Check out the new design

Übersetzung der Bedeutungen von dem heiligen Quran - Amharische Übersetzung - Akademie Afrika * - Übersetzungen


Übersetzung der Bedeutungen Surah / Kapitel: Al-Ḥaschr   Vers:

አል ሐሽር

سَبَّحَ لِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۖ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ
1. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ አላህን አጠራ:: እርሱም ሁሉንም አሸናፊና ጥበበኛው ነው::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
هُوَ ٱلَّذِيٓ أَخۡرَجَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِنۡ أَهۡلِ ٱلۡكِتَٰبِ مِن دِيَٰرِهِمۡ لِأَوَّلِ ٱلۡحَشۡرِۚ مَا ظَنَنتُمۡ أَن يَخۡرُجُواْۖ وَظَنُّوٓاْ أَنَّهُم مَّانِعَتُهُمۡ حُصُونُهُم مِّنَ ٱللَّهِ فَأَتَىٰهُمُ ٱللَّهُ مِنۡ حَيۡثُ لَمۡ يَحۡتَسِبُواْۖ وَقَذَفَ فِي قُلُوبِهِمُ ٱلرُّعۡبَۚ يُخۡرِبُونَ بُيُوتَهُم بِأَيۡدِيهِمۡ وَأَيۡدِي ٱلۡمُؤۡمِنِينَ فَٱعۡتَبِرُواْ يَٰٓأُوْلِي ٱلۡأَبۡصَٰرِ
2. እርሱ ያ! ከመጽሐፍ ሰዎች መካከል እነዚያን በአላህ የካዱትን ወገኖች ከቤቶቻቸው የመጀመሪያውን ማስወጣት ያስወጣቸው ነው:: (ሙስሊሞች ሆይ!) መውጣታቸውንም አላሰባችሁትም ነበር:: እነርሱም ምሽጎቻቸው ከአላህ ኃይል የሚከላከሉላቸው መሆናቸውን አሰቡ:: አላህ ግን ካላሰቡት በኩል መጣባቸው:: እናም በልቦቻቸው ውስጥ መርበድበድን (ፍርሃትን) ጣለባቸው:: ቤቶቻቸውን በገዛ እጆቻቸውና በትክክለኛ አማኞች እጅ ያፈርሳሉ (አፈረሱ):: እናንተ የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ! አስተውሉ::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
وَلَوۡلَآ أَن كَتَبَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِمُ ٱلۡجَلَآءَ لَعَذَّبَهُمۡ فِي ٱلدُّنۡيَاۖ وَلَهُمۡ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ عَذَابُ ٱلنَّارِ
3. በእነርሱም ላይ አላህ ከአገር መውጣትን ባልፈረደ ኖሮ በቅርቢቱ ዓለም በቀጣቸው ነበር:: ለእነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም የእሳት ቅጣት አለባቸው::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ شَآقُّواْ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥۖ وَمَن يُشَآقِّ ٱللَّهَ فَإِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ
4. ይህ እነርሱ አላህንና መልዕክተኛውን በመከራከራቸው ምክንያት ነው:: አላህን የሚከራከር ሰው ሁሉ (ይቀጣዋል።) አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና ይቀጣቸዋል::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
مَا قَطَعۡتُم مِّن لِّينَةٍ أَوۡ تَرَكۡتُمُوهَا قَآئِمَةً عَلَىٰٓ أُصُولِهَا فَبِإِذۡنِ ٱللَّهِ وَلِيُخۡزِيَ ٱلۡفَٰسِقِينَ
5. ከዘንባባ (ከተምር ዛፍ) ማንኛዋም የቆረጣችኋት ወይም በግንዶቿ ላይ የቆመች ሆና የተዋችኋት ሁሉ በአላህ ፈቃድ ነው:: አመጸኞችንም ያዋርድ ዘንድ (መቁረጥን ፈቀደ)::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
وَمَآ أَفَآءَ ٱللَّهُ عَلَىٰ رَسُولِهِۦ مِنۡهُمۡ فَمَآ أَوۡجَفۡتُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ خَيۡلٖ وَلَا رِكَابٖ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ يُسَلِّطُ رُسُلَهُۥ عَلَىٰ مَن يَشَآءُۚ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ
6. ከእነርሱም ገንዘብ ወደ መልዕክተኛው አላህ የመለሰውን በእርሱ ላይ ፈረሶችንና ግመሎችን አላስጋልባችሁበትም:: ግን አላህ መልዕክተኞቹን በሚሻው ላይ ይሾማል:: አላህ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነውና::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
مَّآ أَفَآءَ ٱللَّهُ عَلَىٰ رَسُولِهِۦ مِنۡ أَهۡلِ ٱلۡقُرَىٰ فَلِلَّهِ وَلِلرَّسُولِ وَلِذِي ٱلۡقُرۡبَىٰ وَٱلۡيَتَٰمَىٰ وَٱلۡمَسَٰكِينِ وَٱبۡنِ ٱلسَّبِيلِ كَيۡ لَا يَكُونَ دُولَةَۢ بَيۡنَ ٱلۡأَغۡنِيَآءِ مِنكُمۡۚ وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمۡ عَنۡهُ فَٱنتَهُواْۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ
7. አላህ ከከተሞች ሰዎች ሀብት መካከል በመልዕክተኛው ላይ የመለሰው ሀብት ከናንተ ውስጥ በሀብታሞች መካከል ብቻ ተዘዋዋሪ እንዳይሆን ለአላህና ለመልዕክተኛው፤ ለዝምድና ባለቤትም፤ አባት ለሌላቸው የቲም ልጆችም፤ ለድሆችና፤ ለመንገደኛ፤ የሚሰጥ ነው:: መልዕክተኛው የሰጣችሁን ሁሉ ማንኛዉም ነገር ያዙት:: የከለከላችሁን ነገር ሁሉም ተከልከሉ:: አላህን ፍሩ። አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
لِلۡفُقَرَآءِ ٱلۡمُهَٰجِرِينَ ٱلَّذِينَ أُخۡرِجُواْ مِن دِيَٰرِهِمۡ وَأَمۡوَٰلِهِمۡ يَبۡتَغُونَ فَضۡلٗا مِّنَ ٱللَّهِ وَرِضۡوَٰنٗا وَيَنصُرُونَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥٓۚ أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلصَّٰدِقُونَ
8. ለእነዚያ የአላህን ችሮታና ውዴታውን የሚፈልጉና አላህንና መልዕክተኛውን የሚረዱ ሆነው ከአገሮቻቸውና ከገንዘቦቻቸው ለተወጡ (ለተባረሩ) ስደተኞች ድሆች ይሰጣል:: እነዚያ እነርሱ እውነተኞች ናቸው::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
وَٱلَّذِينَ تَبَوَّءُو ٱلدَّارَ وَٱلۡإِيمَٰنَ مِن قَبۡلِهِمۡ يُحِبُّونَ مَنۡ هَاجَرَ إِلَيۡهِمۡ وَلَا يَجِدُونَ فِي صُدُورِهِمۡ حَاجَةٗ مِّمَّآ أُوتُواْ وَيُؤۡثِرُونَ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمۡ وَلَوۡ كَانَ بِهِمۡ خَصَاصَةٞۚ وَمَن يُوقَ شُحَّ نَفۡسِهِۦ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ
9..እነዚያ ከበፊታቸው ሀገሪቱን መዲና መኖሪያ ያደረጓትና እምነት በልባቸው የሰረጸባቸው ወደ እነርሱ የተሰደዱትን ሰዎች ይወዳሉ:: ስደተኞችም ከተሰጡት ነገር ላይ በልቦቻቸው ውስጥ እንኳን ምንም ቅሬታን አያሳድሩም:: በእነርሱ ላይ ችግር ቢኖርባቸዉም እንኳ በነፍሶቻቸው ላይ ሌላውን ያስቀድማሉ:: ከነፍሶቻቸው ንፉግነት የሚጠበቁ ሰዎች ሁሉ እነዚያ የተሳካለቸውና ምኞታቸውን አግኚዎች ማለት እነርሱ ብቻ ናቸው::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
وَٱلَّذِينَ جَآءُو مِنۢ بَعۡدِهِمۡ يَقُولُونَ رَبَّنَا ٱغۡفِرۡ لَنَا وَلِإِخۡوَٰنِنَا ٱلَّذِينَ سَبَقُونَا بِٱلۡإِيمَٰنِ وَلَا تَجۡعَلۡ فِي قُلُوبِنَا غِلّٗا لِّلَّذِينَ ءَامَنُواْ رَبَّنَآ إِنَّكَ رَءُوفٞ رَّحِيمٌ
10. እነዚያ ከበኋላቸው የመጡት «ጌታችን ሆይ! ለእኛም ለእነዚያም በእምነት ለቀደሙን ወንድሞቻችንም ምህረት አድርግ:: በልቦቻችንም ውስጥ ለእነዚያ ለአመኑት ሰዎች ሁሉ ጥላቻን አታድርግ:: ጌታችን ሆይ! አንተ ሩህሩህ፤ አዛኝ ነህና» ይላሉ።
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
۞ أَلَمۡ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ نَافَقُواْ يَقُولُونَ لِإِخۡوَٰنِهِمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِنۡ أَهۡلِ ٱلۡكِتَٰبِ لَئِنۡ أُخۡرِجۡتُمۡ لَنَخۡرُجَنَّ مَعَكُمۡ وَلَا نُطِيعُ فِيكُمۡ أَحَدًا أَبَدٗا وَإِن قُوتِلۡتُمۡ لَنَنصُرَنَّكُمۡ وَٱللَّهُ يَشۡهَدُ إِنَّهُمۡ لَكَٰذِبُونَ
11. እነዚያን ወደ ንፍቅና የገቡትን አላወክምን? ከመጽሐፍ ሰዎች መካከል ለእነዚያ ለካዱት ወንድሞቻቸው «ከአገር ብትባርሩ አብረናችሁ እንወጣለን:: በእናንተ ጉዳይ አንድንም ሰው በፍጹም ሁልጊዜም አንታዘዝም:: ጦርነት ቢታወጅባችሁም በእርግጥ እንረዳችኋለን» ይሏቸዋል:: አላህም እነርሱ ውሸታሞች መሆናቸውን ይመሰክራል::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
لَئِنۡ أُخۡرِجُواْ لَا يَخۡرُجُونَ مَعَهُمۡ وَلَئِن قُوتِلُواْ لَا يَنصُرُونَهُمۡ وَلَئِن نَّصَرُوهُمۡ لَيُوَلُّنَّ ٱلۡأَدۡبَٰرَ ثُمَّ لَا يُنصَرُونَ
12. ቢባረሩም አብረዋቸው አይባረሩም:: ቢገደሉም (ቢወጉም) ቢዘመትባቸዉም አይረዱዋቸዉም:: ቢረዷቸዉም ለሽሽት ጀርባዎችን ያዞራሉ:: ከዚያም እርዳታን አያገኙም::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
لَأَنتُمۡ أَشَدُّ رَهۡبَةٗ فِي صُدُورِهِم مِّنَ ٱللَّهِۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ قَوۡمٞ لَّا يَفۡقَهُونَ
13. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እናንተ በልቦቻቸው ውስጥ በማስፈራራት ከአላህ ይልቅ የበረታችሁ (የከበዳችሁ) ናችሁ:: ይህም የሆነው እነርሱ የማይገነዘቡ ህዝቦች በመሆናቸው ነው::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
لَا يُقَٰتِلُونَكُمۡ جَمِيعًا إِلَّا فِي قُرٗى مُّحَصَّنَةٍ أَوۡ مِن وَرَآءِ جُدُرِۭۚ بَأۡسُهُم بَيۡنَهُمۡ شَدِيدٞۚ تَحۡسَبُهُمۡ جَمِيعٗا وَقُلُوبُهُمۡ شَتَّىٰۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ قَوۡمٞ لَّا يَعۡقِلُونَ
14. በተመሸጉ ከተሞች ውስጥ ወይም ከአጥሮች በስተጀርባ ሆነው እንጂ የተሰበሰቡ ሆነው አይዋጓችሁም:: ኃይላቸው በመካከላቸው ብርቱ ነው:: ልቦቻቸው የተበታተኑ ሲሆን የተሰበሰቡ ናቸው ብለህ ትጠራጠራቸዋለህ (አንድ ይመስሉሃል):: ይህ እነርሱ አእምሮ የሌላቸው ህዝቦች በመሆናቸው ነው::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
كَمَثَلِ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ قَرِيبٗاۖ ذَاقُواْ وَبَالَ أَمۡرِهِمۡ وَلَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ
15. ብጤያቸው ልክ እንደነዚያ ከእነርሱ በፊት በቅርብ ጊዜ የተግባራቸውን ቅጣት እንደቀመሱት ወገኖች ብጤ ነው:: ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
كَمَثَلِ ٱلشَّيۡطَٰنِ إِذۡ قَالَ لِلۡإِنسَٰنِ ٱكۡفُرۡ فَلَمَّا كَفَرَ قَالَ إِنِّي بَرِيٓءٞ مِّنكَ إِنِّيٓ أَخَافُ ٱللَّهَ رَبَّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
16. ምሳሌያቸው ልክ እንደዚያ ሰውን «በአላህ ካድ ብሎ ሰውየው በካደ ጊዜ እኔ ካንተ ንጹህ ነኝ እኔ የዓለማትን ጌታ አላህን እፈራለሁ» እንዳለው ሰይጣን ነው።
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
فَكَانَ عَٰقِبَتَهُمَآ أَنَّهُمَا فِي ٱلنَّارِ خَٰلِدَيۡنِ فِيهَاۚ وَذَٰلِكَ جَزَٰٓؤُاْ ٱلظَّٰلِمِينَ
17. የሁለቱም መጨረሻቸው እነርሱ በውስጡ ዘወታሪዎች ሲሆኑ በእሳት ውስጥ መሆን ነው:: ይህም ቅጣት የበዳዩች ሁሉ ዋጋ ነው::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَلۡتَنظُرۡ نَفۡسٞ مَّا قَدَّمَتۡ لِغَدٖۖ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ خَبِيرُۢ بِمَا تَعۡمَلُونَ
18. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን በትክክል ፍሩ:: ማንኛይቱም ነፍስ ለነገ ያስቀደመችውን ትመልከት፤ አላህን በትክክል ፍሩ:: አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
وَلَا تَكُونُواْ كَٱلَّذِينَ نَسُواْ ٱللَّهَ فَأَنسَىٰهُمۡ أَنفُسَهُمۡۚ أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡفَٰسِقُونَ
19. እንደ እነዚያ አላህን እንደረሱትና ነፍሶቻቸውን እንዳስረሳቸው ሰዎች አትሁኑ:: እነዚያ እነርሱ አመጸኞች ናቸው::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
لَا يَسۡتَوِيٓ أَصۡحَٰبُ ٱلنَّارِ وَأَصۡحَٰبُ ٱلۡجَنَّةِۚ أَصۡحَٰبُ ٱلۡجَنَّةِ هُمُ ٱلۡفَآئِزُونَ
20. የእሳት ጓዶችና የገነት ጓዶች እኩል አይሆኑም:: የገነት ጓዶች ምኞታቸውን አግኝዎች ናቸውና::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
لَوۡ أَنزَلۡنَا هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانَ عَلَىٰ جَبَلٖ لَّرَأَيۡتَهُۥ خَٰشِعٗا مُّتَصَدِّعٗا مِّنۡ خَشۡيَةِ ٱللَّهِۚ وَتِلۡكَ ٱلۡأَمۡثَٰلُ نَضۡرِبُهَا لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمۡ يَتَفَكَّرُونَ
21. (ሙሐመድ ሆይ)፤ ይህንን ቁርኣን በተራራ ላይ ባወረድነው ኖሮ ከአላህ ፍራቻ የተነሳ ተዋራጅና ተሰንጣቂ ሆኖ ባየኸው ነበር:: እነዚህን ምሳሌዎች ለሰዎች ያስተነትኑ ዘንድ እንገልፃቸዋለን::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
هُوَ ٱللَّهُ ٱلَّذِي لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ عَٰلِمُ ٱلۡغَيۡبِ وَٱلشَّهَٰدَةِۖ هُوَ ٱلرَّحۡمَٰنُ ٱلرَّحِيمُ
22. እርሱ ያ አላህ ነው:: ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የሌለ፤ ሩቁንና ቅርቡን አዋቂ የሆነ ነው:: እርሱ እጅግ በጣም ሩህሩህ፤ በጣም አዛኝ ነው::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
هُوَ ٱللَّهُ ٱلَّذِي لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلۡمَلِكُ ٱلۡقُدُّوسُ ٱلسَّلَٰمُ ٱلۡمُؤۡمِنُ ٱلۡمُهَيۡمِنُ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡجَبَّارُ ٱلۡمُتَكَبِّرُۚ سُبۡحَٰنَ ٱللَّهِ عَمَّا يُشۡرِكُونَ
23. እርሱ ያ አላህ ነው:: ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የሌለ፤ ንጉሱ፤ ከጎደሎ ሁሉ የጠራ፤ የሰላም ባለቤት፤ ጸጥታን ሰጪ፤ ባሮቹን ጠባቂ፤ አሸናፊ፤ ኃያልና ኩሩ ነው። አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
هُوَ ٱللَّهُ ٱلۡخَٰلِقُ ٱلۡبَارِئُ ٱلۡمُصَوِّرُۖ لَهُ ٱلۡأَسۡمَآءُ ٱلۡحُسۡنَىٰۚ يُسَبِّحُ لَهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ
24. እርሱ አላህ ፈጣሪዉ፤ ከኢምንት አስገኚዉና ቅርጽን አሳማሪው ነው:: ለእርሱ መልካሞች ስሞች አሉት:: በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ እርሱን ያሞግሳል:: እርሱም ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
 
Übersetzung der Bedeutungen Surah / Kapitel: Al-Ḥaschr
Suren/ Kapiteln Liste Nummer der Seite
 
Übersetzung der Bedeutungen von dem heiligen Quran - Amharische Übersetzung - Akademie Afrika - Übersetzungen

Übersetzt von Muhammad Zain Zaher Al-Din. Herausgegeben von der Afrika-Akademie.

Schließen