Check out the new design

قۇرئان كەرىم مەنىلىرىنىڭ تەرجىمىسى - ئەمھەرىيچە تەرجىمىسى - ئافرىقا ئاكادېمىيىسى * - تەرجىمىلەر مۇندەرىجىسى


مەنالار تەرجىمىسى سۈرە: يۇنۇس   ئايەت:
إِنَّ ٱلَّذِينَ لَا يَرۡجُونَ لِقَآءَنَا وَرَضُواْ بِٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَٱطۡمَأَنُّواْ بِهَا وَٱلَّذِينَ هُمۡ عَنۡ ءَايَٰتِنَا غَٰفِلُونَ
7. እነዚያ ከኛ ጋር መገናኘታቸውን ተስፋ የማያደርጉ ቅርቢቱን ሕይወት የወደዱና በእርሷም የረኩ እነርሱ ከአናቅጻችን ዘንጊዎች የሆኑት።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
أُوْلَٰٓئِكَ مَأۡوَىٰهُمُ ٱلنَّارُ بِمَا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ
8. እነዚያ ይሠሩት በነበሩት ኃጢአት ምክንያት መኖሪያቸው በእሳት ውስጥ ነው::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ يَهۡدِيهِمۡ رَبُّهُم بِإِيمَٰنِهِمۡۖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهِمُ ٱلۡأَنۡهَٰرُ فِي جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ
9. እነዚያ በአላህ ያመኑትና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ሰዎች ሁሉ ጌታቸው በእምነታቸው ምክንያት የገነትን መንገድ ይመራቸዋል:: ከሥሮቻቸው ወንዞች ይፈስሳሉ:: በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥም ዝንታለም ይኖራሉ::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
دَعۡوَىٰهُمۡ فِيهَا سُبۡحَٰنَكَ ٱللَّهُمَّ وَتَحِيَّتُهُمۡ فِيهَا سَلَٰمٞۚ وَءَاخِرُ دَعۡوَىٰهُمۡ أَنِ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
10. በእርሷም ውስጥ ጸሎታቸው የሚሆነው «ጌታችን ሆይ! ጥራት ይገባህ።» ማለት ብቻ ነው:: በእርሷ ውስጥ መከባበሪያቸው ሰላም መባባል ነው:: የመጨረሻ ጸሎታቸዉም «ምስጋና ሁሉ ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይገባው።» ማለት ነው።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
۞ وَلَوۡ يُعَجِّلُ ٱللَّهُ لِلنَّاسِ ٱلشَّرَّ ٱسۡتِعۡجَالَهُم بِٱلۡخَيۡرِ لَقُضِيَ إِلَيۡهِمۡ أَجَلُهُمۡۖ فَنَذَرُ ٱلَّذِينَ لَا يَرۡجُونَ لِقَآءَنَا فِي طُغۡيَٰنِهِمۡ يَعۡمَهُونَ
11. አላህ ለሰዎች ደግን ነገር ለማግኘት እንደ መቻኮላቸው የሚጠይቁትንም ክፉን ነገር ቢያቻኩልባቸው ኖሮ በዚያችው ጊዜያቸው እድሜያቸው በተፈጸመ ነበር:: እነዚያን መገናኘታችንን ተስፋ የማያደርጉትን ሰዎች በጥመታቸው ውስጥ እየዋለሉ እንተዋቸዋለን::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَإِذَا مَسَّ ٱلۡإِنسَٰنَ ٱلضُّرُّ دَعَانَا لِجَنۢبِهِۦٓ أَوۡ قَاعِدًا أَوۡ قَآئِمٗا فَلَمَّا كَشَفۡنَا عَنۡهُ ضُرَّهُۥ مَرَّ كَأَن لَّمۡ يَدۡعُنَآ إِلَىٰ ضُرّٖ مَّسَّهُۥۚ كَذَٰلِكَ زُيِّنَ لِلۡمُسۡرِفِينَ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
12. የሰውን ልጅ ጉዳት ባገኘው ጊዜ በጎኑ ላይ ተጋድሞ ወይም ተቀምጦ ወይም ቆሞ ይለምንና ጉዳቱን ከእሱ ላይ በገለጥንለት ጊዜ ላገኘው ጉዳት እንዳልተማጸንን ሆኖ ያልፋል:: ልክ እንደዚሁ ለድንበር አላፊዎች ሁሉ ይሠሩት የነበሩት መጥፎ ሥራ ተሸለመላቸው::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَلَقَدۡ أَهۡلَكۡنَا ٱلۡقُرُونَ مِن قَبۡلِكُمۡ لَمَّا ظَلَمُواْ وَجَآءَتۡهُمۡ رُسُلُهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِ وَمَا كَانُواْ لِيُؤۡمِنُواْۚ كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلۡمُجۡرِمِينَ
13. ከናንተ በፊት የነበሩትን የብዙ ክፍለ ዘመናት ሰዎች መልዕክተኞቻቸው በማስረጃዎች የመጡላቸው ሲሆኑ በበደሉና የማያምኑም በሆኑ ጊዜ አጠፋናቸው:: ልክ እንደዚሁ ተንኮለኞችን ህዝቦች እንቀጣለን::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
ثُمَّ جَعَلۡنَٰكُمۡ خَلَٰٓئِفَ فِي ٱلۡأَرۡضِ مِنۢ بَعۡدِهِمۡ لِنَنظُرَ كَيۡفَ تَعۡمَلُونَ
14. ከዚያ እንዴት እንደምትሠሩ ልንመለከት ከእነርሱ በኋላ በምድር ላይ ምትኮች አደረግናችሁ::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
 
مەنالار تەرجىمىسى سۈرە: يۇنۇس
سۈرە مۇندەرىجىسى بەت نومۇرى
 
قۇرئان كەرىم مەنىلىرىنىڭ تەرجىمىسى - ئەمھەرىيچە تەرجىمىسى - ئافرىقا ئاكادېمىيىسى - تەرجىمىلەر مۇندەرىجىسى

مۇھەممەد زەين زەھرىدىن تەرجىمە قىلغان. ئافرىقا ئاكادېمىيىسى تەرىپىدىن نەشر قىلىنغان.

تاقاش