Check out the new design

Fassarar Ma'anonin Alqura'ni - Fassarar Amhariyanci - Akadamar Afirka * - Teburin Bayani kan wasu Fassarori


Fassarar Ma'anoni Sura: Al'zukhruf   Aya:
وَإِنَّهُۥ لَعِلۡمٞ لِّلسَّاعَةِ فَلَا تَمۡتَرُنَّ بِهَا وَٱتَّبِعُونِۚ هَٰذَا صِرَٰطٞ مُّسۡتَقِيمٞ
61. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እርሱም (ዒሳ) ለስዓቲቱ ማወቂያ በእርግጥ ምልክት ነው:: በእርሷም አትጠራጠሩ:: ተከተሉኝም:: ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» በላቸው::
Tafsiran larabci:
وَلَا يَصُدَّنَّكُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُۖ إِنَّهُۥ لَكُمۡ عَدُوّٞ مُّبِينٞ
62. ሰይጣንም አያግዳችሁ:: እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና::
Tafsiran larabci:
وَلَمَّا جَآءَ عِيسَىٰ بِٱلۡبَيِّنَٰتِ قَالَ قَدۡ جِئۡتُكُم بِٱلۡحِكۡمَةِ وَلِأُبَيِّنَ لَكُم بَعۡضَ ٱلَّذِي تَخۡتَلِفُونَ فِيهِۖ فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ
63. ዒሳ ግልፅ ተዓምራታችንን ይዞ በመጣ ጊዜ «በእርግጥ በጥበብ መጣሁላችሁ:: የዚያንም የምትለያዩበትን ጉዳይ ከፊሉን ለእናንተ ላብራራላችሁ መጣሁ:: እናም አላህን ፍሩ:: ታዘዙኝም::
Tafsiran larabci:
إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ رَبِّي وَرَبُّكُمۡ فَٱعۡبُدُوهُۚ هَٰذَا صِرَٰطٞ مُّسۡتَقِيمٞ
64. «አላህ ጌታዬ ጌታችሁም ነውና በብቸኝነት ተገዙት:: ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው::» አለ።
Tafsiran larabci:
فَٱخۡتَلَفَ ٱلۡأَحۡزَابُ مِنۢ بَيۡنِهِمۡۖ فَوَيۡلٞ لِّلَّذِينَ ظَلَمُواْ مِنۡ عَذَابِ يَوۡمٍ أَلِيمٍ
65. ከመካከላቸዉም አህዛቦቹ ተለያዩ:: ለእነዚያም ለበደሉት ህዝቦች ከአሳማሚ ቀን ቅጣት ወዮላቸው::
Tafsiran larabci:
هَلۡ يَنظُرُونَ إِلَّا ٱلسَّاعَةَ أَن تَأۡتِيَهُم بَغۡتَةٗ وَهُمۡ لَا يَشۡعُرُونَ
66. ሰዓቲቱን እነርሱ የማያውቁ ሆነው በድንገት ልትመጣባቸው እንጂ (ሌላ) ይጠባበቃሉን?::
Tafsiran larabci:
ٱلۡأَخِلَّآءُ يَوۡمَئِذِۭ بَعۡضُهُمۡ لِبَعۡضٍ عَدُوٌّ إِلَّا ٱلۡمُتَّقِينَ
67. አላህን የሚፈሩ ሰዎች ብቻ ሲቀሩ ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ናቸው።
Tafsiran larabci:
يَٰعِبَادِ لَا خَوۡفٌ عَلَيۡكُمُ ٱلۡيَوۡمَ وَلَآ أَنتُمۡ تَحۡزَنُونَ
68. (አላህም ለነርሱ) «ባሮቼ ሆይ! ዛሬ ቀን በእናንተ ላይ ምንም ፍርሀት የለባችሁም:: እናንተም የምታዝኑ አይደላችሁም።
Tafsiran larabci:
ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَكَانُواْ مُسۡلِمِينَ
69. «እነዚያ በአናቅጻችን ያመኑና ፍጹም ታዛዦች የነበሩ::
Tafsiran larabci:
ٱدۡخُلُواْ ٱلۡجَنَّةَ أَنتُمۡ وَأَزۡوَٰجُكُمۡ تُحۡبَرُونَ
70. (ባሮቼ ሆይ!) « እናንተም ሚስቶቻችሁም ገነትን ግቡ ትደሰታላችሁ (ትከበራላችሁ)።» ይባላሉ::
Tafsiran larabci:
يُطَافُ عَلَيۡهِم بِصِحَافٖ مِّن ذَهَبٖ وَأَكۡوَابٖۖ وَفِيهَا مَا تَشۡتَهِيهِ ٱلۡأَنفُسُ وَتَلَذُّ ٱلۡأَعۡيُنُۖ وَأَنتُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ
71. ከወርቅ የሆኑ ሰፋፊ ዝርግ ሳህኖችና ኩባያዎች በእነርሱ ላይ እንዲዞሩ ይደረጋሉ። በእርሷም ውስጥ ነፍሶች የሚከጅሉት ዓይኖችም የሚደስቱበት ሁሉ አለ:: እናንተም በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናችሁ::
Tafsiran larabci:
وَتِلۡكَ ٱلۡجَنَّةُ ٱلَّتِيٓ أُورِثۡتُمُوهَا بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
72. ይህም ያ ስትሰሩት በነበራችሁት ዋጋ የተሰጣችኋት ገነት ነው::
Tafsiran larabci:
لَكُمۡ فِيهَا فَٰكِهَةٞ كَثِيرَةٞ مِّنۡهَا تَأۡكُلُونَ
73. ለእናንተ በውስጧ ብዙ ፍራፍሬዎች አሏችሁና ከእርሷም እንደልባችሁ ትበላላችሁ ይባላሉ::
Tafsiran larabci:
 
Fassarar Ma'anoni Sura: Al'zukhruf
Teburin Jerin Sunayen Surori Lambar shafi
 
Fassarar Ma'anonin Alqura'ni - Fassarar Amhariyanci - Akadamar Afirka - Teburin Bayani kan wasu Fassarori

Fassararta Muhammad Zain Zahruddin. Fitowa daga Akademiyar Afirka.

Rufewa