Check out the new design

Qurani Kərimin mənaca tərcüməsi - Amhar dilinə tərcümə - Afrika Akademiyası. * - Tərcumənin mündəricatı

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Mənaların tərcüməsi Surə: Loğman   Ayə:

አል ሉቅማን

الٓمٓ
1. አሊፍ፤ ላም፤ ሚይም፤
Ərəbcə təfsirlər:
تِلۡكَ ءَايَٰتُ ٱلۡكِتَٰبِ ٱلۡحَكِيمِ
2. እነዚህ አናቅጽ ጥበብ ከተሞላው መጽሐፍ ናቸው።
Ərəbcə təfsirlər:
هُدٗى وَرَحۡمَةٗ لِّلۡمُحۡسِنِينَ
3. ለበጎ አድራጊዎች ሁሉ መሪ፣ እዝነት ሲሆን፤
Ərəbcə təfsirlər:
ٱلَّذِينَ يُقِيمُونَ ٱلصَّلَوٰةَ وَيُؤۡتُونَ ٱلزَّكَوٰةَ وَهُم بِٱلۡأٓخِرَةِ هُمۡ يُوقِنُونَ
4. ለእነዚያ ሶላትን አስተካክለው ለሚሰግዱ፤ ዘካንም ለሚሰጡት፤ በመጨረሻይቱም ዓለም የሚያረጋግጡ ለሆኑት፤
Ərəbcə təfsirlər:
أُوْلَٰٓئِكَ عَلَىٰ هُدٗى مِّن رَّبِّهِمۡۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ
5. እነዚያ (የተጠቀሱትን ባህሪያት የሚላበሱ ሰዎች ሁሉ) በጌታቸው መመሪያ ላይ የሚጓዙ ናቸው። እነዚያ ፍላጎታቸውንም ያገኙትም እነርሱ ብቻ ናቸው::
Ərəbcə təfsirlər:
وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَشۡتَرِي لَهۡوَ ٱلۡحَدِيثِ لِيُضِلَّ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ بِغَيۡرِ عِلۡمٖ وَيَتَّخِذَهَا هُزُوًاۚ أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ عَذَابٞ مُّهِينٞ
6. ከሰዎች መካከል ያለ ምንም እውቀት ሰዎችን ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና የአላህን መንገድ ማላገጫ ሊያደርግ አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ:: እነዚያ ይህን የሚያደርጉ ሁሉ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አለባቸው::
Ərəbcə təfsirlər:
وَإِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِ ءَايَٰتُنَا وَلَّىٰ مُسۡتَكۡبِرٗا كَأَن لَّمۡ يَسۡمَعۡهَا كَأَنَّ فِيٓ أُذُنَيۡهِ وَقۡرٗاۖ فَبَشِّرۡهُ بِعَذَابٍ أَلِيمٍ
7. አናቅጻችን በእርሱ ላይ በሚነበቡ ጊዜ እንዳልሰማትና በጆሮቹ ድንቁርና እንዳለበት የኮራ ሆኖ ይዞራል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህን ሰው በአሳማሚ ቅጣት አብስረው::
Ərəbcə təfsirlər:
إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَهُمۡ جَنَّٰتُ ٱلنَّعِيمِ
8. እነዚያ ያመኑና መልካሞችን ተግባራት የሰሩ ሁሉ ለእነርሱ የጸጋ ገነቶች አሏቸው::
Ərəbcə təfsirlər:
خَٰلِدِينَ فِيهَاۖ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقّٗاۚ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ
9. በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ሲሆኑ አላህ እውነተኛን የተስፋ ቃል ገባላቸው:: እርሱም ሁሉንም አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::
Ərəbcə təfsirlər:
خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ بِغَيۡرِ عَمَدٖ تَرَوۡنَهَاۖ وَأَلۡقَىٰ فِي ٱلۡأَرۡضِ رَوَٰسِيَ أَن تَمِيدَ بِكُمۡ وَبَثَّ فِيهَا مِن كُلِّ دَآبَّةٖۚ وَأَنزَلۡنَا مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَأَنۢبَتۡنَا فِيهَا مِن كُلِّ زَوۡجٖ كَرِيمٍ
10. ሰማያትን የምታዮዋት ምሰሶ ሳያደርግላት ፈጠረ:: በምድርም ውስጥ በእናንተ እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለ:: በእርሷም ላይ ከተንቀሳቃሽ ነገሮች ሁሉ በተነ:: ከሰማይም ውሃን አወረድን:: በእርሷ ውስጥ ከመልካም ዓይነት ሁሉ አበቀልን::
Ərəbcə təfsirlər:
هَٰذَا خَلۡقُ ٱللَّهِ فَأَرُونِي مَاذَا خَلَقَ ٱلَّذِينَ مِن دُونِهِۦۚ بَلِ ٱلظَّٰلِمُونَ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ
11. ይህ ሁሉ የአላህ ፍጡር ነው:: እነዚያ ከእርሱ ሌላ ያሉት ምንን እንደ ፈጠሩ እስኪ አሳዩኝ:: በዳዮች በእውነት በግልጽ ጥመት ውስጥ ናቸው::
Ərəbcə təfsirlər:
 
Mənaların tərcüməsi Surə: Loğman
Surələrin mündəricatı Səhifənin rəqəmi
 
Qurani Kərimin mənaca tərcüməsi - Amhar dilinə tərcümə - Afrika Akademiyası. - Tərcumənin mündəricatı

Tərcüməsi Məhəmməd Zeyn Zöhrəddin. Afrika Akademiyası tərəfindən nəşr olunub.

Bağlamaq