قۇرئان كەرىم مەنىلىرىنىڭ تەرجىمىسى - الترجمة الأمهرية - زين * - تەرجىمىلەر مۇندەرىجىسى


مەنالار تەرجىمىسى سۈرە: سۈرە زارىيات   ئايەت:

ሱረቱ አዝ ዛሪያት

وَٱلذَّٰرِيَٰتِ ذَرۡوٗا
1. መበተንን በታኝ በሆኑት (ንፋሶች) እምላለሁ
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
فَٱلۡحَٰمِلَٰتِ وِقۡرٗا
2. ከባድ ዝናብን ተሸካሚዎች በሆኑትም (ዳመናዎች)፤
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
فَٱلۡجَٰرِيَٰتِ يُسۡرٗا
3. ገር መንሻለልን ተንሻላዩች በሆኑትም (መርከቦች) እምላለሁ::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
فَٱلۡمُقَسِّمَٰتِ أَمۡرًا
4. ጉዳይን ሁሉ አከፋፋዮች በሆኑትም (መላዕክት) እምላለሁ::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
إِنَّمَا تُوعَدُونَ لَصَادِقٞ
5. የምተቀጠሩት ትንሳኤ እውነት ነው::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَإِنَّ ٱلدِّينَ لَوَٰقِعٞ
6. (እንደየስራው) ዋጋን ማግኘትም የማይቀር ነው።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَٱلسَّمَآءِ ذَاتِ ٱلۡحُبُكِ
7.የ(ከዋክብት) መንገዶች ባለቤት በሆነችው ሰማይ እምላለሁ::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
إِنَّكُمۡ لَفِي قَوۡلٖ مُّخۡتَلِفٖ
8. እናንተ በተለያየ ቃል ውስጥ ናችሁ።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
يُؤۡفَكُ عَنۡهُ مَنۡ أُفِكَ
9. ከእርሱ የሚዝዞር ሰው ይዝዞራል::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
قُتِلَ ٱلۡخَرَّٰصُونَ
10. በግምት የሚናገሩ ውሸታሞች ተረገሙ::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
ٱلَّذِينَ هُمۡ فِي غَمۡرَةٖ سَاهُونَ
11. እነዚያ እነርሱ በሚሸፍን ስህተት ውስጥ ዘንጊዎች የሆኑት::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
يَسۡـَٔلُونَ أَيَّانَ يَوۡمُ ٱلدِّينِ
12. የዋጋ መስጫው ቀን መቼ እንደሆነ ይጠይቃሉ::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
يَوۡمَ هُمۡ عَلَى ٱلنَّارِ يُفۡتَنُونَ
13. (እነርሱ) በእሳት ላይ በሚፈተኑበት ቀን ነው::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
ذُوقُواْ فِتۡنَتَكُمۡ هَٰذَا ٱلَّذِي كُنتُم بِهِۦ تَسۡتَعۡجِلُونَ
14. «መከራችሁን ቅመሱ ይህ ያ በእርሱ ትቻኮሉበት የነበራችሁት ነው» (ይባላሉ)::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
إِنَّ ٱلۡمُتَّقِينَ فِي جَنَّٰتٖ وَعُيُونٍ
15. አላህን ፈሪዎቹ በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
ءَاخِذِينَ مَآ ءَاتَىٰهُمۡ رَبُّهُمۡۚ إِنَّهُمۡ كَانُواْ قَبۡلَ ذَٰلِكَ مُحۡسِنِينَ
16. ያንን ጌታቸው የሰጣቸውን ተቀባዮች ሆነው በገነት ውስጥ ይሆናሉ:: እነርሱ ከዚህ በፊት መልካም ሰሪዎች ነበሩና::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
كَانُواْ قَلِيلٗا مِّنَ ٱلَّيۡلِ مَا يَهۡجَعُونَ
17. ከሌሊቱ ጥቂቱን ብቻ ይተኙ ነበር::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَبِٱلۡأَسۡحَارِ هُمۡ يَسۡتَغۡفِرُونَ
18. በሌሊቱ መጨረሻዎችም እነርሱ ምህረትን ይለምናሉ::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَفِيٓ أَمۡوَٰلِهِمۡ حَقّٞ لِّلسَّآئِلِ وَٱلۡمَحۡرُومِ
19. በገንዘቦቻቸዉም ውስጥ ለለማኝና ከልመና ለተከለከለም (በችሮታቸው) መብት አለ።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَفِي ٱلۡأَرۡضِ ءَايَٰتٞ لِّلۡمُوقِنِينَ
20. በምድርም ውስጥ ለሚያረጋግጡ ሰዎች አያሌ ምልክቶች አሉ::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَفِيٓ أَنفُسِكُمۡۚ أَفَلَا تُبۡصِرُونَ
21. (ሰዎች ሆይ!) በነፍሶቻችሁም ውስጥ አያሌ ምልክቶች አሉ:: ታዲያ አትመለከቱምን?
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَفِي ٱلسَّمَآءِ رِزۡقُكُمۡ وَمَا تُوعَدُونَ
22. ሲሳያችሁም የምትቀጠሩት (ፍዳና ምንዳ) በሰማይ ነው።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
فَوَرَبِّ ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِ إِنَّهُۥ لَحَقّٞ مِّثۡلَ مَآ أَنَّكُمۡ تَنطِقُونَ
23. በሰማይና በምድር ጌታም እምላለሁ። እርሱ እናንተ እንደምትናገሩት ብጤ እርግጠኛ (እውነት) ነው።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
هَلۡ أَتَىٰكَ حَدِيثُ ضَيۡفِ إِبۡرَٰهِيمَ ٱلۡمُكۡرَمِينَ
24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የተከበሩት የኢብራሂም እንግዶች ወሬ መጥቶሃልን?
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
إِذۡ دَخَلُواْ عَلَيۡهِ فَقَالُواْ سَلَٰمٗاۖ قَالَ سَلَٰمٞ قَوۡمٞ مُّنكَرُونَ
25. በእርሱም ላይ በገቡና «ሰላም» ባሉት ጊዜ ምን እንደሆነ አስታውስ። ሰላም ግና ያልታወቃችሁ ህዝቦች ናችሁ አላቸው።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
فَرَاغَ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِۦ فَجَآءَ بِعِجۡلٖ سَمِينٖ
26. ወደ ቤተሰቡም ተዘነበለና ወዲያውም የሰባ ወይፈን አመጣ::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
فَقَرَّبَهُۥٓ إِلَيۡهِمۡ قَالَ أَلَا تَأۡكُلُونَ
27. ከዚያ ወደ እነርሱ (አዘጋጅቶ) አቀረበውና «አትበሉም ወይ? አላቸው።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
فَأَوۡجَسَ مِنۡهُمۡ خِيفَةٗۖ قَالُواْ لَا تَخَفۡۖ وَبَشَّرُوهُ بِغُلَٰمٍ عَلِيمٖ
28. ከእነርሱ መፍራትን በልቡ አሳደረ። «አትፍራ» አሉትም በአዋቂ ልጅም አበስሩት::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
فَأَقۡبَلَتِ ٱمۡرَأَتُهُۥ فِي صَرَّةٖ فَصَكَّتۡ وَجۡهَهَا وَقَالَتۡ عَجُوزٌ عَقِيمٞ
29. ሚስቱም (በደስታ) እየጮኸች መጣች፤ ፊቷንም መታች «መካን አሮጊት (ነኝ)» አለችም።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
قَالُواْ كَذَٰلِكِ قَالَ رَبُّكِۖ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡحَكِيمُ ٱلۡعَلِيمُ
30. እነርሱም «ጌታሽ 'እንዲሁ (ይሁን)' ብሏል። እነሆ እርሱ ጥበበኛና ሁሉን አዋቂ ነው» አሏት::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
۞ قَالَ فَمَا خَطۡبُكُمۡ أَيُّهَا ٱلۡمُرۡسَلُونَ
31. «እናንተ መልዕክተኞች ሆይ! ታዲያ ነገራችሁ ምንድን ነው?» አላቸው::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
قَالُوٓاْ إِنَّآ أُرۡسِلۡنَآ إِلَىٰ قَوۡمٖ مُّجۡرِمِينَ
32. እነርሱም አሉ: «እኛ ወደ አመጸኖች ህዝቦች ተልከናል።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
لِنُرۡسِلَ عَلَيۡهِمۡ حِجَارَةٗ مِّن طِينٖ
33. «በእነርሱ ላይ ከጭቃ የሆኑ ድንጋዮችን ልንለቅባቸው ተላክን።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
مُّسَوَّمَةً عِندَ رَبِّكَ لِلۡمُسۡرِفِينَ
34. «በጌታህ ዘንድ ለድንበር አላፊዎቹ በየስማቸው ምልክት የተደረገባት ስትሆን።» አሉ
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
فَأَخۡرَجۡنَا مَن كَانَ فِيهَا مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
35. ከምዕመናም በእርሷ በከተማቸው ውስጥ የነበሩትን አወጣን::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
فَمَا وَجَدۡنَا فِيهَا غَيۡرَ بَيۡتٖ مِّنَ ٱلۡمُسۡلِمِينَ
36. በውስጧም ከአንድ ቤት ቤተሰቦች በስተቀር ሙስሊሞችን አላገኘንም::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَتَرَكۡنَا فِيهَآ ءَايَةٗ لِّلَّذِينَ يَخَافُونَ ٱلۡعَذَابَ ٱلۡأَلِيمَ
37. በውስጧም ለእነዚያ አሳማሚውን ቅጣት ለሚፈሩት ምልክትን አስቀረን::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَفِي مُوسَىٰٓ إِذۡ أَرۡسَلۡنَٰهُ إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ بِسُلۡطَٰنٖ مُّبِينٖ
38. በሙሳ ወሬ ውስጥም ወደ ፈርዖን በግልጽ ማስረጃ በላክነው ጊዜ (ምልክትን አደረግን)::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
فَتَوَلَّىٰ بِرُكۡنِهِۦ وَقَالَ سَٰحِرٌ أَوۡ مَجۡنُونٞ
39. ከድጋፉ (ከሰራዊቱ) ጋርም ከእምነት ዞረ:: «እርሱ ድግምተኛ ወይም እብድ ነው» አለ::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
فَأَخَذۡنَٰهُ وَجُنُودَهُۥ فَنَبَذۡنَٰهُمۡ فِي ٱلۡيَمِّ وَهُوَ مُلِيمٞ
40. እርሱንም ሰራዊቱንም ያዝናቸው እርሱ ተወቃሽ ሲሆን በባህር ውስጥ ጣልናቸውም።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَفِي عَادٍ إِذۡ أَرۡسَلۡنَا عَلَيۡهِمُ ٱلرِّيحَ ٱلۡعَقِيمَ
41. በዓድም በእነርሱ ላይ መካን (የሆነች) ንፋስን በላክን ጊዜ ምልክት አለ::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
مَا تَذَرُ مِن شَيۡءٍ أَتَتۡ عَلَيۡهِ إِلَّا جَعَلَتۡهُ كَٱلرَّمِيمِ
42. በላዩ ላይ የመጣችበትን ማንኛዉንም ነገር እንደበሰበሰ አጥነት ያደረገችው ብትሆን እንጂ አትተወዉም።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَفِي ثَمُودَ إِذۡ قِيلَ لَهُمۡ تَمَتَّعُواْ حَتَّىٰ حِينٖ
43. በሰሙድም ለእነርሱ «እስከ ጊዜ (ሞታችሁ) ድረስ ተጣቀሙ።» በተባሉ ጊዜ (ምልክት አለ)።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
فَعَتَوۡاْ عَنۡ أَمۡرِ رَبِّهِمۡ فَأَخَذَتۡهُمُ ٱلصَّٰعِقَةُ وَهُمۡ يَنظُرُونَ
44. ከጌታቸው ትዕዘዝም ኮሩ:: እነርሱም እያዩ ጩኸቷ ያዘቻቸው::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
فَمَا ٱسۡتَطَٰعُواْ مِن قِيَامٖ وَمَا كَانُواْ مُنتَصِرِينَ
45. መቆምንም አልቻሉም:: እርዳታ የሚደረግላቸውም አልነበሩም::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَقَوۡمَ نُوحٖ مِّن قَبۡلُۖ إِنَّهُمۡ كَانُواْ قَوۡمٗا فَٰسِقِينَ
46. የኑህንም ህዝቦች (ከዚህ በፊት አጠፋን) እነርሱ አመጸኞች ህዝቦች ነበሩና::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَٱلسَّمَآءَ بَنَيۡنَٰهَا بِأَيۡيْدٖ وَإِنَّا لَمُوسِعُونَ
47. ሰማይንም በሀይል ገነባናት:: እኛም በእርግጥ የምናስፋት ነን::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَٱلۡأَرۡضَ فَرَشۡنَٰهَا فَنِعۡمَ ٱلۡمَٰهِدُونَ
48. ምድርንም ዘረጋናት ምን ያማርንም ዘርጊዎች ነን::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَمِن كُلِّ شَيۡءٍ خَلَقۡنَا زَوۡجَيۡنِ لَعَلَّكُمۡ تَذَكَّرُونَ
49. ትገነዘቡም ዘንድ ከነገሩ ሁሉ ሁለት ተቃራኒ አይነትን ፈጠርን::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
فَفِرُّوٓاْ إِلَى ٱللَّهِۖ إِنِّي لَكُم مِّنۡهُ نَذِيرٞ مُّبِينٞ
50. ወደ አላህም ሽሹ እኔ ለእናንተ ከእርሱ ግልጽ አስጠንቃቂ ነኝ።
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَلَا تَجۡعَلُواْ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَۖ إِنِّي لَكُم مِّنۡهُ نَذِيرٞ مُّبِينٞ
51. ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አታድርጉ:: እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላኩ:: ግልጽ አስፈራሪ ነኝና::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
كَذَٰلِكَ مَآ أَتَى ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِم مِّن رَّسُولٍ إِلَّا قَالُواْ سَاحِرٌ أَوۡ مَجۡنُونٌ
52. ልክ እንደዚሁ እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ከመልዕክተኛ ማንም አልመጣቸዉም:: «እርሱ ድግምተኛ ወይም እብድ ነው» ያሉ ቢሆን እንጂ::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
أَتَوَاصَوۡاْ بِهِۦۚ بَلۡ هُمۡ قَوۡمٞ طَاغُونَ
53. በእርሱ (በዚህ ቃል) አደራ ተባብለዋልን? ይልቁን እነርሱ ጥጋበኞች ህዝቦች ናቸው::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
فَتَوَلَّ عَنۡهُمۡ فَمَآ أَنتَ بِمَلُومٖ
54. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ዘወር በል (ተዋቸው)፤ አንተ ምንም ተወቃሽ አይደለህምና::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَذَكِّرۡ فَإِنَّ ٱلذِّكۡرَىٰ تَنفَعُ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
55. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ገስጽም ግሳጼ አማኞችን ትጠቅማለችና::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
وَمَا خَلَقۡتُ ٱلۡجِنَّ وَٱلۡإِنسَ إِلَّا لِيَعۡبُدُونِ
56. ጋኔንና ሰዉን ሊገዙኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸዉም::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
مَآ أُرِيدُ مِنۡهُم مِّن رِّزۡقٖ وَمَآ أُرِيدُ أَن يُطۡعِمُونِ
57. ከእነርሱም ምንም ሲሳይን አልፈልግም:: እንዲመግቡኝም አልፈልግም::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلرَّزَّاقُ ذُو ٱلۡقُوَّةِ ٱلۡمَتِينُ
58. አላህ ሰጪና የብርቱ ሀይል ባለቤት ነውና::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
فَإِنَّ لِلَّذِينَ ظَلَمُواْ ذَنُوبٗا مِّثۡلَ ذَنُوبِ أَصۡحَٰبِهِمۡ فَلَا يَسۡتَعۡجِلُونِ
59. ለእነዚያም ለበደሉት እንደ ጓደኞቻቸው ፋንታ ብጤ የቅጣት ፋንታ አለላቸው:: ስለዚህ አያስቸኩሉኝ::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
فَوَيۡلٞ لِّلَّذِينَ كَفَرُواْ مِن يَوۡمِهِمُ ٱلَّذِي يُوعَدُونَ
60. ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ከዚያ ከሚቀጠሩት ቀናቸው ወዩላቸው::
ئەرەپچە تەپسىرلەر:
 
مەنالار تەرجىمىسى سۈرە: سۈرە زارىيات
سۈرە مۇندەرىجىسى بەت نومۇرى
 
قۇرئان كەرىم مەنىلىرىنىڭ تەرجىمىسى - الترجمة الأمهرية - زين - تەرجىمىلەر مۇندەرىجىسى

ترجمة معاني القرآن الكريم إلى اللغة الأمهرية ترجمها محمد زين نهر الدين صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

تاقاش