Check out the new design

Firo maanaaji al-quraan tedduɗo oo - Eggo Amhariiwo - Akademii Afrik * - Tippudi firooji ɗii

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Firo maanaaji Simoore: Simoore Yuusuf   Aaya:
۞ وَمَآ أُبَرِّئُ نَفۡسِيٓۚ إِنَّ ٱلنَّفۡسَ لَأَمَّارَةُۢ بِٱلسُّوٓءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّيٓۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٞ رَّحِيمٞ
53. «ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም:: ነፍስ ሁሉ ጌታዬ ያዘነላት (የጠበቃት) ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና:: ጌታዬ በጣም መሐሪና አዛኝ ነው።»
Faccirooji aarabeeji:
وَقَالَ ٱلۡمَلِكُ ٱئۡتُونِي بِهِۦٓ أَسۡتَخۡلِصۡهُ لِنَفۡسِيۖ فَلَمَّا كَلَّمَهُۥ قَالَ إِنَّكَ ٱلۡيَوۡمَ لَدَيۡنَا مَكِينٌ أَمِينٞ
54. ንጉሡም «እርሱን አምጡልኝ ለራሴ የግሌ አደርገዋለሁና።» አለ። ባናገረዉም ጊዜ «አንተ ዛሬ እኛ ዘንድ ባለሟልና ታማኝ ነህ።» አለው።
Faccirooji aarabeeji:
قَالَ ٱجۡعَلۡنِي عَلَىٰ خَزَآئِنِ ٱلۡأَرۡضِۖ إِنِّي حَفِيظٌ عَلِيمٞ
55. «በምድር ግምጃ ቤቶች ላይ ሹም አድርገኝ እኔ ጠባቂ አዋቂ ነኝና።» አለ።
Faccirooji aarabeeji:
وَكَذَٰلِكَ مَكَّنَّا لِيُوسُفَ فِي ٱلۡأَرۡضِ يَتَبَوَّأُ مِنۡهَا حَيۡثُ يَشَآءُۚ نُصِيبُ بِرَحۡمَتِنَا مَن نَّشَآءُۖ وَلَا نُضِيعُ أَجۡرَ ٱلۡمُحۡسِنِينَ
56. እንደዚሁም ለዩሱፍ በምድር ላይ ከእርሷ በፈለገው ስፍራ የሚሰፍር ሲሆን አስመቸነው:: በችሮታችን የምንሻውን ሰው እንለያለን። የበጎ ሠሪዎችንም ዋጋ አናጠፋም።
Faccirooji aarabeeji:
وَلَأَجۡرُ ٱلۡأٓخِرَةِ خَيۡرٞ لِّلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَكَانُواْ يَتَّقُونَ
57. የመጨረሻይቱም ዓለም ምንዳ ለእነዚያ ላመኑትና ይጠነቀቁ ለነበሩት የበለጠ ነው::
Faccirooji aarabeeji:
وَجَآءَ إِخۡوَةُ يُوسُفَ فَدَخَلُواْ عَلَيۡهِ فَعَرَفَهُمۡ وَهُمۡ لَهُۥ مُنكِرُونَ
58. የዩሱፍ ወንድሞችም መጡ በእርሱም ላይ ገቡ:: እነርሱም እርሱን የሳቱት ሲሆኑ አወቃቸው::
Faccirooji aarabeeji:
وَلَمَّا جَهَّزَهُم بِجَهَازِهِمۡ قَالَ ٱئۡتُونِي بِأَخٖ لَّكُم مِّنۡ أَبِيكُمۡۚ أَلَا تَرَوۡنَ أَنِّيٓ أُوفِي ٱلۡكَيۡلَ وَأَنَا۠ خَيۡرُ ٱلۡمُنزِلِينَ
59. ጉዳያቸውን ፈጽሞ ስንቃቸውንም ባዘጋጀላቸው ጊዜ አለ: «ከአባታችሁ በኩል የሆነውን ወንድማችሁን አምጡልኝ እኔ ከአስተናጋጆች ሁሉ በላጭ ስሆን ስፍርን የምሞላ መሆኔን አታዩምን?
Faccirooji aarabeeji:
فَإِن لَّمۡ تَأۡتُونِي بِهِۦ فَلَا كَيۡلَ لَكُمۡ عِندِي وَلَا تَقۡرَبُونِ
60. «እርሱንም ባታመጡልኝ። እኔ ዘንድ ለእናንተ ስፍር የላችሁም:: አትቀርቡኝምም።» አለ
Faccirooji aarabeeji:
قَالُواْ سَنُرَٰوِدُ عَنۡهُ أَبَاهُ وَإِنَّا لَفَٰعِلُونَ
61. «ስለ እርሱ አባቱን በጥብቅ እንጠይቃለን፤ እኛም ይህንን በእርግጥ ሰሪዎች ነን።» አሉት።
Faccirooji aarabeeji:
وَقَالَ لِفِتۡيَٰنِهِ ٱجۡعَلُواْ بِضَٰعَتَهُمۡ فِي رِحَالِهِمۡ لَعَلَّهُمۡ يَعۡرِفُونَهَآ إِذَا ٱنقَلَبُوٓاْ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِمۡ لَعَلَّهُمۡ يَرۡجِعُونَ
62. ለአሽከሮቹም፡- «ወደ ቤተሰቦቻቸው በተመለሱ ጊዜ ሸቀጣቸውን (ገንዘባቸውን) ያውቋት ዘንድ በየጓዞቻቸው ውስጥ አድርጉላቸው ሊመለሱ ይከጀላልና።» አላቸው።
Faccirooji aarabeeji:
فَلَمَّا رَجَعُوٓاْ إِلَىٰٓ أَبِيهِمۡ قَالُواْ يَٰٓأَبَانَا مُنِعَ مِنَّا ٱلۡكَيۡلُ فَأَرۡسِلۡ مَعَنَآ أَخَانَا نَكۡتَلۡ وَإِنَّا لَهُۥ لَحَٰفِظُونَ
63. ወደ አባታቸዉም በተመለሱ ጊዜ፡- «አባታችን ሆይ! (ወንድማችንን እስከምንወስድ) ስፍር ከኛ ተከልክሏል። ስለዚህ ወንድማችንን ከእኛ ጋር ላከው፤ ይሰፈርልናልና እኛም ለእርሱ ጠባቂዎች ነን።» አሉ::
Faccirooji aarabeeji:
 
Firo maanaaji Simoore: Simoore Yuusuf
Tippudi cimooje Tonngoode hello ngoo
 
Firo maanaaji al-quraan tedduɗo oo - Eggo Amhariiwo - Akademii Afrik - Tippudi firooji ɗii

Eggo mum - Muhammad Zain Zahr al-Din. E haala Akademii Afrik.

Uddude