Check out the new design

Kur'an-ı Kerim meal tercümesi - Amharca Tercüme - Afrika Akademisi * - Mealler fihristi


Anlam tercümesi Sure: Sûratu Yûnus   Ayet:
قَالَ قَدۡ أُجِيبَت دَّعۡوَتُكُمَا فَٱسۡتَقِيمَا وَلَا تَتَّبِعَآنِّ سَبِيلَ ٱلَّذِينَ لَا يَعۡلَمُونَ
89. (አላህም) ፡- «ጸሎታችሁ ተሰምታለች:: ቀጥም በሉ:: የእነዚያን የማያውቁትን ሰዎች መንገድ አትከተሉ።» አላቸው::
Arapça tefsirler:
۞ وَجَٰوَزۡنَا بِبَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ ٱلۡبَحۡرَ فَأَتۡبَعَهُمۡ فِرۡعَوۡنُ وَجُنُودُهُۥ بَغۡيٗا وَعَدۡوًاۖ حَتَّىٰٓ إِذَآ أَدۡرَكَهُ ٱلۡغَرَقُ قَالَ ءَامَنتُ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا ٱلَّذِيٓ ءَامَنَتۡ بِهِۦ بَنُوٓاْ إِسۡرَٰٓءِيلَ وَأَنَا۠ مِنَ ٱلۡمُسۡلِمِينَ
90. የኢስራኢል ልጆችን ባህሩን አሳለፍናቸው:: ፈርዖንና ሰራዊቱም ወሰን ለማለፍና ለመበደል ተከተሏቸው:: የመስመጥ አደጋ ባገኘውም ጊዜ «አመንኩ:: እነሆ ከዚያ የእሥራኤል ልጆች ካመኑበት አምላክ በስተቀር ሌላ የእውነት አምላክ የለም:: እኔም ከታዛዦቹ (ሙስሊሞች) አንዱ ነኝ።» አለ::
Arapça tefsirler:
ءَآلۡـَٰٔنَ وَقَدۡ عَصَيۡتَ قَبۡلُ وَكُنتَ مِنَ ٱلۡمُفۡسِدِينَ
91. «ከአሁን በፊት በእርግጥ ያመጽክና ከአጥፊዎችም የነበርክ ስትሆን አሁን ታምናለህን?» ተባለ።
Arapça tefsirler:
فَٱلۡيَوۡمَ نُنَجِّيكَ بِبَدَنِكَ لِتَكُونَ لِمَنۡ خَلۡفَكَ ءَايَةٗۚ وَإِنَّ كَثِيرٗا مِّنَ ٱلنَّاسِ عَنۡ ءَايَٰتِنَا لَغَٰفِلُونَ
92. እናም ዛሬ ከኋላህ ለሚመጡ ትውልዶች ተዓምር ትሆን ዘንድ አካልህን (ከባሕሩ) እናወጣሀለን ከሰዎችም ብዙዎቹ ከተዐምሮቻችን በእርግጥ ዘንጊዎች ናቸው::
Arapça tefsirler:
وَلَقَدۡ بَوَّأۡنَا بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ مُبَوَّأَ صِدۡقٖ وَرَزَقۡنَٰهُم مِّنَ ٱلطَّيِّبَٰتِ فَمَا ٱخۡتَلَفُواْ حَتَّىٰ جَآءَهُمُ ٱلۡعِلۡمُۚ إِنَّ رَبَّكَ يَقۡضِي بَيۡنَهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ فِيمَا كَانُواْ فِيهِ يَخۡتَلِفُونَ
93. የኢስራኢልን ልጆችም ምስጉንን ስፍራ በእርግጥ አሰፈርናቸው:: ከመልካም ሲሳዮችም ሰጠናቸው:: እውቀትም እስከመጣላቸው ድረስ አልተለያዩም:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በእርሱ ይለያዩበት በነበሩት ነገር በትንሳኤ ቀን በመካከላቸው ይፈርዳል::
Arapça tefsirler:
فَإِن كُنتَ فِي شَكّٖ مِّمَّآ أَنزَلۡنَآ إِلَيۡكَ فَسۡـَٔلِ ٱلَّذِينَ يَقۡرَءُونَ ٱلۡكِتَٰبَ مِن قَبۡلِكَۚ لَقَدۡ جَآءَكَ ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّكَ فَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡمُمۡتَرِينَ
94. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)) ወደ አንተ ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ከሆንክ እነዚያን ካንተ በፊት መጽሐፉን የሚያነቡትን ሰዎች ጠይቅ:: እውነቱ ከጌታህ ዘንድ መጥቶልሃል:: እናም ከተጠራጣሪዎች አትሁን::
Arapça tefsirler:
وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ فَتَكُونَ مِنَ ٱلۡخَٰسِرِينَ
95. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነዚያ የአላህን አናቅጽ ካስተባበሉት ሰዎች አትሁን:: ከከሳሪዎቹ ትሆናለህና::
Arapça tefsirler:
إِنَّ ٱلَّذِينَ حَقَّتۡ عَلَيۡهِمۡ كَلِمَتُ رَبِّكَ لَا يُؤۡمِنُونَ
96. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ የጌታህ ቃል የተረጋገጠባቸው ሰዎች አያምኑም::
Arapça tefsirler:
وَلَوۡ جَآءَتۡهُمۡ كُلُّ ءَايَةٍ حَتَّىٰ يَرَوُاْ ٱلۡعَذَابَ ٱلۡأَلِيمَ
97. ተዓምራት ሁሉ ቢመጣላቸዉም አሳማሚን ቅጣት እስከሚያዩ ድረስ(አያምኑም)::
Arapça tefsirler:
 
Anlam tercümesi Sure: Sûratu Yûnus
Surelerin fihristi Sayfa numarası
 
Kur'an-ı Kerim meal tercümesi - Amharca Tercüme - Afrika Akademisi - Mealler fihristi

Muhammed Zeyn Zehruddin Tercümesi. Afrika Akademisi Tarafından Yayınlandı.

Kapat