Check out the new design

Qurani Kərimin mənaca tərcüməsi - Amhar dilinə tərcümə - Afrika Akademiyası. * - Tərcumənin mündəricatı

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Mənaların tərcüməsi Surə: əl-Maidə   Ayə:
۞ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَتَّخِذُواْ ٱلۡيَهُودَ وَٱلنَّصَٰرَىٰٓ أَوۡلِيَآءَۘ بَعۡضُهُمۡ أَوۡلِيَآءُ بَعۡضٖۚ وَمَن يَتَوَلَّهُم مِّنكُمۡ فَإِنَّهُۥ مِنۡهُمۡۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلظَّٰلِمِينَ
51. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አይሁድንና ክርስቲያኖችን ረዳቶች አታድርጓቸው:: ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸውና:: ከናንተ ውስጥ እነርሱን ረዳቶቹ (ወዳጆቹ) የሚያደርጋቸው ከእነርሱው ነው:: አላህ አመጸኞችን ህዝቦች አያቀናም።
Ərəbcə təfsirlər:
فَتَرَى ٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٞ يُسَٰرِعُونَ فِيهِمۡ يَقُولُونَ نَخۡشَىٰٓ أَن تُصِيبَنَا دَآئِرَةٞۚ فَعَسَى ٱللَّهُ أَن يَأۡتِيَ بِٱلۡفَتۡحِ أَوۡ أَمۡرٖ مِّنۡ عِندِهِۦ فَيُصۡبِحُواْ عَلَىٰ مَآ أَسَرُّواْ فِيٓ أَنفُسِهِمۡ نَٰدِمِينَ
52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያን በልቦቻቸው ውስጥ የንፍቅና በሽታ ያለባቸውን ሰዎች «የጊዜ መለዋወጥ እንዳያገኘን እንፈራለን።» የሚሉ ሆነው አይሁድን ለመርዳት ሲቻኮሉ ታያቸዋለህ:: አላህ ድል መቀዳጀትን ወይም ከእርሱ ዘንድ የሆነን ነገር ሊያመጣና ከዚያ በነፍሶቻቸው ውስጥ በደበቁት ነገር ተጸፃቾች እንደሚሆኑ ይከጀላል።
Ərəbcə təfsirlər:
وَيَقُولُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَهَٰٓؤُلَآءِ ٱلَّذِينَ أَقۡسَمُواْ بِٱللَّهِ جَهۡدَ أَيۡمَٰنِهِمۡ إِنَّهُمۡ لَمَعَكُمۡۚ حَبِطَتۡ أَعۡمَٰلُهُمۡ فَأَصۡبَحُواْ خَٰسِرِينَ
53. እነዚያ ያመኑት ሰዎች «እነዚያ ‹ከናንተ ጋር ነን› ብለው የጠነከረ መሀላቸውን በአላህ የማሉት እነዚህ ናቸውን?» ይላሉ:: ስራዎቻቸዉም ተበላሹ:: ከሳሪዎችም ሆኑ::
Ərəbcə təfsirlər:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَن يَرۡتَدَّ مِنكُمۡ عَن دِينِهِۦ فَسَوۡفَ يَأۡتِي ٱللَّهُ بِقَوۡمٖ يُحِبُّهُمۡ وَيُحِبُّونَهُۥٓ أَذِلَّةٍ عَلَى ٱلۡمُؤۡمِنِينَ أَعِزَّةٍ عَلَى ٱلۡكَٰفِرِينَ يُجَٰهِدُونَ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ وَلَا يَخَافُونَ لَوۡمَةَ لَآئِمٖۚ ذَٰلِكَ فَضۡلُ ٱللَّهِ يُؤۡتِيهِ مَن يَشَآءُۚ وَٱللَّهُ وَٰسِعٌ عَلِيمٌ
54. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእናንተ ውስጥ ከሃይማኖቱ ወደ ክህደት የሚመለስ ሁሉ አላህ በእርሱ ስፍራ የሚወዳቸውና የሚወዱትን በምዕምናን ላይ ትሁቶች፤ በከሓዲያን ላይ ሀያላን፤ የሆኑትንና በአላህ መንገድ የሚታገሉን የወቃሽንም ወቀሳ የማይፈሩ ህዝቦችን ያመጣል:: ይህ የአላህ ችሮታ ነው:: ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል:: አላህ ችሮታው ሰፊ ሁሉንም አዋቂ ነውና።
Ərəbcə təfsirlər:
إِنَّمَا وَلِيُّكُمُ ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱلَّذِينَ يُقِيمُونَ ٱلصَّلَوٰةَ وَيُؤۡتُونَ ٱلزَّكَوٰةَ وَهُمۡ رَٰكِعُونَ
55. (አማኞች ሆይ!) ረዳታችሁ አላህና መልዕክተኛው እንደዚሁም እነዚያ በአላህ ያመኑት ናቸው:: እነርሱ ማለት እነዚያ ሶላትን በደንቡ የሚሰግዱ እነርሱም (ለአምልኮ) የሚያጎነብሱ ሆነው ምጽዋትን የሚሰጡ ናቸው::
Ərəbcə təfsirlər:
وَمَن يَتَوَلَّ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ فَإِنَّ حِزۡبَ ٱللَّهِ هُمُ ٱلۡغَٰلِبُونَ
56. አላህን፤ መልዕክተኛውንና እንደዚሁ እነዚያ በአላህ ያመኑትን ሰዎች የሚወዳጅ (ከአላህ ጭፍሮች ይሆናል።) የአላህ ጭፍሮች ደግሞ አሸናፊዎቹ ናቸው::
Ərəbcə təfsirlər:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَتَّخِذُواْ ٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُواْ دِينَكُمۡ هُزُوٗا وَلَعِبٗا مِّنَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ مِن قَبۡلِكُمۡ وَٱلۡكُفَّارَ أَوۡلِيَآءَۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ
57. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእነዚያ ከበፊታችሁ መጽሐፉን ከተሰጡትና ከእነዚያ ሃይማኖታችሁን መሳለቂያና መጫዎቻ ካደረጉት ከሓዲያን መካከል ወዳጆች አታድርጉ:: ትክክለኛ አማኞች እንደሆናችሁ አላህን ብቻ ፍሩ::
Ərəbcə təfsirlər:
 
Mənaların tərcüməsi Surə: əl-Maidə
Surələrin mündəricatı Səhifənin rəqəmi
 
Qurani Kərimin mənaca tərcüməsi - Amhar dilinə tərcümə - Afrika Akademiyası. - Tərcumənin mündəricatı

Tərcüməsi Məhəmməd Zeyn Zöhrəddin. Afrika Akademiyası tərəfindən nəşr olunub.

Bağlamaq