Check out the new design

Firo maanaaji al-quraan tedduɗo oo - Eggo Amhariiwo - Akademii Afrik * - Tippudi firooji ɗii

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Firo maanaaji Simoore: Simoore Lukmaan   Aaya:
أَلَمۡ تَرَوۡاْ أَنَّ ٱللَّهَ سَخَّرَ لَكُم مَّا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ وَأَسۡبَغَ عَلَيۡكُمۡ نِعَمَهُۥ ظَٰهِرَةٗ وَبَاطِنَةٗۗ وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يُجَٰدِلُ فِي ٱللَّهِ بِغَيۡرِ عِلۡمٖ وَلَا هُدٗى وَلَا كِتَٰبٖ مُّنِيرٖ
20. (ሰዎች ሆይ!) አላህ በሰማያት እና በምድር ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ ለእናንተ ያገራላችሁ፤ ጸጋዎችንም ግልጽም ይሁኑ ድብቅ የሞላላችሁ መሆኑን አታዩምን? ከስሞች መካከል ያለ በቂ እውቀትና ያለ መሪ፤ ያለ ግልጽ መጽሀፍም፤ ስለ አላህ የሚከራከር አለ::
Faccirooji aarabeeji:
وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ٱتَّبِعُواْ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ قَالُواْ بَلۡ نَتَّبِعُ مَا وَجَدۡنَا عَلَيۡهِ ءَابَآءَنَآۚ أَوَلَوۡ كَانَ ٱلشَّيۡطَٰنُ يَدۡعُوهُمۡ إِلَىٰ عَذَابِ ٱلسَّعِيرِ
21. ለእነርሱም «አላህ ያወረደውን ተከተሉ።» በተባሉ ጊዜ «አይደለም በእርሱ ላይ አባቶቻችንን ያገኘንበትን እንከተላለን።» ይላሉ:: ሰይጣን (ይህን ተግባር በማስዋብ) ወደ እሳት ቅጣት የሚጠራቸው ቢሆንም ይከተሏቸዋልን?
Faccirooji aarabeeji:
۞ وَمَن يُسۡلِمۡ وَجۡهَهُۥٓ إِلَى ٱللَّهِ وَهُوَ مُحۡسِنٞ فَقَدِ ٱسۡتَمۡسَكَ بِٱلۡعُرۡوَةِ ٱلۡوُثۡقَىٰۗ وَإِلَى ٱللَّهِ عَٰقِبَةُ ٱلۡأُمُورِ
22. መልካም ሰሪ ሆኖ ፊቱን ወደ አላህ የሚሰጥ ሁሉ ጠንካራ ገመድን በእርግጥ ጨበጠ:: የነገሩ ሁሉ ፍጻሜ ወደ አላህ ብቻ ነው::
Faccirooji aarabeeji:
وَمَن كَفَرَ فَلَا يَحۡزُنكَ كُفۡرُهُۥٓۚ إِلَيۡنَا مَرۡجِعُهُمۡ فَنُنَبِّئُهُم بِمَا عَمِلُوٓاْۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ
23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ የካደም ሁሉ ክህደቱ አያሳዝንህ። መመለሻቸው ወደ እኛ ብቻ ነውና:: ከዚያም የሰሩትንም ሁሉ እንነግራቸዋለን:: አላህ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ ያውቃልና፡፡
Faccirooji aarabeeji:
نُمَتِّعُهُمۡ قَلِيلٗا ثُمَّ نَضۡطَرُّهُمۡ إِلَىٰ عَذَابٍ غَلِيظٖ
24. ጥቂትን ጊዜ እናጣቅማቸዋለን:: ከዚያም ወደ ብርቱ ቅጣት እናስገድዳቸዋለን::
Faccirooji aarabeeji:
وَلَئِن سَأَلۡتَهُم مَّنۡ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ لَيَقُولُنَّ ٱللَّهُۚ قُلِ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِۚ بَلۡ أَكۡثَرُهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ
25. ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው «በእርግጥ አላህ ነው።» ይላሉ። «ምስጋና ሁሉ ለአላህ ብቻ ይገባው።» በላቸው:: ይልቁንም አብዛኞቹ አያውቁም።
Faccirooji aarabeeji:
لِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلۡغَنِيُّ ٱلۡحَمِيدُ
26. በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: አላህ በራሱ ተብቃቂዉና ምስጉኑ ነው::
Faccirooji aarabeeji:
وَلَوۡ أَنَّمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ مِن شَجَرَةٍ أَقۡلَٰمٞ وَٱلۡبَحۡرُ يَمُدُّهُۥ مِنۢ بَعۡدِهِۦ سَبۡعَةُ أَبۡحُرٖ مَّا نَفِدَتۡ كَلِمَٰتُ ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٞ
27. በምድር ያሉ ሁሉ ዛፎች ብዕሮች ቢሆኑ ኖሮ ባህሩም ከእርሱ ማለቅ በኋላ ሰባት ባህሮች የሚጨመሩለት ሆኖ ቀለም ቢሆንና ቢጻፍባቸው የአላህ ቃላት ባላለቀች ነበር:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::
Faccirooji aarabeeji:
مَّا خَلۡقُكُمۡ وَلَا بَعۡثُكُمۡ إِلَّا كَنَفۡسٖ وَٰحِدَةٍۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعُۢ بَصِيرٌ
28. (ሰዎች ሆይ!) እናንተን መፍጠርና እናንተን መቀስቀስ እንደ አንዲት ነፍስ እንጂ ሌላ አይደለም:: አላህ ሁሉን ሰሚና ሁሉን ተመልካች ነውና::
Faccirooji aarabeeji:
 
Firo maanaaji Simoore: Simoore Lukmaan
Tippudi cimooje Tonngoode hello ngoo
 
Firo maanaaji al-quraan tedduɗo oo - Eggo Amhariiwo - Akademii Afrik - Tippudi firooji ɗii

Eggo mum - Muhammad Zain Zahr al-Din. E haala Akademii Afrik.

Uddude