Check out the new design

قۇرئان كەرىم مەنىلىرىنىڭ تەرجىمىسى - ئەمھەرىيچە تەرجىمىسى - ئافرىقا ئاكادېمىيىسى * - تەرجىمىلەر مۇندەرىجىسى


مەنالار تەرجىمىسى سۈرە: ئىسرا   ئايەت:
وَإِذَا مَسَّكُمُ ٱلضُّرُّ فِي ٱلۡبَحۡرِ ضَلَّ مَن تَدۡعُونَ إِلَّآ إِيَّاهُۖ فَلَمَّا نَجَّىٰكُمۡ إِلَى ٱلۡبَرِّ أَعۡرَضۡتُمۡۚ وَكَانَ ٱلۡإِنسَٰنُ كَفُورًا
67. በባህሩ ውስጥ ሆናችሁ ጉዳት በደረሰባችሁ ጊዜ የምትጠሯቸው አማልክት ሁሉ ይጠፉባችሁና እርሱ አላህ ብቻ ይቀራል። ወደ የብስም በማድረስ ባዳናችሁ ጊዜ እምነትን ትተዋላችሁ:: ሰው ሲባል በጣም ከሓዲ ነውና::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
أَفَأَمِنتُمۡ أَن يَخۡسِفَ بِكُمۡ جَانِبَ ٱلۡبَرِّ أَوۡ يُرۡسِلَ عَلَيۡكُمۡ حَاصِبٗا ثُمَّ لَا تَجِدُواْ لَكُمۡ وَكِيلًا
68. (ሰዎች ሆይ!) የየብሱን በኩል ምድርን በናንተ መገልበጡን ወይም ጠጠርን የያዘ ንፋስን በእናንተ ላይ መላኩን ከዚያም ለእናንተ ጠባቂ አለማግኘታችሁን አትፈሩምን?
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
أَمۡ أَمِنتُمۡ أَن يُعِيدَكُمۡ فِيهِ تَارَةً أُخۡرَىٰ فَيُرۡسِلَ عَلَيۡكُمۡ قَاصِفٗا مِّنَ ٱلرِّيحِ فَيُغۡرِقَكُم بِمَا كَفَرۡتُمۡ ثُمَّ لَا تَجِدُواْ لَكُمۡ عَلَيۡنَا بِهِۦ تَبِيعٗا
69. ወይስ ሌላ ጊዜ ወደ እርሱ (ወደ ባህር) የሚመልሳችሁ ወዲያውኑም በእናንተ ላይ ብርቱን ነፋስ የሚልክ፤ በክህደታችሁም ምክንያት የሚያሰምጣችሁ መሆኑን ከዚያም በእኛ ላይ በእርሱ ተከታይነት (ረዳትን) ለእናንተ የማታገኙ መሆናቸሁን አትፈሩምን?
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
۞ وَلَقَدۡ كَرَّمۡنَا بَنِيٓ ءَادَمَ وَحَمَلۡنَٰهُمۡ فِي ٱلۡبَرِّ وَٱلۡبَحۡرِ وَرَزَقۡنَٰهُم مِّنَ ٱلطَّيِّبَٰتِ وَفَضَّلۡنَٰهُمۡ عَلَىٰ كَثِيرٖ مِّمَّنۡ خَلَقۡنَا تَفۡضِيلٗا
70. የአደምን ልጆች በእርግጥ ከሌላው ፍጡር አከበርናቸው:: በየብስና በባህርም አሳፈርናቸው:: ከመልካሞችም ሲሳዮችም ሰጠናቸው፤ ከፈጠርናቸው ፍጡራንም በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጥናቸው::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
يَوۡمَ نَدۡعُواْ كُلَّ أُنَاسِۭ بِإِمَٰمِهِمۡۖ فَمَنۡ أُوتِيَ كِتَٰبَهُۥ بِيَمِينِهِۦ فَأُوْلَٰٓئِكَ يَقۡرَءُونَ كِتَٰبَهُمۡ وَلَا يُظۡلَمُونَ فَتِيلٗا
71. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰዎችን ሁሉ በመሪያቸው የምንጠራበትን ቀን አስታውስ። ያ መጽሐፉንም በቀኙ የተሰጠ ሰው እነዚያ መጽሐፋቸውን ያነባሉ፤ በተምር ፍሬ ስንጥቅ ላይ ያለውን ክር ያክል እንኳን አይበደሉም::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَمَن كَانَ فِي هَٰذِهِۦٓ أَعۡمَىٰ فَهُوَ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ أَعۡمَىٰ وَأَضَلُّ سَبِيلٗا
72. በዚህች ዓለም ልበ እውር የሆነ ሰው ሁሉ እርሱ በመጨረሻይቱም ዓለም እውር ነው:: መንገድንም በጣም የተሳሳተ ነው::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَإِن كَادُواْ لَيَفۡتِنُونَكَ عَنِ ٱلَّذِيٓ أَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡكَ لِتَفۡتَرِيَ عَلَيۡنَا غَيۡرَهُۥۖ وَإِذٗا لَّٱتَّخَذُوكَ خَلِيلٗا
73. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነሆ ከዚያም ወደ አንተ ካወረድነው ሌላን በእኛ ላይ ትዋሽ ዘንድ ሊፈትኑህ በእርግጥ ተቃረቡ፤ ያን ጊዜም ወዳጅ አድርገው በያዙህ ነበር::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَلَوۡلَآ أَن ثَبَّتۡنَٰكَ لَقَدۡ كِدتَّ تَرۡكَنُ إِلَيۡهِمۡ شَيۡـٔٗا قَلِيلًا
74.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ባላረጋጋንህም ኖሮ ወደ እነርሱ ጥቂትን ዝንባሌ ልትዘነበል በእርግጥ በተቃረብክ ነበር::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
إِذٗا لَّأَذَقۡنَٰكَ ضِعۡفَ ٱلۡحَيَوٰةِ وَضِعۡفَ ٱلۡمَمَاتِ ثُمَّ لَا تَجِدُ لَكَ عَلَيۡنَا نَصِيرٗا
75. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያን ጊዜ የሕይወትን ሆነ የሞትን ድርብ ቅጣት እናቀምስህ ነበር:: ከዚያም ላንተ በእኛ ላይ ረዳትን አታገኝም ነበር::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
 
مەنالار تەرجىمىسى سۈرە: ئىسرا
سۈرە مۇندەرىجىسى بەت نومۇرى
 
قۇرئان كەرىم مەنىلىرىنىڭ تەرجىمىسى - ئەمھەرىيچە تەرجىمىسى - ئافرىقا ئاكادېمىيىسى - تەرجىمىلەر مۇندەرىجىسى

مۇھەممەد زەين زەھرىدىن تەرجىمە قىلغان. ئافرىقا ئاكادېمىيىسى تەرىپىدىن نەشر قىلىنغان.

تاقاش