Check out the new design

Übersetzung der Bedeutungen von dem heiligen Quran - Amharische Übersetzung - Akademie Afrika * - Übersetzungen


Übersetzung der Bedeutungen Surah / Kapitel: Al-Aḥqāf   Vers:

አል አህቃፍ

حمٓ
1. ሓ፤ ሚይም፤
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
تَنزِيلُ ٱلۡكِتَٰبِ مِنَ ٱللَّهِ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡحَكِيمِ
2. የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊ፤ ጥበበኛ ከሆነው አላህ ነው::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
مَا خَلَقۡنَا ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ وَمَا بَيۡنَهُمَآ إِلَّا بِٱلۡحَقِّ وَأَجَلٖ مُّسَمّٗىۚ وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ عَمَّآ أُنذِرُواْ مُعۡرِضُونَ
3. ሰማያትን፤ ምድርን እና በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በምር እና በተወሰነ ጊዜንም በመለካት እንጂ ለቀልድ አልፈጠርናቸዉም። እነዚያ በአላህ የካዱት የተስፈራሩትን ነገር ደንታ አይሰጡትም።
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
قُلۡ أَرَءَيۡتُم مَّا تَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَرُونِي مَاذَا خَلَقُواْ مِنَ ٱلۡأَرۡضِ أَمۡ لَهُمۡ شِرۡكٞ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِۖ ٱئۡتُونِي بِكِتَٰبٖ مِّن قَبۡلِ هَٰذَآ أَوۡ أَثَٰرَةٖ مِّنۡ عِلۡمٍ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
4. (መልዕክተኛችንሙሐመድ ሆይ!) «ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን አላያችሁምን? ከምድር ምንን እንደፈጠሩ እስቲ አሳዩኝ:: ወይስ በሰማያት መፍጠር ለእነርሱ ከአላህ ጋር መጋራት አላቸውን? (ያማልዱናል በማለታችሁ) እውነተኞች እንደሆናችሁ ይህንን ጉዳይ ከዚህ በፊት የሆነን መጽሐፍ ወይም ከእውቀት ቅሪት እስቲ አምጡልኝ» በላቸው::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
وَمَنۡ أَضَلُّ مِمَّن يَدۡعُواْ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَن لَّا يَسۡتَجِيبُ لَهُۥٓ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ وَهُمۡ عَن دُعَآئِهِمۡ غَٰفِلُونَ
5. እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስም ለእርሱ የማይመልሱለትን ጣዖታት ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማንነው? እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
 
Übersetzung der Bedeutungen Surah / Kapitel: Al-Aḥqāf
Suren/ Kapiteln Liste Nummer der Seite
 
Übersetzung der Bedeutungen von dem heiligen Quran - Amharische Übersetzung - Akademie Afrika - Übersetzungen

Übersetzt von Muhammad Zain Zaher Al-Din. Herausgegeben von der Afrika-Akademie.

Schließen