Check out the new design

የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም - በመሐመድ ሳዲቅ * - የትርጉሞች ማዉጫ

XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: አል-ፋቲሃ   አንቀጽ:

አል-ፋቲሃ

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡[1]
[1] የመክፈቻይቱ ምእራፍ የቁርኣን በላጭ ሱራ ነች። ነቢዩ ሰ.ዐ.ወ. ለአቢ ሰዒድ እንዲህ አሉ፡- “ከቁርኣን ሱራዎች ውስጥ በላጩን አሳውቅሃለሁ እርሱም አልሃምዱ ሊላሂ ረቢል ዓላሚን- ነው።" [ቡኻሪ ዘግበውታል]።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው፤
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
مَٰلِكِ يَوۡمِ ٱلدِّينِ
የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِيَّاكَ نَعۡبُدُ وَإِيَّاكَ نَسۡتَعِينُ
አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ٱهۡدِنَا ٱلصِّرَٰطَ ٱلۡمُسۡتَقِيمَ
ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
صِرَٰطَ ٱلَّذِينَ أَنۡعَمۡتَ عَلَيۡهِمۡ غَيۡرِ ٱلۡمَغۡضُوبِ عَلَيۡهِمۡ وَلَا ٱلضَّآلِّينَ
የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን፤ በሉ)፡፡ [1]
[1] ኣሚን የምትል ቃል በሶላት ውስጥ እዚህ ትባላለች፤ እንደውም ድምጽ ከፍ በምደረግበት ሶላት ውስጥ ጀማኣው በአንድነት ድምጽ ከፍ ተደርጎ ማለት ያስፈልጋል። ግን እሷ ከፋትሃ አይደለችም።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
 
የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: አል-ፋቲሃ
የምዕራፎች ማውጫ የገፅ ቁጥር
 
የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም - በመሐመድ ሳዲቅ - የትርጉሞች ማዉጫ

በሙሐመድ ሧዲቅ ከሙሐመድ ሳኒ ሐቢብ ጋር በመሆን ተተርጉሞ በሩዋድ የትርጉም ማዕከል ቁጥጥር ስር ማሻሻያ የተደረገበት ፤ አስተያየትና ሃሳቦን ሰጥተው በዘለቄታው እንዲሻሻል መሰረታዊ ትርጉሙን ማየት ይችላሉ

መዝጋት