Check out the new design

Kur'an-ı Kerim meal tercümesi - Amharca Tercüme - Afrika Akademisi * - Mealler fihristi


Anlam tercümesi Sure: Sûratu Âl-i İmrân   Ayet:
وَلِيُمَحِّصَ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَيَمۡحَقَ ٱلۡكَٰفِرِينَ
141. አላህ እነዚያን በትክክል በእርሱ ያመኑትን ከኃጢአት ሊያጸዳና ከሓዲያንንም ሊያጠፋ ይህንን አደረገ።
Arapça tefsirler:
أَمۡ حَسِبۡتُمۡ أَن تَدۡخُلُواْ ٱلۡجَنَّةَ وَلَمَّا يَعۡلَمِ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ جَٰهَدُواْ مِنكُمۡ وَيَعۡلَمَ ٱلصَّٰبِرِينَ
142. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) አላህ ከናንተ መካከል እነዚያን የታገሉትንና ታጋሾችን ሳይለይ ገነትን የምትገቡ መሰላችሁን?
Arapça tefsirler:
وَلَقَدۡ كُنتُمۡ تَمَنَّوۡنَ ٱلۡمَوۡتَ مِن قَبۡلِ أَن تَلۡقَوۡهُ فَقَدۡ رَأَيۡتُمُوهُ وَأَنتُمۡ تَنظُرُونَ
143. በጦርነት ላይ መሞትን ሳታገኙት በፊት የምትመኙት ነበራችሁ:: እናንተም በአይናችሁ የምትመለከቱ ስትሆኑ በእርግጥ አያችሁት። (ታዲያ ለምን ሸሻችሁት?)
Arapça tefsirler:
وَمَا مُحَمَّدٌ إِلَّا رَسُولٞ قَدۡ خَلَتۡ مِن قَبۡلِهِ ٱلرُّسُلُۚ أَفَإِيْن مَّاتَ أَوۡ قُتِلَ ٱنقَلَبۡتُمۡ عَلَىٰٓ أَعۡقَٰبِكُمۡۚ وَمَن يَنقَلِبۡ عَلَىٰ عَقِبَيۡهِ فَلَن يَضُرَّ ٱللَّهَ شَيۡـٔٗاۚ وَسَيَجۡزِي ٱللَّهُ ٱلشَّٰكِرِينَ
144. (መልዕክተኛችን) ሙሐመድ ከበፊቱ ብዙ መልዕክተኞች እንዳለፉት የሆነ መልዕክተኛ እንጂ አይደለም:: ታዲያ እሱ ቢሞት ወይ ቢገደል ወደ ኋላችሁ ትገለበጣላችሁን? ወደ ኋላው የሚቀለበስም አላህን ምንም አይጎዳም:: አላህ አመስጋኞቹን ተገቢዉን ይመነዳልና::
Arapça tefsirler:
وَمَا كَانَ لِنَفۡسٍ أَن تَمُوتَ إِلَّا بِإِذۡنِ ٱللَّهِ كِتَٰبٗا مُّؤَجَّلٗاۗ وَمَن يُرِدۡ ثَوَابَ ٱلدُّنۡيَا نُؤۡتِهِۦ مِنۡهَا وَمَن يُرِدۡ ثَوَابَ ٱلۡأٓخِرَةِ نُؤۡتِهِۦ مِنۡهَاۚ وَسَنَجۡزِي ٱلشَّٰكِرِينَ
145. ማንኛዋም ነፍስ በተወሰነላት ጊዜ በአላህ ፈቃድ ቢሆን እንጂ አትሞትም። የቅርቢቱን ዓለም ምንዳ የሚፈልግን ሁሉ ከእርሷ እንሰጠዋለን:: የመጨረሻይቱን ዓለም ምንዳ የሚፈልግንም ከእርሷ እንሰጠዋለን:: አመስጋኞችንም በእርግጥ ተገቢውን እንመነዳለን::
Arapça tefsirler:
وَكَأَيِّن مِّن نَّبِيّٖ قَٰتَلَ مَعَهُۥ رِبِّيُّونَ كَثِيرٞ فَمَا وَهَنُواْ لِمَآ أَصَابَهُمۡ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ وَمَا ضَعُفُواْ وَمَا ٱسۡتَكَانُواْۗ وَٱللَّهُ يُحِبُّ ٱلصَّٰبِرِينَ
146. ከነብያት ሊቃውንት ከእነሱ ጋር ሆነው የተዋጉ ብዙ አሉ። እናም በአላህ መንገድ ለሚደርስባቸው ነገር ምንም አልፈሩም:: አልደከሙም:: ለጠላት አልተዋረዱም:: አላህም ትዕግስተኞቹን ይወዳል::
Arapça tefsirler:
وَمَا كَانَ قَوۡلَهُمۡ إِلَّآ أَن قَالُواْ رَبَّنَا ٱغۡفِرۡ لَنَا ذُنُوبَنَا وَإِسۡرَافَنَا فِيٓ أَمۡرِنَا وَثَبِّتۡ أَقۡدَامَنَا وَٱنصُرۡنَا عَلَى ٱلۡقَوۡمِ ٱلۡكَٰفِرِينَ
147. ንግግራቸዉም «ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንንና በነገራችን ሁሉ ወሰን ማለፋችንን ማርልን። ጫማዎቻችንንም አደላድል:: በከሓዲያን ሕዝቦች ላይም እርዳን።» ማለታቸው እንጂ ሌላ አልነበረም።
Arapça tefsirler:
فَـَٔاتَىٰهُمُ ٱللَّهُ ثَوَابَ ٱلدُّنۡيَا وَحُسۡنَ ثَوَابِ ٱلۡأٓخِرَةِۗ وَٱللَّهُ يُحِبُّ ٱلۡمُحۡسِنِينَ
148. አላህ የቅርቢቱን ዓለም ምንዳና የመጨረሻይቱን መልካም ምንዳ ሰጣቸው:: አላህ በጎ አድራጊዎችን ሁሉ ይወዳልና::
Arapça tefsirler:
 
Anlam tercümesi Sure: Sûratu Âl-i İmrân
Surelerin fihristi Sayfa numarası
 
Kur'an-ı Kerim meal tercümesi - Amharca Tercüme - Afrika Akademisi - Mealler fihristi

Muhammed Zeyn Zehruddin Tercümesi. Afrika Akademisi Tarafından Yayınlandı.

Kapat