Check out the new design

Fassarar Ma'anonin Alqura'ni - Fassarar Amhariyanci - Akadamar Afirka * - Teburin Bayani kan wasu Fassarori


Fassarar Ma'anoni Sura: Al'tahreem   Aya:

አት ተህሪም

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ لِمَ تُحَرِّمُ مَآ أَحَلَّ ٱللَّهُ لَكَۖ تَبۡتَغِي مَرۡضَاتَ أَزۡوَٰجِكَۚ وَٱللَّهُ غَفُورٞ رَّحِيمٞ
1. አንተ ነብይ ሆይ! አላህ ላንተ የፈቀደልህን ነገር ሚሰቶችህን ማስወደድን የምትፈልግ ስትሆን (ባንተ ላይ) ለምን እርም ታደርጋለህ? አላህ እጅግ መሀሪና አዛኝ ነው::
Tafsiran larabci:
قَدۡ فَرَضَ ٱللَّهُ لَكُمۡ تَحِلَّةَ أَيۡمَٰنِكُمۡۚ وَٱللَّهُ مَوۡلَىٰكُمۡۖ وَهُوَ ٱلۡعَلِيمُ ٱلۡحَكِيمُ
2. አላህ ለእናንተ የመሐሎቻችሁን መፍቻ ደነገገላችሁ፤ አላህ ረዳታችሁ ነው:: እርሱም ሁሉን አዋቂና እጅግ ጥበበኛ ነው።
Tafsiran larabci:
وَإِذۡ أَسَرَّ ٱلنَّبِيُّ إِلَىٰ بَعۡضِ أَزۡوَٰجِهِۦ حَدِيثٗا فَلَمَّا نَبَّأَتۡ بِهِۦ وَأَظۡهَرَهُ ٱللَّهُ عَلَيۡهِ عَرَّفَ بَعۡضَهُۥ وَأَعۡرَضَ عَنۢ بَعۡضٖۖ فَلَمَّا نَبَّأَهَا بِهِۦ قَالَتۡ مَنۡ أَنۢبَأَكَ هَٰذَاۖ قَالَ نَبَّأَنِيَ ٱلۡعَلِيمُ ٱلۡخَبِيرُ
3. ነብዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሰጠረ ጊዜ (አስታውስ):: እርሱንም በነገረችና አላህ እርሱን ማውራቷን ባሳወቀው ጊዜ ከፊሉን አሳወቀ፤ ከፊሉንም ተወ፤ በእርሱም ባወራት ጊዜ «ይህን ማን ነገረህ?» አለች፤ «ሁሉን አዋቂው እና ውስጠ አዋቂው ነገረኝ» አላት::
Tafsiran larabci:
إِن تَتُوبَآ إِلَى ٱللَّهِ فَقَدۡ صَغَتۡ قُلُوبُكُمَاۖ وَإِن تَظَٰهَرَا عَلَيۡهِ فَإِنَّ ٱللَّهَ هُوَ مَوۡلَىٰهُ وَجِبۡرِيلُ وَصَٰلِحُ ٱلۡمُؤۡمِنِينَۖ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ بَعۡدَ ذَٰلِكَ ظَهِيرٌ
4. (ሁለታችሁም) ወደ አላህ ብትመለሱ ልቦቻችሁ በእርግጥ ተዘንብለዋልና (ትስማማላችሁ):: በእርሱ (ጥቃት) ላይ ብትረዳዱ ግን ረዳቱ አላህ ነው። ጂብሪልም ከምእምናንም መልካሙ ከዚህም በኋላ መላእክቱ ረዳቶቹ ናቸው፡፡
Tafsiran larabci:
عَسَىٰ رَبُّهُۥٓ إِن طَلَّقَكُنَّ أَن يُبۡدِلَهُۥٓ أَزۡوَٰجًا خَيۡرٗا مِّنكُنَّ مُسۡلِمَٰتٖ مُّؤۡمِنَٰتٖ قَٰنِتَٰتٖ تَٰٓئِبَٰتٍ عَٰبِدَٰتٖ سَٰٓئِحَٰتٖ ثَيِّبَٰتٖ وَأَبۡكَارٗا
5. ሁላችሁንም ቢፈታችሁ ከናንተ የበለጡ ሚስቶች ሙስሊሞች፤ ትክክለኛ አማኞች፤ ታዛዦች፤ ተጸፃቾች፤ ለአላህ ተገዢዎች፤ ጿሚዎች፤ ፈቴዎችም ደናግልም የሆኑትን ጌታው ሊለውጠው ይከጅላል::
Tafsiran larabci:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ قُوٓاْ أَنفُسَكُمۡ وَأَهۡلِيكُمۡ نَارٗا وَقُودُهَا ٱلنَّاسُ وَٱلۡحِجَارَةُ عَلَيۡهَا مَلَٰٓئِكَةٌ غِلَاظٞ شِدَادٞ لَّا يَعۡصُونَ ٱللَّهَ مَآ أَمَرَهُمۡ وَيَفۡعَلُونَ مَا يُؤۡمَرُونَ
6. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከሆነች እሳት ነፍሶቻችሁንም ቤተሰቦቻችሁንም ጠብቁ፤ በእርሷ ላይ ጨካኝና ኃይለኛ የሆኑ መላዕክት አሉ:: አላህን ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፤ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሰራሉ::
Tafsiran larabci:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَا تَعۡتَذِرُواْ ٱلۡيَوۡمَۖ إِنَّمَا تُجۡزَوۡنَ مَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
7. እናንተ በአላህ የካዳችሁ ሰዎች ሆይ! ዛሬ አታመካኙ፤ የምትመነዱት ያንን ትሰሩት የነበራችሁትን ብቻ ነው (ይባላሉ)::
Tafsiran larabci:
 
Fassarar Ma'anoni Sura: Al'tahreem
Teburin Jerin Sunayen Surori Lambar shafi
 
Fassarar Ma'anonin Alqura'ni - Fassarar Amhariyanci - Akadamar Afirka - Teburin Bayani kan wasu Fassarori

Fassararta Muhammad Zain Zahruddin. Fitowa daga Akademiyar Afirka.

Rufewa