Check out the new design

Firo maanaaji al-quraan tedduɗo oo - Eggo Amhariiwo - Akademii Afrik * - Tippudi firooji ɗii


Firo maanaaji Simoore: Simoore Gaafir   Aaya:
وَقَالَ فِرۡعَوۡنُ ذَرُونِيٓ أَقۡتُلۡ مُوسَىٰ وَلۡيَدۡعُ رَبَّهُۥٓۖ إِنِّيٓ أَخَافُ أَن يُبَدِّلَ دِينَكُمۡ أَوۡ أَن يُظۡهِرَ فِي ٱلۡأَرۡضِ ٱلۡفَسَادَ
26. ፈርዖንም «ተዉኝ፤ ሙሳን ልግደል:: (ያድነው እንደሆነም) ጌታውን ይጥራ:: እኔ ሃይማኖታችሁን ሊለውጥ ወይም በምድር ውስጥ ጥፋትን ሊያሰራጭ እፈራለሁና።» አለ::
Faccirooji aarabeeji:
وَقَالَ مُوسَىٰٓ إِنِّي عُذۡتُ بِرَبِّي وَرَبِّكُم مِّن كُلِّ مُتَكَبِّرٖ لَّا يُؤۡمِنُ بِيَوۡمِ ٱلۡحِسَابِ
27. ሙሳም «እኔ በምርመራው ቀን ከማያምን ትዕቢተኛ ሁሉ በጌታየና በጌታችሁ ተጠበቅሁ።» አለ::
Faccirooji aarabeeji:
وَقَالَ رَجُلٞ مُّؤۡمِنٞ مِّنۡ ءَالِ فِرۡعَوۡنَ يَكۡتُمُ إِيمَٰنَهُۥٓ أَتَقۡتُلُونَ رَجُلًا أَن يَقُولَ رَبِّيَ ٱللَّهُ وَقَدۡ جَآءَكُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِ مِن رَّبِّكُمۡۖ وَإِن يَكُ كَٰذِبٗا فَعَلَيۡهِ كَذِبُهُۥۖ وَإِن يَكُ صَادِقٗا يُصِبۡكُم بَعۡضُ ٱلَّذِي يَعِدُكُمۡۖ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي مَنۡ هُوَ مُسۡرِفٞ كَذَّابٞ
28. ከፈርዖን ቤተሰቦች አንድ እምነቱን የሚደብቅ ምዕመን ሰውም አለ: «ሰውዬው ከጌታችሁ በታዐምራቶች በእርግጥ የመጣላችሁ ሲሆን 'ጌታየ አላህ ነው' ስለሚል ትገድሉታላችሁን? ውሸታምም ቢሆን ውሸቱ በእርሱ ላይ ነው:: እውነተኛ ቢሆን ግን የእዚያ የሚያስፈራራችሁ ከፊሉ ያገኛችኋል:: አላህ እርሱ ያንን ድንበር አላፊና ውሸታም የሆነውን አይመራምና።
Faccirooji aarabeeji:
يَٰقَوۡمِ لَكُمُ ٱلۡمُلۡكُ ٱلۡيَوۡمَ ظَٰهِرِينَ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَمَن يَنصُرُنَا مِنۢ بَأۡسِ ٱللَّهِ إِن جَآءَنَاۚ قَالَ فِرۡعَوۡنُ مَآ أُرِيكُمۡ إِلَّا مَآ أَرَىٰ وَمَآ أَهۡدِيكُمۡ إِلَّا سَبِيلَ ٱلرَّشَادِ
29. «ወገኖቼ ሆይ! በምድር ላይ አሸናፊዎች ስትሆኑ ዛሬ መንግስትነት የእናንተ ነው:: ታዲያ ከአላህ ቅጣት ቢመጣብን የሚያድነን ማን ነው?» አለ:: ፈርዖንም «የማየውን እንጂ አላመላክታችሁም፤ ቅኑን መንገድ እንጂ አልመራችሁም።» አላቸው።
Faccirooji aarabeeji:
وَقَالَ ٱلَّذِيٓ ءَامَنَ يَٰقَوۡمِ إِنِّيٓ أَخَافُ عَلَيۡكُم مِّثۡلَ يَوۡمِ ٱلۡأَحۡزَابِ
30. ያ ያመነው ሰውም አለ፡- «እኔ በእናንተ ላይ የአህዛብን ቀን ብጤ እፈራላችኋለሁ።
Faccirooji aarabeeji:
مِثۡلَ دَأۡبِ قَوۡمِ نُوحٖ وَعَادٖ وَثَمُودَ وَٱلَّذِينَ مِنۢ بَعۡدِهِمۡۚ وَمَا ٱللَّهُ يُرِيدُ ظُلۡمٗا لِّلۡعِبَادِ
31. «የ(ነብዩ) ኑህን ህዝቦች የዓድንና የሰሙድም የእነዚያን ከኋላቸው የነበሩትንም ህዝቦች ልማድ ብጤ እፈራላችኋለሁ:: አላህም ለባሮቹ መበደል የሚሻ ጌታ (ሆኖ) አይደለም::
Faccirooji aarabeeji:
وَيَٰقَوۡمِ إِنِّيٓ أَخَافُ عَلَيۡكُمۡ يَوۡمَ ٱلتَّنَادِ
32. «ወገኖቼ ሆይ! እኔ በእናንተ ላይ የመጠራሪያን ቀን እፈራለሁ::»
Faccirooji aarabeeji:
يَوۡمَ تُوَلُّونَ مُدۡبِرِينَ مَا لَكُم مِّنَ ٱللَّهِ مِنۡ عَاصِمٖۗ وَمَن يُضۡلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِنۡ هَادٖ
33. ወደ ኋላ ዞራችሁ በምትሸሹበት ቀን፤ ለእናንተ ከአላህ ቅጣት ምንም ጠባቂ የላችሁም፤ አላህም የሚያጠመው ሰው ለእርሱ ምንም አቅኚ የለዉም::
Faccirooji aarabeeji:
 
Firo maanaaji Simoore: Simoore Gaafir
Tippudi cimooje Tonngoode hello ngoo
 
Firo maanaaji al-quraan tedduɗo oo - Eggo Amhariiwo - Akademii Afrik - Tippudi firooji ɗii

Eggo mum - Muhammad Zain Zahr al-Din. E haala Akademii Afrik.

Uddude