٞ وَلَّىٰ مُدۡبِرٗا وَلَمۡ يُعَقِّبۡۚ يَٰمُوسَىٰٓ أَقۡبِلۡ وَلَا تَخَفۡۖ إِنَّكَ مِنَ ٱلۡأٓمِنِينَ
31. “ብትርህንም ጣል” ተባለ:: እንደ ትንሽ እባብ ስትስለከለክ ባያትም ጊዜ ወደ ኋላ ዞሮ ሸሸ:: አልተመለሰምም፤ ተባለም: “ሙሳ ሆይ! ተመለስ አትፍራም፤ አንተ ከጥብቆቹ ነህና
Ərəbcə təfsirlər:
ٱسۡلُكۡ يَدَكَ فِي جَيۡبِكَ تَخۡرُجۡ بَيۡضَآءَ مِنۡ غَيۡرِ سُوٓءٖ وَٱضۡمُمۡ إِلَيۡكَ جَنَاحَكَ مِنَ ٱلرَّهۡبِۖ فَذَٰنِكَ بُرۡهَٰنَانِ مِن رَّبِّكَ إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ وَمَلَإِيْهِۦٓۚ إِنَّهُمۡ كَانُواْ قَوۡمٗا فَٰسِقِينَ
32. "እጅህን በአንገትጌህ ውስጥ አስግባ:: ያለ ነውር ነጭ ሆና ትወጣለችና፤ ክንፍህንም ከፍርሃት ለመዳን ወደ አንተ አጣብቅ:: እነዚህም ከጌታህ የሆኑ ወደ ፈርዖንና ወደ መኳንቶች የሚደርሱ ሁለት አስረጅዎች ናቸው:: እነርሱ አመጠኞች ህዝቦች ነበሩና።“
Ərəbcə təfsirlər:
قَالَ رَبِّ إِنِّي قَتَلۡتُ مِنۡهُمۡ نَفۡسٗا فَأَخَافُ أَن يَقۡتُلُونِ
33. ሙሳ አለ: "ጌታዬ ሆይ! እኔ ከእነርሱ ነፍስን ገድያለሁ ስለዚህ እንዳይገሉኝ እፈራለሁ::
Ərəbcə təfsirlər:
وَأَخِي هَٰرُونُ هُوَ أَفۡصَحُ مِنِّي لِسَانٗا فَأَرۡسِلۡهُ مَعِيَ رِدۡءٗا يُصَدِّقُنِيٓۖ إِنِّيٓ أَخَافُ أَن يُكَذِّبُونِ
34. "ወንድሜንም ሃሩን እርሱ ምላሱ ከእኔ የተባ (የተሻለ) ነው:: እውነተኛነቴንም የሚያረጋግጥልኝ ረዳት ሆኖ ከእኔ ጋር ላከው እኔ ሊያስተባብሉኝ እፈራለሁና።”
Ərəbcə təfsirlər:
قَالَ سَنَشُدُّ عَضُدَكَ بِأَخِيكَ وَنَجۡعَلُ لَكُمَا سُلۡطَٰنٗا فَلَا يَصِلُونَ إِلَيۡكُمَا بِـَٔايَٰتِنَآۚ أَنتُمَا وَمَنِ ٱتَّبَعَكُمَا ٱلۡغَٰلِبُونَ
35. (አላህም)፡- “ጡንቻህን በወንድምህ በእርግጥ እናበረታለን:: ለሁለታችሁም ስልጣንን እናደርጋለን:: ወደ እናንተም በመጥፎ አይደርሱም:: በታዓምራታችን ሂዱ:: እናንተና የተከተላችሁ ሁሉ አሸናፊዎች ናችሁ” አላቸው።
Ərəbcə təfsirlər:
فَلَمَّا جَآءَهُم مُّوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَا بَيِّنَٰتٖ قَالُواْ مَا هَٰذَآ إِلَّا سِحۡرٞ مُّفۡتَرٗى وَمَا سَمِعۡنَا بِهَٰذَا فِيٓ ءَابَآئِنَا ٱلۡأَوَّلِينَ
36. ሙሳም ተዓምራቶቻችንም ግልጽ ሆነው በመጣባቸው ጊዜ “ይህ የተቀጠፈ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም:: ይህንንም በመጀመሪያዎች አባቶቻችን ውስጥ አልሰማንም” አሉ::
Ərəbcə təfsirlər:
وَقَالَ مُوسَىٰ رَبِّيٓ أَعۡلَمُ بِمَن جَآءَ بِٱلۡهُدَىٰ مِنۡ عِندِهِۦ وَمَن تَكُونُ لَهُۥ عَٰقِبَةُ ٱلدَّارِۚ إِنَّهُۥ لَا يُفۡلِحُ ٱلظَّٰلِمُونَ
37. ሙሳም “ጌታዬ ከእርሱ ዘንድ በቀጥታው መንገድ የመጣውን ምስጉኒትም አገር ለእርሱ የምትሆንለትን ሰው አዋቂ ነው:: እነሆ በደለኞች አይድኑም” አለ።
Ərəbcə təfsirlər:
وَقَالَ فِرۡعَوۡنُ يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡمَلَأُ مَا عَلِمۡتُ لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرِي فَأَوۡقِدۡ لِي يَٰهَٰمَٰنُ عَلَى ٱلطِّينِ فَٱجۡعَل لِّي صَرۡحٗا لَّعَلِّيٓ أَطَّلِعُ إِلَىٰٓ إِلَٰهِ مُوسَىٰ وَإِنِّي لَأَظُنُّهُۥ مِنَ ٱلۡكَٰذِبِينَ
38. ፈርዖንም “እናንተ ቡድኖች ሆይ! ከእኔ ሌላ ለእናንተ አምላክን ምንም አላውቅም:: ሃማን ሆይ! ጭቃ ለእኔ አቃጥልልኝ:: ጡብ ስራልኝ:: ለእኔም ከፍተኛ ህንጻን ስራልኝ:: ወደ ሙሳ አምላክ ልወጣ እከጅላለሁና:: እኔም ከውሸታሞች መሆኑን እጠረጥረዋለሁ” አለ።
Ərəbcə təfsirlər:
وَٱسۡتَكۡبَرَ هُوَ وَجُنُودُهُۥ فِي ٱلۡأَرۡضِ بِغَيۡرِ ٱلۡحَقِّ وَظَنُّوٓاْ أَنَّهُمۡ إِلَيۡنَا لَا يُرۡجَعُونَ
39. እርሱም ሰራዊቶቹም በምድር ላይ ያለ አግባብ ኮሩ:: እነርሱም ወደእኛ የማይመለሱ መሆናቸውን ጠረጠሩ::
Ərəbcə təfsirlər:
فَأَخَذۡنَٰهُ وَجُنُودَهُۥ فَنَبَذۡنَٰهُمۡ فِي ٱلۡيَمِّۖ فَٱنظُرۡ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلظَّٰلِمِينَ
40. እርሱንም ሰራዊቱንም በጥብቅ ያዝናቸው:: በባህርም ውስጥ ጣልናቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የበደለኞች መጨረሻም እንዴት እንደነበረ ተመልከት::
Ərəbcə təfsirlər:
وَجَعَلۡنَٰهُمۡ أَئِمَّةٗ يَدۡعُونَ إِلَى ٱلنَّارِۖ وَيَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ لَا يُنصَرُونَ
41. ወደ እሳት የሚጠሩ መሪዎችም አደረግናቸው:: በትንሳኤም ቀን አይረዱም::
Ərəbcə təfsirlər:
وَأَتۡبَعۡنَٰهُمۡ فِي هَٰذِهِ ٱلدُّنۡيَا لَعۡنَةٗۖ وَيَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ هُم مِّنَ ٱلۡمَقۡبُوحِينَ
42. በዚችም በቅርቢቱ ዓለም ውስጥ እርግማንን አስከተልናቸው:: በትንሳኤም ቀን እነርሱ ከሚባረሩት ናቸው::
Ərəbcə təfsirlər:
وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ مِنۢ بَعۡدِ مَآ أَهۡلَكۡنَا ٱلۡقُرُونَ ٱلۡأُولَىٰ بَصَآئِرَ لِلنَّاسِ وَهُدٗى وَرَحۡمَةٗ لَّعَلَّهُمۡ يَتَذَكَّرُونَ
43. የፊተኞቹን የክፍለ ዘመናት ህዝቦችንም ከአጠፋን በኋላ ለሰዎች የልብ ብርሃን መሪም እዝነትም ሲሆን ይገሠጹ ዘንድ ለሙሳ መጽሐፉን በእርግጥ ሰጠነው::
Ərəbcə təfsirlər:
وَمَا كُنتَ بِجَانِبِ ٱلۡغَرۡبِيِّ إِذۡ قَضَيۡنَآ إِلَىٰ مُوسَى ٱلۡأَمۡرَ وَمَا كُنتَ مِنَ ٱلشَّٰهِدِينَ
44. ወደ ሙሳም ትዕዛዝን ባወረድንለት ጊዜ ከተራራው በምዕራባዊው ጎን አልነበርክም:: ከተጣዱትም አልነበርክም::
Ərəbcə təfsirlər:
وَلَٰكِنَّآ أَنشَأۡنَا قُرُونٗا فَتَطَاوَلَ عَلَيۡهِمُ ٱلۡعُمُرُۚ وَمَا كُنتَ ثَاوِيٗا فِيٓ أَهۡلِ مَدۡيَنَ تَتۡلُواْ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتِنَا وَلَٰكِنَّا كُنَّا مُرۡسِلِينَ
45. እኛ ግን ከእርሱ ኋላ አያሌ የክፍለ ዘመናትን ሰዎች አስገኘን:: በእነርሱም ላይ ዕድሜዎች ተራዘሙ:: በመድየንም ሰዎች ውስጥ ተቀማጭና በእነርሱ ላይ አናቅጻችንን የምታነብ አልነበርክም:: እኛ ግን ላኪዎችህ ሆንን::
Ərəbcə təfsirlər:
وَمَا كُنتَ بِجَانِبِ ٱلطُّورِ إِذۡ نَادَيۡنَا وَلَٰكِن رَّحۡمَةٗ مِّن رَّبِّكَ لِتُنذِرَ قَوۡمٗا مَّآ أَتَىٰهُم مِّن نَّذِيرٖ مِّن قَبۡلِكَ لَعَلَّهُمۡ يَتَذَكَّرُونَ
46. በጠራነዉም ጊዜ በጡሩ (ጋራ) ጎን አልነበርክም፤ ግን ካንተ በፊት ምንም አስፈራሪ ያልመጣባቸውን ህዝቦች ታስፈራራ ዘንድ ከጌታህ በሆነ ችሮታ ላክንህ ሊገሠጹ ይከጅላልና።
Ərəbcə təfsirlər:
وَلَوۡلَآ أَن تُصِيبَهُم مُّصِيبَةُۢ بِمَا قَدَّمَتۡ أَيۡدِيهِمۡ فَيَقُولُواْ رَبَّنَا لَوۡلَآ أَرۡسَلۡتَ إِلَيۡنَا رَسُولٗا فَنَتَّبِعَ ءَايَٰتِكَ وَنَكُونَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
47. እጆቻቸዉም ባሳለፉት ምክንያት መከራ የምትነካቸውና “ጌታችን ሆይ! አናቅጽህን እንድንከተል ከትክክለኛ አማኞችም እንድንሆን ወደ እኛ መልዕክተኛን አትልክም ኖሯልን? ይህ ሁሉ የሚሉ ባልሆኑ ኖሮ” አንልክም ነበር።
Ərəbcə təfsirlər:
فَلَمَّا جَآءَهُمُ ٱلۡحَقُّ مِنۡ عِندِنَا قَالُواْ لَوۡلَآ أُوتِيَ مِثۡلَ مَآ أُوتِيَ مُوسَىٰٓۚ أَوَلَمۡ يَكۡفُرُواْ بِمَآ أُوتِيَ مُوسَىٰ مِن قَبۡلُۖ قَالُواْ سِحۡرَانِ تَظَٰهَرَا وَقَالُوٓاْ إِنَّا بِكُلّٖ كَٰفِرُونَ
48. እውነቱም ከኛ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ “ለሙሳ የተሰጠው ብጤ አይሰጠዉም ኖሯልን?” አሉ፤ ከዚህ በፊት ሙሳ በተሰጠው አልካዱምን? “ሁለት የተረዳዱ ድግምቶች ናቸው። እኛ በሁሉም ከሓዲያን ነን” አሉ።
Ərəbcə təfsirlər:
قُلۡ فَأۡتُواْ بِكِتَٰبٖ مِّنۡ عِندِ ٱللَّهِ هُوَ أَهۡدَىٰ مِنۡهُمَآ أَتَّبِعۡهُ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
49. “ከአላህ ዘንድ የሆነን መጽሐፍ እርሱ ከሁለቱም ይበልጥ ቅን የሆነን አምጡ፤ እውነተኞች እንደ ሆናችሁ ብታመጡት እከተለዋለሁ” በላቸው።
Ərəbcə təfsirlər:
فَإِن لَّمۡ يَسۡتَجِيبُواْ لَكَ فَٱعۡلَمۡ أَنَّمَا يَتَّبِعُونَ أَهۡوَآءَهُمۡۚ وَمَنۡ أَضَلُّ مِمَّنِ ٱتَّبَعَ هَوَىٰهُ بِغَيۡرِ هُدٗى مِّنَ ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلظَّٰلِمِينَ
50. እሺ ባይሉህም የሚከተሉት ዝንባሌዎቻቸውን ብቻ መሆኑን ዕወቅ፤ ከአላህም የሆነ መምሪያ ሳይኖረው ዝንባሌውን ብቻ ከተከተለ ይበልጥ የጠመመ አንድም የለም፤ አላህ በደለኞች ህዝቦችን አይመራምና::
Ərəbcə təfsirlər:
۞ وَلَقَدۡ وَصَّلۡنَا لَهُمُ ٱلۡقَوۡلَ لَعَلَّهُمۡ يَتَذَكَّرُونَ
51. ይገሠጹም ዘንድ ቃልን (ቁርኣንን በያይነቱ) ለእነርሱ በእርግጥ አስከታተልን::
Ərəbcə təfsirlər:
ٱلَّذِينَ ءَاتَيۡنَٰهُمُ ٱلۡكِتَٰبَ مِن قَبۡلِهِۦ هُم بِهِۦ يُؤۡمِنُونَ
52. እነዚያም ከእርሱ በፊት መጽሐፍን የሰጠናቸው እነርሱ በእርሱ ያምናሉ::
Ərəbcə təfsirlər:
وَإِذَا يُتۡلَىٰ عَلَيۡهِمۡ قَالُوٓاْ ءَامَنَّا بِهِۦٓ إِنَّهُ ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّنَآ إِنَّا كُنَّا مِن قَبۡلِهِۦ مُسۡلِمِينَ
53. በእነርሱ ላይ በሚነበብላቸዉም ጊዜ «በእርሱ አምነናል:: እርሱ ከጌታችን የሆነ እውነት ነው እኛ ከእርሱ በፊት ሙስሊሞች ነበርን።» ይላሉ።
Ərəbcə təfsirlər:
أُوْلَٰٓئِكَ يُؤۡتَوۡنَ أَجۡرَهُم مَّرَّتَيۡنِ بِمَا صَبَرُواْ وَيَدۡرَءُونَ بِٱلۡحَسَنَةِ ٱلسَّيِّئَةَ وَمِمَّا رَزَقۡنَٰهُمۡ يُنفِقُونَ
54. እነዚያ በመታገሳቸው ምክኒያት ዋጋቸውን ሁለት ጊዜ ይሰጣሉ:: ክፉውንም ነገር በበጎ ምግባር ይገፈትራሉ፤ ከሰጠናቸዉም ሲሳይ ይለግሳሉ::
Ərəbcə təfsirlər:
وَإِذَا سَمِعُواْ ٱللَّغۡوَ أَعۡرَضُواْ عَنۡهُ وَقَالُواْ لَنَآ أَعۡمَٰلُنَا وَلَكُمۡ أَعۡمَٰلُكُمۡ سَلَٰمٌ عَلَيۡكُمۡ لَا نَبۡتَغِي ٱلۡجَٰهِلِينَ
55. ውድቅንም ቃል በሰሙ ጊዜ ከእርሱ ይርቃሉ። «ለእኛ ስራዎቻችን አሉን:: ለእናንተም ስራዎቻችሁ አሉላችሁ:: ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን ባለጌዎችን አንፈልግም።» ይላሉ።
Ərəbcə təfsirlər:
إِنَّكَ لَا تَهۡدِي مَنۡ أَحۡبَبۡتَ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ يَهۡدِي مَن يَشَآءُۚ وَهُوَ أَعۡلَمُ بِٱلۡمُهۡتَدِينَ
56. አንተ የወደድከውን ሰው ፈጽሞ አታቀናም:: ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያቀናል:: እርሱም ቅኖቹን አዋቂ ነው።
Ərəbcə təfsirlər:
وَقَالُوٓاْ إِن نَّتَّبِعِ ٱلۡهُدَىٰ مَعَكَ نُتَخَطَّفۡ مِنۡ أَرۡضِنَآۚ أَوَلَمۡ نُمَكِّن لَّهُمۡ حَرَمًا ءَامِنٗا يُجۡبَىٰٓ إِلَيۡهِ ثَمَرَٰتُ كُلِّ شَيۡءٖ رِّزۡقٗا مِّن لَّدُنَّا وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ
57. «ካንተ ጋር ቅንን መንገድ ብንከተል ከምድራችን እንባረራለን።» አሉም:: ከእኛ ዘንድ የተሰጠ ሲሳይ ሲሆን የነገሩ ሁሉ ፍሬዎች ወደ እርሱ የሚሄዱበትን ጸጥተኛ ክልል (መካን) እነርሱ አላስመቸናቸዉምን? ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም::
Ərəbcə təfsirlər:
وَكَمۡ أَهۡلَكۡنَا مِن قَرۡيَةِۭ بَطِرَتۡ مَعِيشَتَهَاۖ فَتِلۡكَ مَسَٰكِنُهُمۡ لَمۡ تُسۡكَن مِّنۢ بَعۡدِهِمۡ إِلَّا قَلِيلٗاۖ وَكُنَّا نَحۡنُ ٱلۡوَٰرِثِينَ
58. ከከተማም ኑሮዋን ምቾትዋን የካደችን ከተማ ያጠፋናት ብዙ ናት፤ እነዚህም ከእነርሱ በኋላ ጥቂት ጊዜ እንጂ ያልተኖረባቸው ሲሆኑ መኖሪያዎቻቸው ናቸው:: እኛም ከእነርሱ ወራሾች ነበርን።
Ərəbcə təfsirlər:
وَمَا كَانَ رَبُّكَ مُهۡلِكَ ٱلۡقُرَىٰ حَتَّىٰ يَبۡعَثَ فِيٓ أُمِّهَا رَسُولٗا يَتۡلُواْ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتِنَاۚ وَمَا كُنَّا مُهۡلِكِي ٱلۡقُرَىٰٓ إِلَّا وَأَهۡلُهَا ظَٰلِمُونَ
59. ጌታህም ከተሞችን በዋናዋ ከተማ ውስጥ አናቅጻችንን በእነርሱ ላይ የሚያነብ መልዕክተኛን እስከሚልክ ድረስ አጥፊ አልነበረም:: ከተሞችንም ባለቤቶችዋ በዳዮች ሆነው እንጂ አጥፊዎች አልነበርንም::
Ərəbcə təfsirlər:
وَمَآ أُوتِيتُم مِّن شَيۡءٖ فَمَتَٰعُ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَزِينَتُهَاۚ وَمَا عِندَ ٱللَّهِ خَيۡرٞ وَأَبۡقَىٰٓۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ
60. ሰዎች ሆይ! በማንኛዉም ነገር የተሰጣችሁት የቅርቢቱ ሂይወት ጥቅምና ጌጣ ጌጥ ነው:: አላህ ዘንድ ያለዉም ምንዳ በጣም በላጭና ዘውታሪ ነው:: አታውቁምን?
Ərəbcə təfsirlər:
أَفَمَن وَعَدۡنَٰهُ وَعۡدًا حَسَنٗا فَهُوَ لَٰقِيهِ كَمَن مَّتَّعۡنَٰهُ مَتَٰعَ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا ثُمَّ هُوَ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ مِنَ ٱلۡمُحۡضَرِينَ
61. መልካምን ተስፋ ቃል የገባንለትና እርሱም አግኚው የሆነ ሰው የቅርቢቱን ህይወት ጥቅም እንዳስመቸነውና ከዚያ እርሱ በትንሳኤ ቀን ለእሳት ከሚቀረቡት እንደ ሆነው ሰው ነውን?
Ərəbcə təfsirlər:
وَيَوۡمَ يُنَادِيهِمۡ فَيَقُولُ أَيۡنَ شُرَكَآءِيَ ٱلَّذِينَ كُنتُمۡ تَزۡعُمُونَ
62. (አላህ) የሚጠራባቸውንና «እነዚያ ተጋሪዎቼ ትሏቸው የነበራችሁት የት ናቸው?» የሚልበትን ቀን (አስታውስ)::
Ərəbcə təfsirlər:
قَالَ ٱلَّذِينَ حَقَّ عَلَيۡهِمُ ٱلۡقَوۡلُ رَبَّنَا هَٰٓؤُلَآءِ ٱلَّذِينَ أَغۡوَيۡنَآ أَغۡوَيۡنَٰهُمۡ كَمَا غَوَيۡنَاۖ تَبَرَّأۡنَآ إِلَيۡكَۖ مَا كَانُوٓاْ إِيَّانَا يَعۡبُدُونَ
63. እነዚያ በእነርሱ ላይ ቅጣቱ የተረጋገጠባቸው ይላሉ «ጌታችን ሆይ እነዚህ እነዚያ ያጠመምናቸው ናቸው፤ እንደጠመምን አጠመምናቸው (ከእነርሱ) ወደ አንተ ተጥራራን:: እኛን ይገዙ አልነበሩም።»
Ərəbcə təfsirlər:
وَقِيلَ ٱدۡعُواْ شُرَكَآءَكُمۡ فَدَعَوۡهُمۡ فَلَمۡ يَسۡتَجِيبُواْ لَهُمۡ وَرَأَوُاْ ٱلۡعَذَابَۚ لَوۡ أَنَّهُمۡ كَانُواْ يَهۡتَدُونَ
64. «ለአላህ የምታጋሯቸውንም ጥሩ» ይባላሉ:: ይጠሩዋቸዋልም ግን ለእነርሱ አይመልሱላቸዉም:: ቅጣትንም ያያሉ፤ እነርሱ ይመሩ በነበሩ ኖሮ (አያዩትም ነበር)::
Ərəbcə təfsirlər:
وَيَوۡمَ يُنَادِيهِمۡ فَيَقُولُ مَاذَآ أَجَبۡتُمُ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
65. የሚጠራባቸውንና «ለመልዕክተኞች ምንን መለሳችሁ?» የሚልበትን ቀን አስታውስ።
Ərəbcə təfsirlər:
فَعَمِيَتۡ عَلَيۡهِمُ ٱلۡأَنۢبَآءُ يَوۡمَئِذٖ فَهُمۡ لَا يَتَسَآءَلُونَ
66. በዚያም ቀን ወሬዎች ሁሉ በእነርሱ ላይ ይሰወሩባቸዋል፤ እነርሱም አይጠያየቁም::
Ərəbcə təfsirlər:
فَأَمَّا مَن تَابَ وَءَامَنَ وَعَمِلَ صَٰلِحٗا فَعَسَىٰٓ أَن يَكُونَ مِنَ ٱلۡمُفۡلِحِينَ
67. የተጸጸተና ያመነማ መልካምንም የሰራ ከሚድኑት ሊሆን ይከጀላል::
Ərəbcə təfsirlər:
وَرَبُّكَ يَخۡلُقُ مَا يَشَآءُ وَيَخۡتَارُۗ مَا كَانَ لَهُمُ ٱلۡخِيَرَةُۚ سُبۡحَٰنَ ٱللَّهِ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشۡرِكُونَ
68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም የሚፈልገውን ይፈጥራል:: ይመርጣልም:: ለእነርሱ ምርጫ የላቸዉም:: አላህ ከማይገባው ሁሉ ጠራ ከሚያጋሯቸዉም ላቀ::
Ərəbcə təfsirlər:
وَرَبُّكَ يَعۡلَمُ مَا تُكِنُّ صُدُورُهُمۡ وَمَا يُعۡلِنُونَ
69. ጌታህም ልቦቻቸው የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ሁሉ ያውቃል።
Ərəbcə təfsirlər:
وَهُوَ ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ لَهُ ٱلۡحَمۡدُ فِي ٱلۡأُولَىٰ وَٱلۡأٓخِرَةِۖ وَلَهُ ٱلۡحُكۡمُ وَإِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ
70. እርሱም አላህ ነው። ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም:: ምስጋና ሁሉ በመጀመሪያም በመጨረሻይቱም ዓለም ለእርሱ ብቻ ነው:: ፍርዱም የእርሱ ብቻ ነው፤ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ::
Ərəbcə təfsirlər:
قُلۡ أَرَءَيۡتُمۡ إِن جَعَلَ ٱللَّهُ عَلَيۡكُمُ ٱلَّيۡلَ سَرۡمَدًا إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ مَنۡ إِلَٰهٌ غَيۡرُ ٱللَّهِ يَأۡتِيكُم بِضِيَآءٍۚ أَفَلَا تَسۡمَعُونَ
71. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አያችሁን? (እስቲ ንገሩኝ) አላህ በእናንተ ላይ ሌሊትን እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ዘውታሪ ቢያደርገው ከአላህ ሌላ ብርሃንን የሚያመጣላችሁ አምላክ ማነው? አትሰሙምን?» በላቸው።
Ərəbcə təfsirlər:
قُلۡ أَرَءَيۡتُمۡ إِن جَعَلَ ٱللَّهُ عَلَيۡكُمُ ٱلنَّهَارَ سَرۡمَدًا إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ مَنۡ إِلَٰهٌ غَيۡرُ ٱللَّهِ يَأۡتِيكُم بِلَيۡلٖ تَسۡكُنُونَ فِيهِۚ أَفَلَا تُبۡصِرُونَ
72. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አያችሁን? አላህ በእናንተ ላይ ቀንን እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ዘውታሪ ቢያደርገው ከአላህ ሌላ በውስጡ የምታርፉበትን ሌሊት የሚያመጣላችሁ አምላክ ማን ነው? አታስተውሉምን?» በላቸው።
Ərəbcə təfsirlər:
وَمِن رَّحۡمَتِهِۦ جَعَلَ لَكُمُ ٱلَّيۡلَ وَٱلنَّهَارَ لِتَسۡكُنُواْ فِيهِ وَلِتَبۡتَغُواْ مِن فَضۡلِهِۦ وَلَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ
73. ከችሮታዉም ለእናንተ ሌሊትንና ቀንን በውስጡ ልታርፉበት ከትሩፋቱም ልትፈልጉበት አመስጋኞችም ልትሆኑ አደረገላችሁ::
Ərəbcə təfsirlər:
وَيَوۡمَ يُنَادِيهِمۡ فَيَقُولُ أَيۡنَ شُرَكَآءِيَ ٱلَّذِينَ كُنتُمۡ تَزۡعُمُونَ
74. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሚጠራባቸውንም ቀንና «እነዚያ ተጋሪዎቼ ትሉዋቸው የነበራችሁት የት ናቸው?» የሚልበትን ቀን አስታውስ::
Ərəbcə təfsirlər:
وَنَزَعۡنَا مِن كُلِّ أُمَّةٖ شَهِيدٗا فَقُلۡنَا هَاتُواْ بُرۡهَٰنَكُمۡ فَعَلِمُوٓاْ أَنَّ ٱلۡحَقَّ لِلَّهِ وَضَلَّ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَفۡتَرُونَ
75. ከህዝቦችም ሁሉ መስካሪን እናወጣና «ማስረጃችሁን አምጡ» እንላለን። ያን ጊዜ እውነተኛዉም አምላክነት ለአላህ ብቻ መሆኑን ያውቃሉ:: ይቀጣጥፉት የነበሩትም ከእነርሱ ይጠፋባቸዋል::
Ərəbcə təfsirlər:
۞ إِنَّ قَٰرُونَ كَانَ مِن قَوۡمِ مُوسَىٰ فَبَغَىٰ عَلَيۡهِمۡۖ وَءَاتَيۡنَٰهُ مِنَ ٱلۡكُنُوزِ مَآ إِنَّ مَفَاتِحَهُۥ لَتَنُوٓأُ بِٱلۡعُصۡبَةِ أُوْلِي ٱلۡقُوَّةِ إِذۡ قَالَ لَهُۥ قَوۡمُهُۥ لَا تَفۡرَحۡۖ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ ٱلۡفَرِحِينَ
76. ቃሩን ከሙሳ ነገዶች አንዱ ነበር:: በእነርሱም ላይ አመጸ:: ከድልቦችም ያንን መክፈቻዎቹ ብቻ የኃይል ባለቤቶች የሆኑ ቡድኖችን ሸክሙ የሚከብድን ሰጠነው:: ወገኖቹ ለእርሱ ባሉትም ጊዜ አስታውስ: «አትኩራ አላህ ኩራተኞችን አይወድምና።
Ərəbcə təfsirlər:
وَٱبۡتَغِ فِيمَآ ءَاتَىٰكَ ٱللَّهُ ٱلدَّارَ ٱلۡأٓخِرَةَۖ وَلَا تَنسَ نَصِيبَكَ مِنَ ٱلدُّنۡيَاۖ وَأَحۡسِن كَمَآ أَحۡسَنَ ٱللَّهُ إِلَيۡكَۖ وَلَا تَبۡغِ ٱلۡفَسَادَ فِي ٱلۡأَرۡضِۖ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ ٱلۡمُفۡسِدِينَ
77. «አላህም በሰጠህ ሀብት የመጨረሻይቱን አገር ፈልግ:: ሆኖም ከቅርቢቱ አለምም ፈንታህን አትርሳ:: አላህ ወደ አንተ መልካምን እንዳደረገልህ መልካምን አድርግ:: በምድርም ውስጥ ማጥፋትን አትፈልግ:: አላህ አጥፊዎችን አይወድምና።» አሉት።
Ərəbcə təfsirlər:
قَالَ إِنَّمَآ أُوتِيتُهُۥ عَلَىٰ عِلۡمٍ عِندِيٓۚ أَوَلَمۡ يَعۡلَمۡ أَنَّ ٱللَّهَ قَدۡ أَهۡلَكَ مِن قَبۡلِهِۦ مِنَ ٱلۡقُرُونِ مَنۡ هُوَ أَشَدُّ مِنۡهُ قُوَّةٗ وَأَكۡثَرُ جَمۡعٗاۚ وَلَا يُسۡـَٔلُ عَن ذُنُوبِهِمُ ٱلۡمُجۡرِمُونَ
78. «(ሀብትን) የተሰጠሁት እኔ ዘንድ ባለው እውቀት ነው።» አለ። አላህ ከእርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ሰዎች በኃይል ከእርሱ ይበልጥ የበረቱትን ሀብትን በመሰብሰብም ይበልጥ የበዙትን በእርግጥ ያጠፋ መሆኑን አያውቅምን? አመጸኞችም ከኃጢአቶቻቸው ጥያቄ አይጠየቁም።
Ərəbcə təfsirlər:
فَخَرَجَ عَلَىٰ قَوۡمِهِۦ فِي زِينَتِهِۦۖ قَالَ ٱلَّذِينَ يُرِيدُونَ ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَا يَٰلَيۡتَ لَنَا مِثۡلَ مَآ أُوتِيَ قَٰرُونُ إِنَّهُۥ لَذُو حَظٍّ عَظِيمٖ
79. በህዝቦቹም ላይ በጌጡ ውስጥ ሆኖ ወጣ:: እነዚያ ቅርቢቱን ህይወት የሚፈልጉት «ወይ ምኞታችን! ቃሩን የተሰጠው ቢጤ ምነው ለእኛ በኖረን፤ እርሱ የታላቅ ዕድል ባለቤት ነውና።» አሉ።
Ərəbcə təfsirlər:
وَقَالَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡعِلۡمَ وَيۡلَكُمۡ ثَوَابُ ٱللَّهِ خَيۡرٞ لِّمَنۡ ءَامَنَ وَعَمِلَ صَٰلِحٗاۚ وَلَا يُلَقَّىٰهَآ إِلَّا ٱلصَّٰبِرُونَ
80. እነዚያም ዕውቀትን የተሰጡት «ወዮላችሁ! የአላህ ምንዳ ላመነ ሰው መልካምንም ለሰራ በላጭ ነው:: ታጋሾችም እንጂ ሌላው አያገኛትም።» አሉ።
Ərəbcə təfsirlər:
فَخَسَفۡنَا بِهِۦ وَبِدَارِهِ ٱلۡأَرۡضَ فَمَا كَانَ لَهُۥ مِن فِئَةٖ يَنصُرُونَهُۥ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَمَا كَانَ مِنَ ٱلۡمُنتَصِرِينَ
81. በእርሱም በቤትም ምድርን ደረባን (አሰጠምን):: ለእርሱም ከአላህ ሌላ የሚረዱት ቡድኖች ምንም አልነበሩትም:: ከሚረዱትም አልነበረም::
Ərəbcə təfsirlər:
وَأَصۡبَحَ ٱلَّذِينَ تَمَنَّوۡاْ مَكَانَهُۥ بِٱلۡأَمۡسِ يَقُولُونَ وَيۡكَأَنَّ ٱللَّهَ يَبۡسُطُ ٱلرِّزۡقَ لِمَن يَشَآءُ مِنۡ عِبَادِهِۦ وَيَقۡدِرُۖ لَوۡلَآ أَن مَّنَّ ٱللَّهُ عَلَيۡنَا لَخَسَفَ بِنَاۖ وَيۡكَأَنَّهُۥ لَا يُفۡلِحُ ٱلۡكَٰفِرُونَ
82. እነዚያም በትላንትናው ቀን ስፍራውን ይመኙ የነበሩት «ወይ ጉድ! ለካ አላህ ከባሮቹ ለሚሻው ሰው ሲሳይን ያሰፋል:: ያጠባልም:: አላህ በእኛ ላይ በእምነት ባልለገሰልን ኖሮ ምድርን በእኛ ላይ በገለበጠብን ነበር:: ወይ ጉድ! ከሓዲያን አይድኑም።» የሚሉ ሆነው አነጉ።
Ərəbcə təfsirlər:
تِلۡكَ ٱلدَّارُ ٱلۡأٓخِرَةُ نَجۡعَلُهَا لِلَّذِينَ لَا يُرِيدُونَ عُلُوّٗا فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَا فَسَادٗاۚ وَٱلۡعَٰقِبَةُ لِلۡمُتَّقِينَ
83. ይህች የመጨረሻይቱ አገር ናት:: ለእነዚያ በምድር ውስጥ ኩራትንና ማመጽን ለማይፈልጉት ሁሉ እናደርጋታለን:: ምስጉኒቱም መጨረሻ ለጥንቁቆቹ ብቻ ናት::
Ərəbcə təfsirlər:
مَن جَآءَ بِٱلۡحَسَنَةِ فَلَهُۥ خَيۡرٞ مِّنۡهَاۖ وَمَن جَآءَ بِٱلسَّيِّئَةِ فَلَا يُجۡزَى ٱلَّذِينَ عَمِلُواْ ٱلسَّيِّـَٔاتِ إِلَّا مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
84. በደግ ስራ የመጣ ለእርሱ ከእርሷ በላጭ ምንዳ አለው:: በክፉም ስራ የመጡ እነዚህ መጥፎዎችን የሰሩ ይሰሩት የነበሩትን እንጂ አይመነዱም::
Ərəbcə təfsirlər:
إِنَّ ٱلَّذِي فَرَضَ عَلَيۡكَ ٱلۡقُرۡءَانَ لَرَآدُّكَ إِلَىٰ مَعَادٖۚ قُل رَّبِّيٓ أَعۡلَمُ مَن جَآءَ بِٱلۡهُدَىٰ وَمَنۡ هُوَ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ
85. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያ ቁርኣንን የተከፋፈለ ሆኖ ባንተ ላይ ያወረደውና ህግጋቱን እንድትትገበር ግድ ያደረግብህ አምላክ ወደ መመለሻ (ወደ መካ) በእርግጥ መላሽህ ነው። «ጌታዬ በቅን መንገድ የመጣውንና እርሱም በግልጽ ስህተት ውስጥ የሆነውን አዋቂ ነው» በላቸው።
Ərəbcə təfsirlər:
وَمَا كُنتَ تَرۡجُوٓاْ أَن يُلۡقَىٰٓ إِلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبُ إِلَّا رَحۡمَةٗ مِّن رَّبِّكَۖ فَلَا تَكُونَنَّ ظَهِيرٗا لِّلۡكَٰفِرِينَ
86.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መጽሐፉ ወደ አንተ መወረዱን ተስፋ የምታደርግ አልነበርክም :: ግን ከጌታህ ችሮታ ተወረደልህ:: ለከሓዲያን በፍጹም ረዳት አትሁን::
Ərəbcə təfsirlər:
وَلَا يَصُدُّنَّكَ عَنۡ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ بَعۡدَ إِذۡ أُنزِلَتۡ إِلَيۡكَۖ وَٱدۡعُ إِلَىٰ رَبِّكَۖ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ
87.(መልዕክተኛችንሙሐመድ ሆይ!) ከአላህም አናቅጽ ወደ አንተ ከተወረዱ በኋላ አያግዱህ:: ወደ ጌታህም ሰዎችን ጥራ:: ከአጋሪዎችም አትሁን::
Ərəbcə təfsirlər:
وَلَا تَدۡعُ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَۘ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۚ كُلُّ شَيۡءٍ هَالِكٌ إِلَّا وَجۡهَهُۥۚ لَهُ ٱلۡحُكۡمُ وَإِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ
88. ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትገዛ:: ከእርሱም በቀር አምላክ የለም። ከእርሱ በስተቀር ሁሉም ጠፊ ነው:: ፍርዱ የእርሱ ብቻ ነው:: ሁላችሁም ወደ እርሱ ትመለሳላችሁ::
Ərəbcə təfsirlər:
 
Mənaların tərcüməsi Surə: əl-Qəsəs
Surələrin mündəricatı Səhifənin rəqəmi
 
Qurani Kərimin mənaca tərcüməsi - الترجمة الأمهرية - زين - Tərcumənin mündəricatı

ترجمة معاني القرآن الكريم إلى اللغة الأمهرية ترجمها محمد زين نهر الدين صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

Bağlamaq