Check out the new design

Firo maanaaji al-quraan tedduɗo oo - Eggo Amhariiwo - Akademii Afrik * - Tippudi firooji ɗii


Firo maanaaji Simoore: Simoore faatir   Aaya:
وَمَا يَسۡتَوِي ٱلۡأَعۡمَىٰ وَٱلۡبَصِيرُ
19. እውርና የሚያይ አይሰተካከሉም፤
Faccirooji aarabeeji:
وَلَا ٱلظُّلُمَٰتُ وَلَا ٱلنُّورُ
20. ጨለማዎችና ብርሃንም፤
Faccirooji aarabeeji:
وَلَا ٱلظِّلُّ وَلَا ٱلۡحَرُورُ
21. ጥላና ሐሩርም።
Faccirooji aarabeeji:
وَمَا يَسۡتَوِي ٱلۡأَحۡيَآءُ وَلَا ٱلۡأَمۡوَٰتُۚ إِنَّ ٱللَّهَ يُسۡمِعُ مَن يَشَآءُۖ وَمَآ أَنتَ بِمُسۡمِعٖ مَّن فِي ٱلۡقُبُورِ
22. ህያውና ሙታንም አይስተካከሉም:: አላህ የሚሻውን ሰው ያሰማል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ግን በመቃብር ውስጥ ያሉትን አሰሚ አይደለህም::
Faccirooji aarabeeji:
إِنۡ أَنتَ إِلَّا نَذِيرٌ
23. አንተ አስጠንቃቂ እንጂ ሌላ አይደለህም::
Faccirooji aarabeeji:
إِنَّآ أَرۡسَلۡنَٰكَ بِٱلۡحَقِّ بَشِيرٗا وَنَذِيرٗاۚ وَإِن مِّنۡ أُمَّةٍ إِلَّا خَلَا فِيهَا نَذِيرٞ
24. እኛ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን በእውነቱ መምሪያ ላክንህ:: ማንኛይቱም ህዝብ በውስጧ አስፈራሪ ያላለፈባት የለችም::
Faccirooji aarabeeji:
وَإِن يُكَذِّبُوكَ فَقَدۡ كَذَّبَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ جَآءَتۡهُمۡ رُسُلُهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِ وَبِٱلزُّبُرِ وَبِٱلۡكِتَٰبِ ٱلۡمُنِيرِ
25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢያስተባብሉህም ከእነዚህ ከበፊታቸው የነበሩትም ህዝቦች በእርግጥ ነብያትን አስተባብለዋል:: መልዕክተኞቻቸው በግልጽ ማስረጃዎች፣ በጹሁፎችም አብራሪ በሆነ መጽሐፍም መጥተዋቸዋል::
Faccirooji aarabeeji:
ثُمَّ أَخَذۡتُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْۖ فَكَيۡفَ كَانَ نَكِيرِ
26. ከዚያም እነዚያን የካዱትን ቀጣኋቸው:: ቅጣቴም እንዴት ነበር! (በስፍራው ነው ተገቢ ነው)።
Faccirooji aarabeeji:
أَلَمۡ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَأَخۡرَجۡنَا بِهِۦ ثَمَرَٰتٖ مُّخۡتَلِفًا أَلۡوَٰنُهَاۚ وَمِنَ ٱلۡجِبَالِ جُدَدُۢ بِيضٞ وَحُمۡرٞ مُّخۡتَلِفٌ أَلۡوَٰنُهَا وَغَرَابِيبُ سُودٞ
27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ከሰማይ ውሃን ማውረዱን አላየህምን? በእርሱም ዓይነቶቻቸው የተለያዩ ፍሬዎችን አወጣን:: ከጋራዎችም መልካቸው የተለያዩ ነጮችም፤ ቀዮችም፤ በጣም ጥቁሮችም የሆኑ መንገዶች አሉ።
Faccirooji aarabeeji:
وَمِنَ ٱلنَّاسِ وَٱلدَّوَآبِّ وَٱلۡأَنۡعَٰمِ مُخۡتَلِفٌ أَلۡوَٰنُهُۥ كَذَٰلِكَۗ إِنَّمَا يَخۡشَى ٱللَّهَ مِنۡ عِبَادِهِ ٱلۡعُلَمَٰٓؤُاْۗ إِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ غَفُورٌ
28. ከሰዎችም፤ ከተንቀሳቃሾችም፤ ከቤት እንስሳዎችም እንደዚሁ መልኮቻቸው የተለያዩ አሉ:: አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት አዋቂዎቹ ብቻ ናቸው:: አላህ አሸናፊና መሃሪ ነው::
Faccirooji aarabeeji:
إِنَّ ٱلَّذِينَ يَتۡلُونَ كِتَٰبَ ٱللَّهِ وَأَقَامُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَأَنفَقُواْ مِمَّا رَزَقۡنَٰهُمۡ سِرّٗا وَعَلَانِيَةٗ يَرۡجُونَ تِجَٰرَةٗ لَّن تَبُورَ
29. እነዚያ የአላህን መጽሐፍ የሚያነቡ፣ ሶላትን አስተካክለው የሰገዱ፤ ከሰጠናቸዉም ሲሳይ በምስጢርም ሆነ በግልጽ የለገሱ የማትከስርን ንግድ ተስፋ ያደርጋሉ::
Faccirooji aarabeeji:
لِيُوَفِّيَهُمۡ أُجُورَهُمۡ وَيَزِيدَهُم مِّن فَضۡلِهِۦٓۚ إِنَّهُۥ غَفُورٞ شَكُورٞ
30. ምንዳዎቻቸውን ሊሞላላቸው ከችሮታዉም ሊጨምርላቸው ተስፋ ያደርጋሉ:: እርሱ በጣም መሃሪና አመስጋኝ ነውና::
Faccirooji aarabeeji:
 
Firo maanaaji Simoore: Simoore faatir
Tippudi cimooje Tonngoode hello ngoo
 
Firo maanaaji al-quraan tedduɗo oo - Eggo Amhariiwo - Akademii Afrik - Tippudi firooji ɗii

Eggo mum - Muhammad Zain Zahr al-Din. E haala Akademii Afrik.

Uddude