Check out the new design

قۇرئان كەرىم مەنىلىرىنىڭ تەرجىمىسى - ئەمھەرىيچە تەرجىمىسى - ئافرىقا ئاكادېمىيىسى * - تەرجىمىلەر مۇندەرىجىسى


مەنالار تەرجىمىسى سۈرە: ئال ئىمران   ئايەت:
إِذۡ هَمَّت طَّآئِفَتَانِ مِنكُمۡ أَن تَفۡشَلَا وَٱللَّهُ وَلِيُّهُمَاۗ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلۡيَتَوَكَّلِ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ
122. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ረዳታቸው ሲሆን ከእናንተ መካከል ሁለት ቡድኖች (ወገኖች) ለመፍራት ባሰቡ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: በአላህ ላይ ብቻ አማኞች ይመኩ::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَلَقَدۡ نَصَرَكُمُ ٱللَّهُ بِبَدۡرٖ وَأَنتُمۡ أَذِلَّةٞۖ فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ لَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ
123. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በበድር ዘመቻ ዕለት እናንተ ጥቂቶች ሆናችሁ ሳለ አላህ በእርግጥ ረዳችሁ:: አላህን ታመሰግኑ ዘንድ ፍሩት::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
إِذۡ تَقُولُ لِلۡمُؤۡمِنِينَ أَلَن يَكۡفِيَكُمۡ أَن يُمِدَّكُمۡ رَبُّكُم بِثَلَٰثَةِ ءَالَٰفٖ مِّنَ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ مُنزَلِينَ
124. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለአማኞች (እንዲህ) በምትል ጊዜ የሆነውን አስታውስ: «ጌታችሁ በሶስት ሺ መላዕክት የተወረዱ ሲሆኑ ቢረዳችሁ አይበቃችሁምን?
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
بَلَىٰٓۚ إِن تَصۡبِرُواْ وَتَتَّقُواْ وَيَأۡتُوكُم مِّن فَوۡرِهِمۡ هَٰذَا يُمۡدِدۡكُمۡ رَبُّكُم بِخَمۡسَةِ ءَالَٰفٖ مِّنَ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ مُسَوِّمِينَ
125. «አዎን! ብትታገሱና ብትጠነቀቁ አሁኑኑ በፍጥነት ጠላቶቻችሁ ቢመጡባችሁም ጌታችሁ ምልክት ባላቸው አምስት ሺህ መላዕክት ይረዳችኋል።»
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَمَا جَعَلَهُ ٱللَّهُ إِلَّا بُشۡرَىٰ لَكُمۡ وَلِتَطۡمَئِنَّ قُلُوبُكُم بِهِۦۗ وَمَا ٱلنَّصۡرُ إِلَّا مِنۡ عِندِ ٱللَّهِ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡحَكِيمِ
126. አላህ ለእናንተ ብስራትና ልቦቻችሁ በእርሱ እንዲረኩ እንጂ እርዳታውን ለምንም አላደረገዉም:: ድልም አሸናፊና ጥበበኛ ከሆነው ከአላህ ዘንድ ብቻ እንጂ ከሌላ ከማንም የሚገኝ አይደለም::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
لِيَقۡطَعَ طَرَفٗا مِّنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ أَوۡ يَكۡبِتَهُمۡ فَيَنقَلِبُواْ خَآئِبِينَ
127. (ድልን ያጎናፀፋችሁ) ከእነዚያ ከካዱት ከፊልን ሊቆርጥ (ሊያጠፋ) ወይም ሊያዋርዳቸውና ያፈሩ ሁነው እንዲመለሱ ነው።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
لَيۡسَ لَكَ مِنَ ٱلۡأَمۡرِ شَيۡءٌ أَوۡ يَتُوبَ عَلَيۡهِمۡ أَوۡ يُعَذِّبَهُمۡ فَإِنَّهُمۡ ظَٰلِمُونَ
128. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱ ራሳቸውን በዳዮች ናቸውና አላህ በእነርሱ ላይ ከፈለገም ይቅርታ ቢያደርግ ወይም በጥፋታቸው ቢቀጣቸውም ላንተ በነገሩ ላይ ምንም የለህም።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَلِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۚ يَغۡفِرُ لِمَن يَشَآءُ وَيُعَذِّبُ مَن يَشَآءُۚ وَٱللَّهُ غَفُورٞ رَّحِيمٞ
129. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውም ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: ለፈለገው ሰው ይምራል:: የሚፈለገውን ሰው ይቀጣል:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَأۡكُلُواْ ٱلرِّبَوٰٓاْ أَضۡعَٰفٗا مُّضَٰعَفَةٗۖ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ لَعَلَّكُمۡ تُفۡلِحُونَ
130. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አራጣን የተነባበሩ እጥፎች ሲሆኑ አትብሉ:: ከገሀነም እሳት ትድኑም ዘንድ (አራጣን በመተው) አላህን ፍሩ::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَٱتَّقُواْ ٱلنَّارَ ٱلَّتِيٓ أُعِدَّتۡ لِلۡكَٰفِرِينَ
131. ያችን ለከሓዲያን የተደገሰችውን የገሀነም እሳት ተጠንቀቁ::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَأَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَٱلرَّسُولَ لَعَلَّكُمۡ تُرۡحَمُونَ
132.(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህንና መልዕክተኛውን ታዘዙ::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
 
مەنالار تەرجىمىسى سۈرە: ئال ئىمران
سۈرە مۇندەرىجىسى بەت نومۇرى
 
قۇرئان كەرىم مەنىلىرىنىڭ تەرجىمىسى - ئەمھەرىيچە تەرجىمىسى - ئافرىقا ئاكادېمىيىسى - تەرجىمىلەر مۇندەرىجىسى

مۇھەممەد زەين زەھرىدىن تەرجىمە قىلغان. ئافرىقا ئاكادېمىيىسى تەرىپىدىن نەشر قىلىنغان.

تاقاش