Check out the new design

የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ * - የትርጉሞች ማዉጫ


የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: ዩኑስ   አንቀጽ:
وَقَالَ فِرۡعَوۡنُ ٱئۡتُونِي بِكُلِّ سَٰحِرٍ عَلِيمٖ
79. ፈርዖን፡- «አዋቂ ድግምተኛን ሁሉ አምጡልኝ።» አለ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَلَمَّا جَآءَ ٱلسَّحَرَةُ قَالَ لَهُم مُّوسَىٰٓ أَلۡقُواْ مَآ أَنتُم مُّلۡقُونَ
80. ድግምተኞቹ በመጡ ጊዜም ሙሳ ለእነርሱ፡- «እናንተ የምትጥሉትን ነገር ጣሉ።» አላቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَلَمَّآ أَلۡقَوۡاْ قَالَ مُوسَىٰ مَا جِئۡتُم بِهِ ٱلسِّحۡرُۖ إِنَّ ٱللَّهَ سَيُبۡطِلُهُۥٓ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُصۡلِحُ عَمَلَ ٱلۡمُفۡسِدِينَ
81. በጣሉም ጊዜ ሙሳ፡- «ያ በእርሱ የመጣችሁበት ነገር ድግምት ነው:: አላህ በእርግጥ ያፈርሰዋል:: አላህ የአጥፊዎችን ሥራ ፈጽሞ አያበጅምና።» አለ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَيُحِقُّ ٱللَّهُ ٱلۡحَقَّ بِكَلِمَٰتِهِۦ وَلَوۡ كَرِهَ ٱلۡمُجۡرِمُونَ
82. አላህም ከሓዲያን ቢጠሉም እውነትን በቃላቱ ያረጋግጣል::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَمَآ ءَامَنَ لِمُوسَىٰٓ إِلَّا ذُرِّيَّةٞ مِّن قَوۡمِهِۦ عَلَىٰ خَوۡفٖ مِّن فِرۡعَوۡنَ وَمَلَإِيْهِمۡ أَن يَفۡتِنَهُمۡۚ وَإِنَّ فِرۡعَوۡنَ لَعَالٖ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَإِنَّهُۥ لَمِنَ ٱلۡمُسۡرِفِينَ
83. ለሙሳም ከፈርዖንና ከሹማምንቶቻቸው ማሰቃየትን በመፍራት ከወገኖቹ ጥቂት ትውልዶች ብቻ እንጂ አላመኑለትም:: ፈርዖንም በምድር ላይ በእርግጥ ይኮራ ነበር። እርሱም በእርግጥ ወሰን ካለፉት ነበር።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَقَالَ مُوسَىٰ يَٰقَوۡمِ إِن كُنتُمۡ ءَامَنتُم بِٱللَّهِ فَعَلَيۡهِ تَوَكَّلُوٓاْ إِن كُنتُم مُّسۡلِمِينَ
84. ሙሳም፡- «ህዝቦቼ ሆይ! በአላህ አምናችሁ እንደ ሆነ በእርሱ ላይ ብቻ ተጠጉ:: ታዛዦች እንደ ሆናችሁም በአላህ ላይ ብቻ ተመኩ።» አለ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَقَالُواْ عَلَى ٱللَّهِ تَوَكَّلۡنَا رَبَّنَا لَا تَجۡعَلۡنَا فِتۡنَةٗ لِّلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ
85. አሉ፡- «በአላህ ላይ ተጠጋን:: ጌታችን ሆይ! ለበደለኞች ህዝቦች መፈተኛ አታድርገን::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَنَجِّنَا بِرَحۡمَتِكَ مِنَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلۡكَٰفِرِينَ
86. «በእዝነትህም ከከሓዲያን ህዝቦች ግፍ አድነን።»
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰ وَأَخِيهِ أَن تَبَوَّءَا لِقَوۡمِكُمَا بِمِصۡرَ بُيُوتٗا وَٱجۡعَلُواْ بُيُوتَكُمۡ قِبۡلَةٗ وَأَقِيمُواْ ٱلصَّلَوٰةَۗ وَبَشِّرِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
87. ወደ ሙሳና ወደ ወንድሙ፡ «ለህዝቦቻችሁ በግብጽ ውስጥ ቤቶችን ሥሩ:: ቤቶቻችሁንም መስገጃ አድርጉ:: ሶላትንም በደንቡ ስገዱ:: ምዕመናኖቹንም አብስር።» ስንል ላክን::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَقَالَ مُوسَىٰ رَبَّنَآ إِنَّكَ ءَاتَيۡتَ فِرۡعَوۡنَ وَمَلَأَهُۥ زِينَةٗ وَأَمۡوَٰلٗا فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا رَبَّنَا لِيُضِلُّواْ عَن سَبِيلِكَۖ رَبَّنَا ٱطۡمِسۡ عَلَىٰٓ أَمۡوَٰلِهِمۡ وَٱشۡدُدۡ عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ فَلَا يُؤۡمِنُواْ حَتَّىٰ يَرَوُاْ ٱلۡعَذَابَ ٱلۡأَلِيمَ
88. ሙሳም: «ጌታችን ሆይ! አንተ ለፈርዖንና ለሹሞቹ በቅርቢቱ ህይወት ጌጥን ብዙ ገንዘቦችንም በእርግጥ ሰጠህ:: ጌታችን ሆይ! ከመንገድህ ያሳስቱ ዘንድ ሰጠሃቸው:: ጌታችን ሆይ! ገንዘቦቻቸውን አጥፋ:: በልቦቻቸዉም ላይ አትም:: አሳማሚን ቅጣት አስከሚያዩ አያምኑምና።» አለ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
 
የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: ዩኑስ
የምዕራፎች ማውጫ የገፅ ቁጥር
 
የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ - የትርጉሞች ማዉጫ

ተርጓሙ በመሐመድ ዘይን ዘህር ዲን። የተሰኘ በአፍሪካ አካዳሚ።

መዝጋት