Check out the new design

قۇرئان كەرىم مەنىلىرىنىڭ تەرجىمىسى - ئەمھەرىيچە تەرجىمىسى - ئافرىقا ئاكادېمىيىسى * - تەرجىمىلەر مۇندەرىجىسى


مەنالار تەرجىمىسى سۈرە: مۇھەممەد   ئايەت:
إِنَّ ٱللَّهَ يُدۡخِلُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُۖ وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ يَتَمَتَّعُونَ وَيَأۡكُلُونَ كَمَا تَأۡكُلُ ٱلۡأَنۡعَٰمُ وَٱلنَّارُ مَثۡوٗى لَّهُمۡ
12. አላህ እነዚያን በእሱ ያመኑትንና መልካሞችን ተግባራት የሰሩትን ሁሉ ከስሮቻቸው ወንዞች ወደ ሚፈሱባቸው ገነቶች ያስገባቸዋል:: እነዚያም በአላህ የካዱት በቅርቢቱ ዓለም ብቻ ይጣቀማሉ። እንሰሳዎች እንደሚበሉም ይበላሉ:: የገሀነም እሳትም ለእነርሱ (የሁል ጊዜ) መኖሪያቸው ናት::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَكَأَيِّن مِّن قَرۡيَةٍ هِيَ أَشَدُّ قُوَّةٗ مِّن قَرۡيَتِكَ ٱلَّتِيٓ أَخۡرَجَتۡكَ أَهۡلَكۡنَٰهُمۡ فَلَا نَاصِرَ لَهُمۡ
13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዚያች አንተን ካወጣችህ ከተማህ ይበልጥ በሀይል ጠንካራ የሆኑ ባለቤቶቻቸዉን ያጠፋናቸው ብዙ ናቸው:: ለእነርሱም ረዳት አልነበራቸዉም::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
أَفَمَن كَانَ عَلَىٰ بَيِّنَةٖ مِّن رَّبِّهِۦ كَمَن زُيِّنَ لَهُۥ سُوٓءُ عَمَلِهِۦ وَٱتَّبَعُوٓاْ أَهۡوَآءَهُم
14. ከጌታው በሆነች አስረጅ ላይ የሆነ ምዕመን ክፉ ስራቸው ለእነርሱ እንደተሸለመላቸውና ዝንባሌዎቻቸውን እንደ ተከተሉ ክፍሎች ነውን?
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
مَّثَلُ ٱلۡجَنَّةِ ٱلَّتِي وُعِدَ ٱلۡمُتَّقُونَۖ فِيهَآ أَنۡهَٰرٞ مِّن مَّآءٍ غَيۡرِ ءَاسِنٖ وَأَنۡهَٰرٞ مِّن لَّبَنٖ لَّمۡ يَتَغَيَّرۡ طَعۡمُهُۥ وَأَنۡهَٰرٞ مِّنۡ خَمۡرٖ لَّذَّةٖ لِّلشَّٰرِبِينَ وَأَنۡهَٰرٞ مِّنۡ عَسَلٖ مُّصَفّٗىۖ وَلَهُمۡ فِيهَا مِن كُلِّ ٱلثَّمَرَٰتِ وَمَغۡفِرَةٞ مِّن رَّبِّهِمۡۖ كَمَنۡ هُوَ خَٰلِدٞ فِي ٱلنَّارِ وَسُقُواْ مَآءً حَمِيمٗا فَقَطَّعَ أَمۡعَآءَهُمۡ
15. ያች አላህን ለሚፈሩ ሰዎች ቃል የተገባችው ገነት (ይህን ትመስላለች)፤ በውስጧ ሽታው ከማይለወጥ የውሃ ወንዞች፤ ጣዕሙ የማይለወጥ የወተት ወንዞች፤ ለጠጪዎች ሁሉ እጅግ ጣፋጭ የሆኑ የወይን ጠጅ ወንዞችና የንጹህ(የተነጠረ) ማር ወንዞች አሉባት:: በውስጧ ሁሉም የፍራፍሬ አይነቶች ከጌታቸዉም ምህረት ተዘጋጅተውላቸዋል:: በእነዚህ ገነቶች የሆነ እንደነዚያ እሳት ውስጥ ዘወትር እንደሚኖሩ የፈላ ውሃም እንዲጠጡ እንደሚደረጉትና ውሃዉም የሆድ ዕቃቸውን እንደሚበጣጥስባቸው ነውን? አይደለም።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَمِنۡهُم مَّن يَسۡتَمِعُ إِلَيۡكَ حَتَّىٰٓ إِذَا خَرَجُواْ مِنۡ عِندِكَ قَالُواْ لِلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡعِلۡمَ مَاذَا قَالَ ءَانِفًاۚ أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ طَبَعَ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ وَٱتَّبَعُوٓاْ أَهۡوَآءَهُمۡ
16. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም መካከል ወደ አንተ የሚያዳምጡ አሉ:: ካንተ ዘንድ በወጡ ጊዜ ለእነዚያ እውቀት ለተሰጡት «አሁን ምን አለ?» ይላሉ:: እነዚያ እነዚህ በልቦቻቸው ላይ አላህ ያተማቸው ዝንባሌዎቻቸውን የተከተሉ ናቸው::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَٱلَّذِينَ ٱهۡتَدَوۡاْ زَادَهُمۡ هُدٗى وَءَاتَىٰهُمۡ تَقۡوَىٰهُمۡ
17. እነዚያም ወደ ቀናው መንገድ የተመሩት አላህ መመራትን ጨመረላቸው:: (ከእሳት) መጠበቂያቸውንም ሰጣቸው::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
فَهَلۡ يَنظُرُونَ إِلَّا ٱلسَّاعَةَ أَن تَأۡتِيَهُم بَغۡتَةٗۖ فَقَدۡ جَآءَ أَشۡرَاطُهَاۚ فَأَنَّىٰ لَهُمۡ إِذَا جَآءَتۡهُمۡ ذِكۡرَىٰهُمۡ
18. የሰዓቲቱንም በድንገት መምጣት እንጂ ሌላን ይጠባበቃሉን? ምልክቶቿም በእርግጥ መጥተዋል:: በመጣችባቸዉም ጊዜ ማስታወሳቸው ለእነርሱ እንዴት ይጠቅማቸዋል::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
فَٱعۡلَمۡ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا ٱللَّهُ وَٱسۡتَغۡفِرۡ لِذَنۢبِكَ وَلِلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتِۗ وَٱللَّهُ يَعۡلَمُ مُتَقَلَّبَكُمۡ وَمَثۡوَىٰكُمۡ
19. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነሆ ከአላህ ሌላ ትክክለኛ አምላክ አለመኖሩንም እወቅ:: ስለ ስህተትህም ሆነ ለወንድም ለሴትም አማኞች ስህተት ምህረትን ለምን:: አላህም መዘዋወሪያችሁንም ሆነ መርጊያችሁን ያውቃል::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
 
مەنالار تەرجىمىسى سۈرە: مۇھەممەد
سۈرە مۇندەرىجىسى بەت نومۇرى
 
قۇرئان كەرىم مەنىلىرىنىڭ تەرجىمىسى - ئەمھەرىيچە تەرجىمىسى - ئافرىقا ئاكادېمىيىسى - تەرجىمىلەر مۇندەرىجىسى

مۇھەممەد زەين زەھرىدىن تەرجىمە قىلغان. ئافرىقا ئاكادېمىيىسى تەرىپىدىن نەشر قىلىنغان.

تاقاش