Kur'an-ı Kerim meal tercümesi - الترجمة الأمهرية - زين * - Mealler fihristi


Anlam tercümesi Sure: Sûretu'l-Mumtehine   Ayet:

ሱረቱ አል ሙምተሂና

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَتَّخِذُواْ عَدُوِّي وَعَدُوَّكُمۡ أَوۡلِيَآءَ تُلۡقُونَ إِلَيۡهِم بِٱلۡمَوَدَّةِ وَقَدۡ كَفَرُواْ بِمَا جَآءَكُم مِّنَ ٱلۡحَقِّ يُخۡرِجُونَ ٱلرَّسُولَ وَإِيَّاكُمۡ أَن تُؤۡمِنُواْ بِٱللَّهِ رَبِّكُمۡ إِن كُنتُمۡ خَرَجۡتُمۡ جِهَٰدٗا فِي سَبِيلِي وَٱبۡتِغَآءَ مَرۡضَاتِيۚ تُسِرُّونَ إِلَيۡهِم بِٱلۡمَوَدَّةِ وَأَنَا۠ أَعۡلَمُ بِمَآ أَخۡفَيۡتُمۡ وَمَآ أَعۡلَنتُمۡۚ وَمَن يَفۡعَلۡهُ مِنكُمۡ فَقَدۡ ضَلَّ سَوَآءَ ٱلسَّبِيلِ
1. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጠላቶቼንና ጠላቶቻችሁን ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዙ:: የመጣላችሁን ትክክለኛ ሃይማኖት የካዱ ሲሆኑ ውዴታን ለእነርሱ ታደርጋላችሁ:: እነርሱ መልዕክተኛውና እናንተን በጌታችሁ በአላህ ስላመናችሁ ብቻ ከሀገራችሁ አስወጧችሁ። በመንገዴ ለመታገልና ውዴታየን ለመፈለግ የወጣችሁ እንደሆናችሁ እነርሱን ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዟቸው:: እኔ የምትደብቁትንና የምትገልጹትን የማውቅ ስሆን ከእነርሱ ጋር ፍቅር ትመሳጠራላችሁ:: ከናንተ መካከልም ይህንን ሚፈጽም ሰው ቀጥተኛውን መንገድ በእርግጥ ስቷል::
Arapça tefsirler:
إِن يَثۡقَفُوكُمۡ يَكُونُواْ لَكُمۡ أَعۡدَآءٗ وَيَبۡسُطُوٓاْ إِلَيۡكُمۡ أَيۡدِيَهُمۡ وَأَلۡسِنَتَهُم بِٱلسُّوٓءِ وَوَدُّواْ لَوۡ تَكۡفُرُونَ
2. ቢያሸንፏችሁ (ቢያገኟችሁ) ለእናንተ ጠላቶች ይሆናሉ:: እጆቻቸውና ምላሶቻቸውንም ወደ እናንተ በክፉ ይዘረጋሉ:: ብትክዱም ተመኙ::
Arapça tefsirler:
لَن تَنفَعَكُمۡ أَرۡحَامُكُمۡ وَلَآ أَوۡلَٰدُكُمۡۚ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ يَفۡصِلُ بَيۡنَكُمۡۚ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٞ
3. ዘመዶቻችሁም ሆኑ ልጆቻችሁ በትንሳኤ ቀን አይጠቅሟችሁም:: አላህ በትንሳኤ ቀን በመካከላችሁ (ብይን በመስጠት) ይለያል:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::
Arapça tefsirler:
قَدۡ كَانَتۡ لَكُمۡ أُسۡوَةٌ حَسَنَةٞ فِيٓ إِبۡرَٰهِيمَ وَٱلَّذِينَ مَعَهُۥٓ إِذۡ قَالُواْ لِقَوۡمِهِمۡ إِنَّا بُرَءَٰٓؤُاْ مِنكُمۡ وَمِمَّا تَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ كَفَرۡنَا بِكُمۡ وَبَدَا بَيۡنَنَا وَبَيۡنَكُمُ ٱلۡعَدَٰوَةُ وَٱلۡبَغۡضَآءُ أَبَدًا حَتَّىٰ تُؤۡمِنُواْ بِٱللَّهِ وَحۡدَهُۥٓ إِلَّا قَوۡلَ إِبۡرَٰهِيمَ لِأَبِيهِ لَأَسۡتَغۡفِرَنَّ لَكَ وَمَآ أَمۡلِكُ لَكَ مِنَ ٱللَّهِ مِن شَيۡءٖۖ رَّبَّنَا عَلَيۡكَ تَوَكَّلۡنَا وَإِلَيۡكَ أَنَبۡنَا وَإِلَيۡكَ ٱلۡمَصِيرُ
4. ኢብራሂምና እነዚያ ከእርሱ ጋር አብረው የነበሩት አማኞች ለእናንተ መልካም አርአያ ናቸው:: ይኸዉም ለህዝቦቻቸው «እኛ ከናንተና ከዚያ ከአላህ ሌላ ከምትገዙት ጣዖታት ሁሉ ንጹሆች ነን:: በእናንተም ካድን:: በአላህ አንድነት እስከምታምኑ ድረስ በእኛና በእናንተ መካከል ጠብና ጥላቻ ዘወትር ተገለጸ::» ባሉ ጊዜ ኢብራሂም ለአባቱ፡- «ላንተ ከአላህ ቅጣት ምንም የማልጠቅምህ (የማላድንህ) ስሆን ላንተ በእርግጥ ምህረትን እለምንልሃለሁ::» ማለቱ ብቻ ሲቀር «ጌታችን ሆይ ባንተ ላይ ተመካን ወደ አንተም ተመለስን መመለሻም ወደ አንተ ብቻ ነው::» (ባለው ተከተሉ።)
Arapça tefsirler:
رَبَّنَا لَا تَجۡعَلۡنَا فِتۡنَةٗ لِّلَّذِينَ كَفَرُواْ وَٱغۡفِرۡ لَنَا رَبَّنَآۖ إِنَّكَ أَنتَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ
5. ጌታችን ሆይ! ለእነዚያ ለካዱት ሰዎች መሞከሪያ አታድረገን:: ለእኛ ምህረት አድርግልን:: ጌታችን ሆይ! አንተ አሸናፊና ጥበበኛው ነህ::
Arapça tefsirler:
لَقَدۡ كَانَ لَكُمۡ فِيهِمۡ أُسۡوَةٌ حَسَنَةٞ لِّمَن كَانَ يَرۡجُواْ ٱللَّهَ وَٱلۡيَوۡمَ ٱلۡأٓخِرَۚ وَمَن يَتَوَلَّ فَإِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلۡغَنِيُّ ٱلۡحَمِيدُ
6. ከናንተ መካከል አላህንና የመጨረሻውን ቀን ተስፋ ለሚያደርግ ሰው ሁሉ እነርሱ መልካም አርአያዎች አሉላችሁ:: ፊቱን የሚያዞር ሰው (ራሱን ብቻ ይጎዳል።) አላህ ብቸኛ፤ ተብቃቂና ምስጉን ነውና::
Arapça tefsirler:
۞ عَسَى ٱللَّهُ أَن يَجۡعَلَ بَيۡنَكُمۡ وَبَيۡنَ ٱلَّذِينَ عَادَيۡتُم مِّنۡهُم مَّوَدَّةٗۚ وَٱللَّهُ قَدِيرٞۚ وَٱللَّهُ غَفُورٞ رَّحِيمٞ
7. አላህ በእናንተና በእነዚያ ከእነርሱ ጋር በተጣላችሁት ሰዎች መካከል መፋቀርን ሊያደርግ ይከጀላል:: አላህ ሁሉን ማድረግ ቻይ ነው:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::
Arapça tefsirler:
لَّا يَنۡهَىٰكُمُ ٱللَّهُ عَنِ ٱلَّذِينَ لَمۡ يُقَٰتِلُوكُمۡ فِي ٱلدِّينِ وَلَمۡ يُخۡرِجُوكُم مِّن دِيَٰرِكُمۡ أَن تَبَرُّوهُمۡ وَتُقۡسِطُوٓاْ إِلَيۡهِمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلۡمُقۡسِطِينَ
8. ለእነዚያ በሃይማኖት ላልተዋጓችሁ ከአገሮቻችሁም ላላስወጧችሁ ከሓዲያን መልካም ብትውሉላቸውና ወደ እነርሱ ፍትህ ልትውሉላቸው አላህ አይከለክላችሁም:: አላህ ትክክለኞችን (ፍትሃዊያን ትክክለኛ አማኞች) ይወዳልና::
Arapça tefsirler:
إِنَّمَا يَنۡهَىٰكُمُ ٱللَّهُ عَنِ ٱلَّذِينَ قَٰتَلُوكُمۡ فِي ٱلدِّينِ وَأَخۡرَجُوكُم مِّن دِيَٰرِكُمۡ وَظَٰهَرُواْ عَلَىٰٓ إِخۡرَاجِكُمۡ أَن تَوَلَّوۡهُمۡۚ وَمَن يَتَوَلَّهُمۡ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ
9. አላህ የሚከለክላችሁማ ከእነዚያ በሃይማኖት ሰበብ ከተዋጓችሁና ከቤቶቻችሁም ያስወጧችሁ እናንተንም ከሀገር በማስውጣት ላይ የረዱትን እንዳትወዳጇቸው ብቻ ነው:: እነርሱን ወጃጅ የሚያደርጓቸው ሰዎች ሁሉ እነዚያ እነርሱ (ራሳቸዉን) በዳዩች ናቸው::
Arapça tefsirler:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِذَا جَآءَكُمُ ٱلۡمُؤۡمِنَٰتُ مُهَٰجِرَٰتٖ فَٱمۡتَحِنُوهُنَّۖ ٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِإِيمَٰنِهِنَّۖ فَإِنۡ عَلِمۡتُمُوهُنَّ مُؤۡمِنَٰتٖ فَلَا تَرۡجِعُوهُنَّ إِلَى ٱلۡكُفَّارِۖ لَا هُنَّ حِلّٞ لَّهُمۡ وَلَا هُمۡ يَحِلُّونَ لَهُنَّۖ وَءَاتُوهُم مَّآ أَنفَقُواْۚ وَلَا جُنَاحَ عَلَيۡكُمۡ أَن تَنكِحُوهُنَّ إِذَآ ءَاتَيۡتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّۚ وَلَا تُمۡسِكُواْ بِعِصَمِ ٱلۡكَوَافِرِ وَسۡـَٔلُواْ مَآ أَنفَقۡتُمۡ وَلۡيَسۡـَٔلُواْ مَآ أَنفَقُواْۚ ذَٰلِكُمۡ حُكۡمُ ٱللَّهِ يَحۡكُمُ بَيۡنَكُمۡۖ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٞ
10. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሴት ምዕመናት ስደተኞች ሆነው ወደ እናንተ በሚመጡበት ጊዜ (ለሀይማኖት ሲሉ መሰደዳቸውን) ፈትኗቸው:: አላህ በእምነታቸው ከናንተ ይልቅ አዋቂ ነው:: ትክክለኛ አማኞችም መሆናቸውን ብታውቁ ወደ ከሓዲያን ባሎቻቸው አትመልሷቸው:: እነርሱ ሙስሊም ሴቶች ለከሓዲ ወንዶች አይፈቀዱምና:: ከሓዲያን ወንዶችም ለአማኝ ሴቶች የተፈቀዱ አይደሉምና:: ያወጡትንም ገንዘብ መህሩን ስጧቸው:: መህራቸውንም ከሰጣችኋቸው ብታገቧቸው ኃጢአት የለባችሁም :: የከሓዲያንንም ሴቶች የጋብቻ ቃል ኪዳኖች አትያዙ:: ሆኖም እናንተ ያወጣችሁትን ገንዘብ ጠይቁ :: እነርሱም ያወጡትን ይጠይቁ:: ይህ የአላህ ፍርድ ነውና:: በመካከላችሁም ይፈርዳል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::
Arapça tefsirler:
وَإِن فَاتَكُمۡ شَيۡءٞ مِّنۡ أَزۡوَٰجِكُمۡ إِلَى ٱلۡكُفَّارِ فَعَاقَبۡتُمۡ فَـَٔاتُواْ ٱلَّذِينَ ذَهَبَتۡ أَزۡوَٰجُهُم مِّثۡلَ مَآ أَنفَقُواْۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ ٱلَّذِيٓ أَنتُم بِهِۦ مُؤۡمِنُونَ
11. ከሚስቶቻችሁም አንዳቸው ወደ ከሓዲያን ቢያመልጧችሁ ቀጥሎም ብትዘምቱባቸው ለእነዚያ ሚስቶቻቸው ለሄዱባቸው ሰዎች ያወጡትን ወጪ ያክል ስጧቸው። ያንንም እናንተ በእርሱ ያመናችሁበትን አላህን ፍሩት::
Arapça tefsirler:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ إِذَا جَآءَكَ ٱلۡمُؤۡمِنَٰتُ يُبَايِعۡنَكَ عَلَىٰٓ أَن لَّا يُشۡرِكۡنَ بِٱللَّهِ شَيۡـٔٗا وَلَا يَسۡرِقۡنَ وَلَا يَزۡنِينَ وَلَا يَقۡتُلۡنَ أَوۡلَٰدَهُنَّ وَلَا يَأۡتِينَ بِبُهۡتَٰنٖ يَفۡتَرِينَهُۥ بَيۡنَ أَيۡدِيهِنَّ وَأَرۡجُلِهِنَّ وَلَا يَعۡصِينَكَ فِي مَعۡرُوفٖ فَبَايِعۡهُنَّ وَٱسۡتَغۡفِرۡ لَهُنَّ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٞ
12. አንተ ነብይ ሆይ! ምዕመናቶቹ በአላህ ምንም ላያጋሩ፤ ላይሰርቁ፤ ላያመነዝሩ፤ ልጆቻቸውን ላይገድሉ፤ በእጆቻቸውና በእግሮቻቸው መካከል ኃጢአትን ላያመጡ (ላይሰሩ)፤ በበጎም ስራም ትዕዛዝን ላይጥሱ ቃል ኪዳን ሊገቡልህ ወደ አንተ በመጡ ጊዜ ቃል ኪዳን ተጋባቸው:: ለእነርሱም አላህን ምህረት ለምንላቸው:: አላህ በጣም መሀሪና እጂግ በጣም አዛኝ ነውና::
Arapça tefsirler:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَتَوَلَّوۡاْ قَوۡمًا غَضِبَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِمۡ قَدۡ يَئِسُواْ مِنَ ٱلۡأٓخِرَةِ كَمَا يَئِسَ ٱلۡكُفَّارُ مِنۡ أَصۡحَٰبِ ٱلۡقُبُورِ
13. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህ በእነርሱ ላይ የተቆጣባቸውን ህዝቦች አትወዳጁ:: ከሓዲያን ከመቃብር ሰዎች ተስፋ እንደቆረጡ ሁሉ በመጨረሻይቱም ዓለም (ምንዳ መኖር) በእርግጥ ተስፋ ቆርጠዋል::
Arapça tefsirler:
 
Anlam tercümesi Sure: Sûretu'l-Mumtehine
Surelerin fihristi Sayfa numarası
 
Kur'an-ı Kerim meal tercümesi - الترجمة الأمهرية - زين - Mealler fihristi

ترجمة معاني القرآن الكريم إلى اللغة الأمهرية ترجمها محمد زين نهر الدين صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

Kapat