Check out the new design

Übersetzung der Bedeutungen von dem heiligen Quran - Amharische Übersetzung - Muhammad Sadiq * - Übersetzungen

XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Übersetzung der Bedeutungen Surah / Kapitel: Ġāfir   Vers:

ጋፊር

حمٓ
ሓ.ሚም፤
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
تَنزِيلُ ٱلۡكِتَٰبِ مِنَ ٱللَّهِ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡعَلِيمِ
የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊ ዐዋቂ ከሆነው አላህ ነው፡፡
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
غَافِرِ ٱلذَّنۢبِ وَقَابِلِ ٱلتَّوۡبِ شَدِيدِ ٱلۡعِقَابِ ذِي ٱلطَّوۡلِۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ إِلَيۡهِ ٱلۡمَصِيرُ
ኀጢአትን መሓሪ፣ ጸጸትንም ተቀባይ፣ ቅጣተ ብርቱ፣ የልግስና ባለቤት ከኾነው (አላህ የወረደ ነው)፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ መመለሻው ወደርሱ ብቻ ነው፡፡
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
مَا يُجَٰدِلُ فِيٓ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ إِلَّا ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فَلَا يَغۡرُرۡكَ تَقَلُّبُهُمۡ فِي ٱلۡبِلَٰدِ
በአላህ አንቀጾች እነዚያ የካዱት ቢኾኑ እንጅ ማንም (በመዝለፍ) አይከራከርም፡፡ በያገሮችም ውስጥ መዘዋወራቸው አይሸንግልህ፡፡
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
كَذَّبَتۡ قَبۡلَهُمۡ قَوۡمُ نُوحٖ وَٱلۡأَحۡزَابُ مِنۢ بَعۡدِهِمۡۖ وَهَمَّتۡ كُلُّ أُمَّةِۭ بِرَسُولِهِمۡ لِيَأۡخُذُوهُۖ وَجَٰدَلُواْ بِٱلۡبَٰطِلِ لِيُدۡحِضُواْ بِهِ ٱلۡحَقَّ فَأَخَذۡتُهُمۡۖ فَكَيۡفَ كَانَ عِقَابِ
ከእነርሱ በፊት የኑሕ ሕዝቦች ከኋላቸውም አሕዛቦቹ አስተባባሉ፡፡ ሕዝቦችም ሁሉ መልክተኛቸውን ሊይዙ አሰቡ፡፡ በውሸትም በእርሱ እውነትን ሊያጠፉበት ተከራከሩ፡፡ ያዝኳቸውም፡፡ ታዲያ ቅጣቴ እንዴት ነበር?
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
وَكَذَٰلِكَ حَقَّتۡ كَلِمَتُ رَبِّكَ عَلَى ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ أَنَّهُمۡ أَصۡحَٰبُ ٱلنَّارِ
እንደዚሁም የጌታህ ቃል በእነዚያ በካዱት ላይ እነርሱ የእሳት ጓዶች ናቸው ማለት ተረጋገጠች፡፡
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
ٱلَّذِينَ يَحۡمِلُونَ ٱلۡعَرۡشَ وَمَنۡ حَوۡلَهُۥ يُسَبِّحُونَ بِحَمۡدِ رَبِّهِمۡ وَيُؤۡمِنُونَ بِهِۦ وَيَسۡتَغۡفِرُونَ لِلَّذِينَ ءَامَنُواْۖ رَبَّنَا وَسِعۡتَ كُلَّ شَيۡءٖ رَّحۡمَةٗ وَعِلۡمٗا فَٱغۡفِرۡ لِلَّذِينَ تَابُواْ وَٱتَّبَعُواْ سَبِيلَكَ وَقِهِمۡ عَذَابَ ٱلۡجَحِيمِ
እነዚያ ዐርሹን የሚሸከሙት እነዚያም በዙሪያው ያሉት በጌታቸው ምስጋና ያወድሳሉ፡፡ በእርሱም ያምናሉ፡፡ «ጌታችን ሆይ! ነገሩን ሁሉ በእዝነትና በዕውቀት ከበሃል፡፡ ስለዚህ ለእነዚያ ለተጸጸቱት መንገድህንም ለተከተሉት ምሕረት አድርግላቸው፡፡ የእሳትንም ቅጣት ጠብቃቸው፡፡» እያሉ ለእነዚያ ላመኑት ምሕረትን ይለምናሉ፡፡
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
 
Übersetzung der Bedeutungen Surah / Kapitel: Ġāfir
Suren/ Kapiteln Liste Nummer der Seite
 
Übersetzung der Bedeutungen von dem heiligen Quran - Amharische Übersetzung - Muhammad Sadiq - Übersetzungen

Übersetzt von Sheikh Muhammad Sadiq und Muhammad al-Thani Habib. Die Übersetzung wurde unter der Aufsicht des Rowwad-Übersetzungszentrums entwickelt. Es ist möglich sich die Originalübersetzung zum Zwecke der Meinungsäußerung, Bewertung und kontinuierlichen Weiterentwicklung anzuschauen.

Schließen