Check out the new design

Firo maanaaji al-quraan tedduɗo oo - Eggo Amhariiwo - Akademii Afrik * - Tippudi firooji ɗii

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Firo maanaaji Simoore: Simoore hajju   Aaya:
أُذِنَ لِلَّذِينَ يُقَٰتَلُونَ بِأَنَّهُمۡ ظُلِمُواْۚ وَإِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ نَصۡرِهِمۡ لَقَدِيرٌ
39. ለእነዚያ በከሓዲያን ለሚገደሉት ትክክለኛ አማኞች የተበደሉ በመሆናቸው መጋደል ተፈቀደላቸው:: አላህ እነርሱን በመርዳት ላይ በእርግጥ ቻይ ነውና::
Faccirooji aarabeeji:
ٱلَّذِينَ أُخۡرِجُواْ مِن دِيَٰرِهِم بِغَيۡرِ حَقٍّ إِلَّآ أَن يَقُولُواْ رَبُّنَا ٱللَّهُۗ وَلَوۡلَا دَفۡعُ ٱللَّهِ ٱلنَّاسَ بَعۡضَهُم بِبَعۡضٖ لَّهُدِّمَتۡ صَوَٰمِعُ وَبِيَعٞ وَصَلَوَٰتٞ وَمَسَٰجِدُ يُذۡكَرُ فِيهَا ٱسۡمُ ٱللَّهِ كَثِيرٗاۗ وَلَيَنصُرَنَّ ٱللَّهُ مَن يَنصُرُهُۥٓۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَقَوِيٌّ عَزِيزٌ
40. ለእነዚያ «ጌታችን አላህ ነው።» ከማለታቸው በስተቀር ያለ አግባብ ከየቀያቸው የተባረሩ ለሆኑት ከራሳቸው ላይ መከላከል ተፈቀደ:: አላህ ሰዎችን ከፊላቸውን በከፊሉ መገፍተሩ ባልነበረ ኖሮ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችም፣ ምኩራቦችና በውስጣቸው የአላህ ስም በብዛት የሚወሳባቸው መስጊዶችም በተፈረሱ ነበር:: አላህም ሃይማኖቱን የሚረዳውን ሁሉ በእርግጥ ይረዳዋል:: አላህ ብርቱና ሁሉን አሸናፊ ነውና::
Faccirooji aarabeeji:
ٱلَّذِينَ إِن مَّكَّنَّٰهُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ أَقَامُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتَوُاْ ٱلزَّكَوٰةَ وَأَمَرُواْ بِٱلۡمَعۡرُوفِ وَنَهَوۡاْ عَنِ ٱلۡمُنكَرِۗ وَلِلَّهِ عَٰقِبَةُ ٱلۡأُمُورِ
41. እነርሱ ማለት እነዚያ በምድር ላይ ብናስመቻቸው (የበላይነትን ሰጥተን ባጎናጸፍናቸው ኖሮ) ሶላትን እንደሚገባ የሚያስተካክሉ፤ ዘካንም የሚሰጡ፤ በደግ ነገርም የሚያዝዙ፤ ከመጥፎ ነገርም የሚከለከሉ ናቸው:: የነገሮች ሁሉ መጨረሻ ወደ አላህ ብቻ ነው::
Faccirooji aarabeeji:
وَإِن يُكَذِّبُوكَ فَقَدۡ كَذَّبَتۡ قَبۡلَهُمۡ قَوۡمُ نُوحٖ وَعَادٞ وَثَمُودُ
42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢያስተባብሉህም ከእነርሱ በፊት የኑሕ ህዝቦች፣ የዓድና የሰሙድም በእርግጥ አስተባብለዋል።
Faccirooji aarabeeji:
وَقَوۡمُ إِبۡرَٰهِيمَ وَقَوۡمُ لُوطٖ
43. የኢብራሂምም ህዝቦች የሉጥም ህዝቦች እንደዚሁ አስተባብለዋል፤
Faccirooji aarabeeji:
وَأَصۡحَٰبُ مَدۡيَنَۖ وَكُذِّبَ مُوسَىٰۖ فَأَمۡلَيۡتُ لِلۡكَٰفِرِينَ ثُمَّ أَخَذۡتُهُمۡۖ فَكَيۡفَ كَانَ نَكِيرِ
44. የመድየንም ሰዎች እንዲሁ አስተባብለዋል:: ሙሳም ተስተባብሏል:: ለከሓዲያንም ጊዜን ሰጠኋቸው:: ከዚያ ያዝኳቸው። ጥላቻዬም እንዴት ነበረ (ተመልከቱ)።
Faccirooji aarabeeji:
فَكَأَيِّن مِّن قَرۡيَةٍ أَهۡلَكۡنَٰهَا وَهِيَ ظَالِمَةٞ فَهِيَ خَاوِيَةٌ عَلَىٰ عُرُوشِهَا وَبِئۡرٖ مُّعَطَّلَةٖ وَقَصۡرٖ مَّشِيدٍ
45. ከከተሞች መካከል በደለኛ ሆነው ያጠፋናቸው እና በጣሪያዎቻቸው ላይ ወዳቂ የሆኑ ብዙ ናቸው:: ከተራቆተም የውሃ ጉድጓድ ከተገነባም ህንፃ ያጠፋነው ብዙ ነው::
Faccirooji aarabeeji:
أَفَلَمۡ يَسِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَتَكُونَ لَهُمۡ قُلُوبٞ يَعۡقِلُونَ بِهَآ أَوۡ ءَاذَانٞ يَسۡمَعُونَ بِهَاۖ فَإِنَّهَا لَا تَعۡمَى ٱلۡأَبۡصَٰرُ وَلَٰكِن تَعۡمَى ٱلۡقُلُوبُ ٱلَّتِي فِي ٱلصُّدُورِ
46. ለእነርሱም የሚያውቁባቸው ልቦች፤ ወይም የሚሰሙባቸው ጆሮዎች ይኖሯቸው ዘንድ በምድር ላይ አይሄዱምን? እነሆ ዓይኖች አይታወሩም:: እነዚያ በደረቶች ውስጥ ያሉት ልቦች ናቸው የሚታወሩት።
Faccirooji aarabeeji:
 
Firo maanaaji Simoore: Simoore hajju
Tippudi cimooje Tonngoode hello ngoo
 
Firo maanaaji al-quraan tedduɗo oo - Eggo Amhariiwo - Akademii Afrik - Tippudi firooji ɗii

Eggo mum - Muhammad Zain Zahr al-Din. E haala Akademii Afrik.

Uddude