Check out the new design

قۇرئان كەرىم مەنىلىرىنىڭ تەرجىمىسى - ئەمھەرىيچە تەرجىمىسى - ئافرىقا ئاكادېمىيىسى * - تەرجىمىلەر مۇندەرىجىسى

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

مەنالار تەرجىمىسى سۈرە: نىسا   ئايەت:
أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ لَعَنَهُمُ ٱللَّهُۖ وَمَن يَلۡعَنِ ٱللَّهُ فَلَن تَجِدَ لَهُۥ نَصِيرًا
52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ አላህ የረገማቸው ናቸው:: አላህ የረገመውን ደግሞ ለርሱ ፈጽሞ ረዳት አታገኝለትም።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
أَمۡ لَهُمۡ نَصِيبٞ مِّنَ ٱلۡمُلۡكِ فَإِذٗا لَّا يُؤۡتُونَ ٱلنَّاسَ نَقِيرًا
53. በእውነቱ ለእነርሱ ከንግስናው ፈንታ አላቸውን? ያን ጊዜማ ለሰዎች በተምር ፍሬ ላይ ያለችውን ነጥብ ያህል እንኳን አይሰጡም ነበር።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
أَمۡ يَحۡسُدُونَ ٱلنَّاسَ عَلَىٰ مَآ ءَاتَىٰهُمُ ٱللَّهُ مِن فَضۡلِهِۦۖ فَقَدۡ ءَاتَيۡنَآ ءَالَ إِبۡرَٰهِيمَ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡحِكۡمَةَ وَءَاتَيۡنَٰهُم مُّلۡكًا عَظِيمٗا
54. ይልቁንም ለሰዎች አላህ ከችሮታው በሰጣቸው ነገር ላይ ይመቀኛሉን? ለኢብራሂምም ቤተሰቦች መጽሐፍንና ጥበብን በእርግጥ ሰጠን:: ታላቅንም ንግስናን ሰጠናቸው::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
فَمِنۡهُم مَّنۡ ءَامَنَ بِهِۦ وَمِنۡهُم مَّن صَدَّ عَنۡهُۚ وَكَفَىٰ بِجَهَنَّمَ سَعِيرًا
55. ከነሱም (ከአይሁድ) መካከል በነብዩ ሙሐመድ ያመነ አለ:: ከእነርሱም ከዚህ እምነት ያፈገፈገ አለ። አቃጣይነት በገሀነም በቃ።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِنَا سَوۡفَ نُصۡلِيهِمۡ نَارٗا كُلَّمَا نَضِجَتۡ جُلُودُهُم بَدَّلۡنَٰهُمۡ جُلُودًا غَيۡرَهَا لِيَذُوقُواْ ٱلۡعَذَابَۗ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَزِيزًا حَكِيمٗا
56. እነዚያን በተዐምራታችን የካዱትን ሁሉ በእርግጥ እሳትን እናስገባቸዋለን:: ስቃይን እንዲቀምሱም ቆዳዎቻቸው በተቃጠሉ ቁጥር ሌሎችን ቆዳዎች እንለውጥላቸዋለን:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ سَنُدۡخِلُهُمۡ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدٗاۖ لَّهُمۡ فِيهَآ أَزۡوَٰجٞ مُّطَهَّرَةٞۖ وَنُدۡخِلُهُمۡ ظِلّٗا ظَلِيلًا
57. እነዚያ በአላህ አንድነት ያመኑና መልካም ስራዎችን የሰሩ ከስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ዘላለም በውስጣቸው ዘወታሪዎች ሲሆኑ በእርግጥ እናስገባቸዋለን:: ለእነርሱ በውስጧ ንጹህ ሚስቶችም አሏቸው:: የምታስጠልልን ጥላም እናስገባቸዋለን::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
۞ إِنَّ ٱللَّهَ يَأۡمُرُكُمۡ أَن تُؤَدُّواْ ٱلۡأَمَٰنَٰتِ إِلَىٰٓ أَهۡلِهَا وَإِذَا حَكَمۡتُم بَيۡنَ ٱلنَّاسِ أَن تَحۡكُمُواْ بِٱلۡعَدۡلِۚ إِنَّ ٱللَّهَ نِعِمَّا يَعِظُكُم بِهِۦٓۗ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ سَمِيعَۢا بَصِيرٗا
58. አላህ አደራዎችን ወደ የባለቤቶቻቸው እንድታደርሱና በሰዎች መካከል በፈረዳችሁ ጊዜም በትክክል እንድትፈርዱ ያዛችኋል:: አላህ በእርሱ የሚገስፃችሁ ነገር ምን ያምር ነው! አላህ ሁሉን ሰሚ እና ሁሉን ተመልካች ነውና።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُواْ ٱلرَّسُولَ وَأُوْلِي ٱلۡأَمۡرِ مِنكُمۡۖ فَإِن تَنَٰزَعۡتُمۡ فِي شَيۡءٖ فَرُدُّوهُ إِلَى ٱللَّهِ وَٱلرَّسُولِ إِن كُنتُمۡ تُؤۡمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِۚ ذَٰلِكَ خَيۡرٞ وَأَحۡسَنُ تَأۡوِيلًا
59. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ታዘዙ:: መልዕክተኛውን እና ከመካከላችሁም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ:: በማንኛዉም ነገር ብትከራከሩም በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ከሆናችሁ የተከራከራችሁበትን ነገር ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛው መልሱት:: ይህ የተሻለ እና መጨረሻዉም ያማረ ነው::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
 
مەنالار تەرجىمىسى سۈرە: نىسا
سۈرە مۇندەرىجىسى بەت نومۇرى
 
قۇرئان كەرىم مەنىلىرىنىڭ تەرجىمىسى - ئەمھەرىيچە تەرجىمىسى - ئافرىقا ئاكادېمىيىسى - تەرجىمىلەر مۇندەرىجىسى

مۇھەممەد زەين زەھرىدىن تەرجىمە قىلغان. ئافرىقا ئاكادېمىيىسى تەرىپىدىن نەشر قىلىنغان.

تاقاش