Check out the new design

Qurani Kərimin mənaca tərcüməsi - Amhar dilinə tərcümə - Afrika Akademiyası. * - Tərcumənin mündəricatı

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Mənaların tərcüməsi Surə: əl-Mucadilə   Ayə:

አል ሙጃደላ

قَدۡ سَمِعَ ٱللَّهُ قَوۡلَ ٱلَّتِي تُجَٰدِلُكَ فِي زَوۡجِهَا وَتَشۡتَكِيٓ إِلَى ٱللَّهِ وَٱللَّهُ يَسۡمَعُ تَحَاوُرَكُمَآۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعُۢ بَصِيرٌ
1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ የዚያችን በባሏ ጉዳይ ላይ የምትከራከርህንና ወደ አላህ ስሞታን የምታሰማውን ሴትዮ ቃል ሰማ:: አላህ በንግግር መመላለሳችሁን (መወያየታችሁን) ይሰማል:: አላህ (ለሚባለው) ሁሉ ሰሚ (ለሚፈጸመው ሁሉ ነገር) አዋቂ ነውና።
Ərəbcə təfsirlər:
ٱلَّذِينَ يُظَٰهِرُونَ مِنكُم مِّن نِّسَآئِهِم مَّا هُنَّ أُمَّهَٰتِهِمۡۖ إِنۡ أُمَّهَٰتُهُمۡ إِلَّا ٱلَّٰٓـِٔي وَلَدۡنَهُمۡۚ وَإِنَّهُمۡ لَيَقُولُونَ مُنكَرٗا مِّنَ ٱلۡقَوۡلِ وَزُورٗاۚ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَعَفُوٌّ غَفُورٞ
2. እነዚያ ከናንተ መካከል ሚስቶቻቸውን እንደእናቶቻቸው ጀርባዎች ይሁኑብን በማለት የሚምሉ ሰዎች እነርሱ እናቶቻቸው አይደሉም:: ትክክለኛ እናቶቻቸው እነዚያ የወለዷቸው ሴቶች ብቻ ናቸው:: እነርሱ በዚህ ቃል የተጠላ ንግግርንና ውሸትን በእርግጥ ይናገራሉ:: አላህ ለሚጸጸት ሰው ሁሉ ይቅር ባይና መሀሪ ነው::
Ərəbcə təfsirlər:
وَٱلَّذِينَ يُظَٰهِرُونَ مِن نِّسَآئِهِمۡ ثُمَّ يَعُودُونَ لِمَا قَالُواْ فَتَحۡرِيرُ رَقَبَةٖ مِّن قَبۡلِ أَن يَتَمَآسَّاۚ ذَٰلِكُمۡ تُوعَظُونَ بِهِۦۚ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ خَبِيرٞ
3. እነዚያ ሚስቶቻቸውን እንደእናቶቻቸው ጀርባዎች ይሁኑብን በማለት የሚምሉና ከዚያ ወደ ተናገሩት የሚመለሱ ሳይነካኩ በፊት በባርነት የተያዘችዋን ጫንቃ ነፃ ማውጣት ግዴታ አለባቸው:: ይህ ህግ (የተጠቀሰው ህግ) በእርሱ ትገሰጹበታላችሁ:: አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው።
Ərəbcə təfsirlər:
فَمَن لَّمۡ يَجِدۡ فَصِيَامُ شَهۡرَيۡنِ مُتَتَابِعَيۡنِ مِن قَبۡلِ أَن يَتَمَآسَّاۖ فَمَن لَّمۡ يَسۡتَطِعۡ فَإِطۡعَامُ سِتِّينَ مِسۡكِينٗاۚ ذَٰلِكَ لِتُؤۡمِنُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦۚ وَتِلۡكَ حُدُودُ ٱللَّهِۗ وَلِلۡكَٰفِرِينَ عَذَابٌ أَلِيمٌ
4. ይህን ላላገኘም ሰው ከመነካካታቸው በፊት ሁለት ተከታታይ ወሮችን መፆም አለበት:: ይህን ላልቻለም ሰው ስልሳ ድሆችን ማብላት አለበት:: ይህ በአላህና በመልዕክተኛው እንድታምኑ ነው:: እነኚህ ህግጋት የአላህ ህግጋት ናቸው:: (እናም አትተላለፏቸው::) ለከሓዲያንም ሁሉ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::
Ərəbcə təfsirlər:
إِنَّ ٱلَّذِينَ يُحَآدُّونَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ كُبِتُواْ كَمَا كُبِتَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ وَقَدۡ أَنزَلۡنَآ ءَايَٰتِۭ بَيِّنَٰتٖۚ وَلِلۡكَٰفِرِينَ عَذَابٞ مُّهِينٞ
5. ግልጽ ማስረጃዎችን ያወረድን ስንሆን እነዚያ አላህንና መልዕክተኛውን የሚከራከሩ ሰዎች እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩ ሰዎች እንደተዋረዱት ሁሉ ተዋርደዋል:: ለከሓዲያን አዋራጅ ቅጣት አለባቸው::
Ərəbcə təfsirlər:
يَوۡمَ يَبۡعَثُهُمُ ٱللَّهُ جَمِيعٗا فَيُنَبِّئُهُم بِمَا عَمِلُوٓاْۚ أَحۡصَىٰهُ ٱللَّهُ وَنَسُوهُۚ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ شَهِيدٌ
6. አላህ ሁላቸውንም በአንድ አድርጎ (አንድም ሳይቀር በአንድ ዓይነት) በሚቀሰቅሳቸው ቀን (ይቀጣቸዋል):: ከዚያም በዚህ ዓለም የሰሩትን ነገር ሁሉ ይነግራቸዋል:: እነርሱ የረሱት ሲሆን (መዝገባቸው ተመዝግቦ ያገኙታል) አላህ ግን አንድም ሳይቀር አውቆታል:: አላህ ሁሉንም ነገር ተመልካች ነውና::
Ərəbcə təfsirlər:
 
Mənaların tərcüməsi Surə: əl-Mucadilə
Surələrin mündəricatı Səhifənin rəqəmi
 
Qurani Kərimin mənaca tərcüməsi - Amhar dilinə tərcümə - Afrika Akademiyası. - Tərcumənin mündəricatı

Tərcüməsi Məhəmməd Zeyn Zöhrəddin. Afrika Akademiyası tərəfindən nəşr olunub.

Bağlamaq