Check out the new design

Fassarar Ma'anonin Alqura'ni - Fassarar Amhariyanci - Akadamar Afirka * - Teburin Bayani kan wasu Fassarori


Fassarar Ma'anoni Sura: Al'a'raf   Aya:
قَالُوٓاْ ءَامَنَّا بِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
121. አሉም: «በዓለማት ጌታ አመንን።
Tafsiran larabci:
رَبِّ مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ
122. «በሙሳና በሃሩን ጌታ።»
Tafsiran larabci:
قَالَ فِرۡعَوۡنُ ءَامَنتُم بِهِۦ قَبۡلَ أَنۡ ءَاذَنَ لَكُمۡۖ إِنَّ هَٰذَا لَمَكۡرٞ مَّكَرۡتُمُوهُ فِي ٱلۡمَدِينَةِ لِتُخۡرِجُواْ مِنۡهَآ أَهۡلَهَاۖ فَسَوۡفَ تَعۡلَمُونَ
123. (ፊርዓውንም) አለ፡ «እኔ ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት በእርሱ አመናችሁን? ይህ በከተማይቱ ውስጥ ሰውን ከእርሷ ለማውጣት የተስማማችሁበት ተንኮል ነው:: ወደፊት የሚደርሰባችሁን ታውቃላችሁ።
Tafsiran larabci:
لَأُقَطِّعَنَّ أَيۡدِيَكُمۡ وَأَرۡجُلَكُم مِّنۡ خِلَٰفٖ ثُمَّ لَأُصَلِّبَنَّكُمۡ أَجۡمَعِينَ
124. «እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን በማፈራረቅ በእርግጥ እቆራርጣለሁ:: ከዚያም ሁላችሁንም በእንጨት ላይ እስቅላችኋለሁ።» አለ።
Tafsiran larabci:
قَالُوٓاْ إِنَّآ إِلَىٰ رَبِّنَا مُنقَلِبُونَ
125. እነርሱም አሉ: «እኛ ወደ ጌታችን ተመላሾች ነን።
Tafsiran larabci:
وَمَا تَنقِمُ مِنَّآ إِلَّآ أَنۡ ءَامَنَّا بِـَٔايَٰتِ رَبِّنَا لَمَّا جَآءَتۡنَاۚ رَبَّنَآ أَفۡرِغۡ عَلَيۡنَا صَبۡرٗا وَتَوَفَّنَا مُسۡلِمِينَ
126. «የጌታችን ተዓምራት በመጡልን ጊዜ ከማመናችን በስተቀር ከእኛ አትጠላም:: ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አፍስስ:: ሙስሊሞችም ሆነን ግደለን።» አሉ።
Tafsiran larabci:
وَقَالَ ٱلۡمَلَأُ مِن قَوۡمِ فِرۡعَوۡنَ أَتَذَرُ مُوسَىٰ وَقَوۡمَهُۥ لِيُفۡسِدُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَيَذَرَكَ وَءَالِهَتَكَۚ قَالَ سَنُقَتِّلُ أَبۡنَآءَهُمۡ وَنَسۡتَحۡيِۦ نِسَآءَهُمۡ وَإِنَّا فَوۡقَهُمۡ قَٰهِرُونَ
127. ከፈርዖን ሰዎች ቅምጥሎቹ ለፈርዖን: «ሙሳንና ሰዎችን በምድር ላይ እንዲያበላሹና ሙሳም አንተንና አምልኮትህን እንዲተው ትተዋቸዋለህን?» አሉ:: እሱም «ወንዶች ልጆቻቸውን እንገድላለን:: ሴቶቻቸውንም እናስቀራለን:: እኛም ከበላያቸው ነን አሸናፊዎች ነን» አለ።
Tafsiran larabci:
قَالَ مُوسَىٰ لِقَوۡمِهِ ٱسۡتَعِينُواْ بِٱللَّهِ وَٱصۡبِرُوٓاْۖ إِنَّ ٱلۡأَرۡضَ لِلَّهِ يُورِثُهَا مَن يَشَآءُ مِنۡ عِبَادِهِۦۖ وَٱلۡعَٰقِبَةُ لِلۡمُتَّقِينَ
128. ሙሳም ለሰዎቹ፡- «በአላህ ታገዙ፤ ታገሱም። ምድር ለአላህ ናትና ከባሮቹ መካከል ለሚሻው ያወርሳታል:: ምስጉኗም ፍጻሜ ለጥንቁቆቹ ናት።» አላቸው።
Tafsiran larabci:
قَالُوٓاْ أُوذِينَا مِن قَبۡلِ أَن تَأۡتِيَنَا وَمِنۢ بَعۡدِ مَا جِئۡتَنَاۚ قَالَ عَسَىٰ رَبُّكُمۡ أَن يُهۡلِكَ عَدُوَّكُمۡ وَيَسۡتَخۡلِفَكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَيَنظُرَ كَيۡفَ تَعۡمَلُونَ
129. ህዝቦቹም «አንተ ከመምጣትህ በፊትም ሆነ ከመጣህልን በኋላ ተሰቃየን።» አሉት:: ሙሳም «ጌታችሁ ጠላቶቻችሁን ሊያጠፋና እንዴት እንደምትሰሩ ይመለከት ዘንድ በምድር ላይ ሊተካችሁ ይከጀላል።» አላቸው።
Tafsiran larabci:
وَلَقَدۡ أَخَذۡنَآ ءَالَ فِرۡعَوۡنَ بِٱلسِّنِينَ وَنَقۡصٖ مِّنَ ٱلثَّمَرَٰتِ لَعَلَّهُمۡ يَذَّكَّرُونَ
130. የፈርዖንንም ቤተሰቦች እንዲገሰጹ በድርቅና የፍራፍሬ ምርታቸውን በመቀነስ በእርግጥ ቀጣናቸው::
Tafsiran larabci:
 
Fassarar Ma'anoni Sura: Al'a'raf
Teburin Jerin Sunayen Surori Lambar shafi
 
Fassarar Ma'anonin Alqura'ni - Fassarar Amhariyanci - Akadamar Afirka - Teburin Bayani kan wasu Fassarori

Fassararta Muhammad Zain Zahruddin. Fitowa daga Akademiyar Afirka.

Rufewa