Check out the new design

Firo maanaaji al-quraan tedduɗo oo - Eggo Amhariiwo - Akademii Afrik * - Tippudi firooji ɗii


Firo maanaaji Simoore: Simoore annoore   Aaya:
قُلۡ أَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُواْ ٱلرَّسُولَۖ فَإِن تَوَلَّوۡاْ فَإِنَّمَا عَلَيۡهِ مَا حُمِّلَ وَعَلَيۡكُم مَّا حُمِّلۡتُمۡۖ وَإِن تُطِيعُوهُ تَهۡتَدُواْۚ وَمَا عَلَى ٱلرَّسُولِ إِلَّا ٱلۡبَلَٰغُ ٱلۡمُبِينُ
54. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ሙስሊሞች ሆይ!) «አላህንና መልዕክተኛውንም ታዘዙ:: ብትሸሹም አትጎዱትም:: በእርሱ ላይ ያለበት የተገደደውን ማድረስ ብቻ ነው:: በእናንተም ላይ ያለባችሁ የተገደዳችሁትን መታዘዝ ብቻ ነው:: ብትታዘዙትም ወደ ቀናው መንገድ ትመራላችሁ በመልዕክተኛው ላይ ግልጽ ማድረስ እንጂ ሌላ የለበትምና።» በላቸው።
Faccirooji aarabeeji:
وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مِنكُمۡ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَيَسۡتَخۡلِفَنَّهُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ كَمَا ٱسۡتَخۡلَفَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ وَلَيُمَكِّنَنَّ لَهُمۡ دِينَهُمُ ٱلَّذِي ٱرۡتَضَىٰ لَهُمۡ وَلَيُبَدِّلَنَّهُم مِّنۢ بَعۡدِ خَوۡفِهِمۡ أَمۡنٗاۚ يَعۡبُدُونَنِي لَا يُشۡرِكُونَ بِي شَيۡـٔٗاۚ وَمَن كَفَرَ بَعۡدَ ذَٰلِكَ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡفَٰسِقُونَ
55. አላህ እነዚያን ከናንተ መካከል በትክክል ያመኑትንና መልካም ስራዎችን የሰሩትን እነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን እንደተካቸው ሁሉ በምድር ላይ በእርግጥ ሊተካቸው፤ ለእነርሱም ያንን የወደደላቸውን ሃይማኖታቸውን ሊያደላድልላቸው፤ ከፍርሃታቸዉም በኋላ ደህናነትን ሊለውጥላቸው የተስፋን ቃል ሰጥቷቸዋል:: በእኔ ምንንም የማያጋሩ ሆነው ሊገዙኝ ነው፤ ከዚያም በኋላ በሱ የካዱ ሰዎች እነዚያ አመጸኞች ማለት እነርሱ ብቻ ናቸው::
Faccirooji aarabeeji:
وَأَقِيمُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتُواْ ٱلزَّكَوٰةَ وَأَطِيعُواْ ٱلرَّسُولَ لَعَلَّكُمۡ تُرۡحَمُونَ
56. (ሙስሊሞች ሆይ!) ይታዘንላችሁ ዘንድ ሶላትን አስተካክላችሁ ስገዱ፣ ምጽዋትንም ስጡ፣ መልዕክተኛውንም ታዘዙ።
Faccirooji aarabeeji:
لَا تَحۡسَبَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مُعۡجِزِينَ فِي ٱلۡأَرۡضِۚ وَمَأۡوَىٰهُمُ ٱلنَّارُۖ وَلَبِئۡسَ ٱلۡمَصِيرُ
57. እነዚያን በአላህ የካዱትን በምድር ውስጥ የሚያቅቱ አድርገህ አታስብ፤ መኖሪያቸውም እሳት ናት:: ገሀነም በእርግጥም ምንኛ ትከፋ።
Faccirooji aarabeeji:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لِيَسۡتَـٔۡذِنكُمُ ٱلَّذِينَ مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُكُمۡ وَٱلَّذِينَ لَمۡ يَبۡلُغُواْ ٱلۡحُلُمَ مِنكُمۡ ثَلَٰثَ مَرَّٰتٖۚ مِّن قَبۡلِ صَلَوٰةِ ٱلۡفَجۡرِ وَحِينَ تَضَعُونَ ثِيَابَكُم مِّنَ ٱلظَّهِيرَةِ وَمِنۢ بَعۡدِ صَلَوٰةِ ٱلۡعِشَآءِۚ ثَلَٰثُ عَوۡرَٰتٖ لَّكُمۡۚ لَيۡسَ عَلَيۡكُمۡ وَلَا عَلَيۡهِمۡ جُنَاحُۢ بَعۡدَهُنَّۚ طَوَّٰفُونَ عَلَيۡكُم بَعۡضُكُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖۚ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمُ ٱلۡأٓيَٰتِۗ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٞ
58. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያ እጆቻችሁ የጨበጧቸው ባሮች እነዚያም ከናንተ መካከል ለአካለ መጠን ያልደረሱት (ህፃናት) በሶስት ጊዜ: ከጎህ ስግደት በፊት፤ በቀትር ልብሶቻችሁን በምታወልቁበት ጊዜና ከምሽት ስግደትም በኋላ ወደ እናንተ ለመግባት ሲፈልጉ ያስፈቅዷችሁ:: እነዚህ የእናንተ ሶስት የሐፍረተ ገላ መግለጫ ጊዜያቶች ናቸውና:: ከእነዚህ በኋላ ግን በእናንተም ሆነ በነሱ ላይ (ያለፈቃድ በመግባት) ኃጢአት የለም:: እናንተን ለማገልገል በዙሪያችሁ ዟሪዎች ናቸውና:: ከፊላችሁ በከፊሉ ላይ ዟሪ ነውና፤ ልክ እንደዚሁ አላህ ለእናንተ ህግጋቱን ይገልጽላችኋል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና::
Faccirooji aarabeeji:
 
Firo maanaaji Simoore: Simoore annoore
Tippudi cimooje Tonngoode hello ngoo
 
Firo maanaaji al-quraan tedduɗo oo - Eggo Amhariiwo - Akademii Afrik - Tippudi firooji ɗii

Eggo mum - Muhammad Zain Zahr al-Din. E haala Akademii Afrik.

Uddude