የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የ አማርኛ ቋንቋ ትርጉም * - የትርጉሞች ማዉጫ

XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: ሱረቱ አል ቀድር   አንቀጽ:

ሱረቱ አል ቀድር

إِنَّآ أَنزَلۡنَٰهُ فِي لَيۡلَةِ ٱلۡقَدۡرِ
እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው፡፡ {1}
{1} ይህች ሌሊት በሮመዳን ውስጥ ትገኛለች ። በመጨረሻዎቹ አስርት ሌሊቶች ከነሱም በኢተጋማሽ ሌሊቶች በ21፣ 23፣ 25፣ 27፣ 29 ውስጥ ትገኛለች ። እርሷን በሶላትና በኢባዳ ያሳለፋ ሰው ያለፈው ሃጥአቱ ምህረት ይደረግለታል።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا لَيۡلَةُ ٱلۡقَدۡرِ
መወሰኛይቱም ሌሊተ ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لَيۡلَةُ ٱلۡقَدۡرِ خَيۡرٞ مِّنۡ أَلۡفِ شَهۡرٖ
መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
تَنَزَّلُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ وَٱلرُّوحُ فِيهَا بِإِذۡنِ رَبِّهِم مِّن كُلِّ أَمۡرٖ
በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ (ጂብሪል) በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
سَلَٰمٌ هِيَ حَتَّىٰ مَطۡلَعِ ٱلۡفَجۡرِ
እርስዋ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት፡፡
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
 
የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: ሱረቱ አል ቀድር
የምዕራፎች ማውጫ የገፅ ቁጥር
 
የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የ አማርኛ ቋንቋ ትርጉም - የትርጉሞች ማዉጫ

ወደ አማርኛ በሸይኽ ሙሓመድ ሷዲቅ እና በሸይኽ ሙሓመድ ሣኒ ሓቢብ የተተረጎመ የቁርዓን መልዕክተ ትርጉም። በሩዋድ የትርጉም ማእከልም ተቆጣጣሪነት ማስተካከያ ተደርጎበታል። ዋናው የትርጉም ቅጅም ለአስተያየቶች፣ ተከታታይ ግምገማ እና መሻሻል ቀርቧል።

መዝጋት