የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - አማርኛ ትርጉም ‐ ዘይን * - የትርጉሞች ማዉጫ


የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: ሱረቱ አን-ነሕል   አንቀጽ:

ሱረቱ አን-ነሕል

أَتَىٰٓ أَمۡرُ ٱللَّهِ فَلَا تَسۡتَعۡجِلُوهُۚ سُبۡحَٰنَهُۥ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشۡرِكُونَ
1. (ከሓዲያን ሆይ!)፤ የአላህ ትዕዛዝ መጣ ስለዚህ አታጣድፉት:: አላህ ከማይገባው ሁሉ ጠራ:: ከሚያጋሩትም ሁሉ ላቀ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
يُنَزِّلُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةَ بِٱلرُّوحِ مِنۡ أَمۡرِهِۦ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ مِنۡ عِبَادِهِۦٓ أَنۡ أَنذِرُوٓاْ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱتَّقُونِ
2. ከባሮቹ መካከል በሚሻው ሰው ላይ መላዕክትን ከራዕይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል:: «ከሓዲያንን በቅጣት አስጠንቅቁ:: እነሆ ከእኔ በስተቀር ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: ፍሩኝም።» ማለትን አስታውቁ በማለት ያወርዳል።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ بِٱلۡحَقِّۚ تَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشۡرِكُونَ
3. ሰማያትንና ምድርን በእውነት ፈጠረ:: ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ :: ከፍም አለ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
خَلَقَ ٱلۡإِنسَٰنَ مِن نُّطۡفَةٖ فَإِذَا هُوَ خَصِيمٞ مُّبِينٞ
4.ሰውን ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው:: ከዚያም እርሱ ወዲያውኑ ትንሣኤን በመካድ ግልጽ ተከራካሪ ይሆናል::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَٱلۡأَنۡعَٰمَ خَلَقَهَاۖ لَكُمۡ فِيهَا دِفۡءٞ وَمَنَٰفِعُ وَمِنۡهَا تَأۡكُلُونَ
5. (ሰዎች ሆይ!) ግመልን፤ ከብትን፤ ፍየልንም፤ በእርሷ ብርድ መከላከያ ሙቀትና ሌሎች ጥቅሞችም ያሉባት ስትሆን ለእናንተ ፈጠረላችሁ:: ከእርሷም ትበላላችሁ (ትመገባላችሁ)::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلَكُمۡ فِيهَا جَمَالٌ حِينَ تُرِيحُونَ وَحِينَ تَسۡرَحُونَ
6. በእርሷም ወደ ማረፊያዋ በምትመልሷት ጊዜና ጧት ወደ ግጦሽ ቦታዋ በምታሰማሯት ወቅት ለእናንተ ውበት አለላችሁ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَتَحۡمِلُ أَثۡقَالَكُمۡ إِلَىٰ بَلَدٖ لَّمۡ تَكُونُواْ بَٰلِغِيهِ إِلَّا بِشِقِّ ٱلۡأَنفُسِۚ إِنَّ رَبَّكُمۡ لَرَءُوفٞ رَّحِيمٞ
7. ጓዞቻችሁንም ነፍሶቻችሁን በማስቸገር እንጂ ወደ ማትደርሱበት አገር ትሸከማለች:: ጌታችሁ በእርግጥ ሩህሩህ እና አዛኝ ነውና::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَٱلۡخَيۡلَ وَٱلۡبِغَالَ وَٱلۡحَمِيرَ لِتَرۡكَبُوهَا وَزِينَةٗۚ وَيَخۡلُقُ مَا لَا تَعۡلَمُونَ
8. ፈረሶችን፤ በቅሎዎችንና አህዮችን ልትጋልቧቸውና ልታጌጡባቸው ፈጠረላችሁ:: የማታውቁትን ድንቅ ነገርም ወደ ፊት ይፈጥራል::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَعَلَى ٱللَّهِ قَصۡدُ ٱلسَّبِيلِ وَمِنۡهَا جَآئِرٞۚ وَلَوۡ شَآءَ لَهَدَىٰكُمۡ أَجۡمَعِينَ
9. በአላህም ላይ በችሮታው ቀጥተኛውን መንገድ መግለጽ አለበት:: ከእርሷም ጠማማ አለ:: በሻም ኖሮ ሁላችሁንም ባቀናችሁ ነበር::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
هُوَ ٱلَّذِيٓ أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗۖ لَّكُم مِّنۡهُ شَرَابٞ وَمِنۡهُ شَجَرٞ فِيهِ تُسِيمُونَ
10. እርሱ ያ ከሰማይ ውሃን ያወረደ ነው:: ከእርሱም ለእናንተ መጠጥ አለላችሁ:: ከእርሱም እንስሳዎችን በእርሱ ውስጥ የምታሰማሩበት ዛፍ ይበቅልበታል::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
يُنۢبِتُ لَكُم بِهِ ٱلزَّرۡعَ وَٱلزَّيۡتُونَ وَٱلنَّخِيلَ وَٱلۡأَعۡنَٰبَ وَمِن كُلِّ ٱلثَّمَرَٰتِۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗ لِّقَوۡمٖ يَتَفَكَّرُونَ
11. በእርሱ አዝመራን፣ የዘይት ወይራን፣ ዘምባባዎችን፣ ወይኖችንና ከፍሬዎችም ሁሉ ያበቅልላችኋል:: በዚህ ክስተት ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ሁሉ በእርግጥ ትልቅ ተዓምር አለ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَسَخَّرَ لَكُمُ ٱلَّيۡلَ وَٱلنَّهَارَ وَٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَۖ وَٱلنُّجُومُ مُسَخَّرَٰتُۢ بِأَمۡرِهِۦٓۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يَعۡقِلُونَ
12. ለእናንተ ሌሊትንና ቀንን ጸሐይንና ጨረቃንም ገራላችሁ:: ከዋክብትም በሙሉ በፈቃዱ ብቻ የተገሩ ናቸው:: በዚህ ክስተት ውስጥ ለሚያውቁ ሕዝቦች ሁሉ በእርግጥ አያሌ ተዓምራት አሉ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَمَا ذَرَأَ لَكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ مُخۡتَلِفًا أَلۡوَٰنُهُۥٓۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗ لِّقَوۡمٖ يَذَّكَّرُونَ
13. በምድርም ላይ መልኮቹ የተለያዩ ሆኖ የፈጠረላችሁን ሁሉ ገራላችሁ:: በዚህ ውስጥ ለሚገሠጹ ሕዝቦች ሁሉ ግልጽ ተዐምር አለ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَهُوَ ٱلَّذِي سَخَّرَ ٱلۡبَحۡرَ لِتَأۡكُلُواْ مِنۡهُ لَحۡمٗا طَرِيّٗا وَتَسۡتَخۡرِجُواْ مِنۡهُ حِلۡيَةٗ تَلۡبَسُونَهَاۖ وَتَرَى ٱلۡفُلۡكَ مَوَاخِرَ فِيهِ وَلِتَبۡتَغُواْ مِن فَضۡلِهِۦ وَلَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ
14. እርሱ ያ ባሕርን ከእርሱ እርጥብ ስጋን ልትበሉና ከእርሱም የምትለብሱትን ጌጣጌጥ ታወጡ ዘንድ የገራ ነው:: መርከቦችንም በውስጡ ውሃውን ቀዳጆች ሆነው ሲንሻለሉ ታያለህ:: ከችሮታው ልትፈልጉና ልታመሰግኑም ገራላችሁ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَلۡقَىٰ فِي ٱلۡأَرۡضِ رَوَٰسِيَ أَن تَمِيدَ بِكُمۡ وَأَنۡهَٰرٗا وَسُبُلٗا لَّعَلَّكُمۡ تَهۡتَدُونَ
15. በምድር ውስጥ በናንተ እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለባት። ትመሩም ዘንድ ጅረቶችንና መንገዶችን አደረገ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَعَلَٰمَٰتٖۚ وَبِٱلنَّجۡمِ هُمۡ يَهۡتَدُونَ
16. ምልክቶችንም አደረገ:: በከዋክብትም እነርሱ ይመራሉ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَفَمَن يَخۡلُقُ كَمَن لَّا يَخۡلُقُۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ
17. (ሰዎች ሆይ!) የሚፈጥር ልክ እንደማይፈጥር ነውን? አትገሠጹምን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَإِن تَعُدُّواْ نِعۡمَةَ ٱللَّهِ لَا تُحۡصُوهَآۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَغَفُورٞ رَّحِيمٞ
18. የአላህን ጸጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም:: አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَٱللَّهُ يَعۡلَمُ مَا تُسِرُّونَ وَمَا تُعۡلِنُونَ
19. አላህ የምትደብቁትንና የምትገልጹትንም ሁሉ ያውቃል::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَٱلَّذِينَ يَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ لَا يَخۡلُقُونَ شَيۡـٔٗا وَهُمۡ يُخۡلَقُونَ
20. እነዚያም ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው አማልክት ሁሉ ምንንም አይፈጥሩም:: እንዲያዉም እነርሱ ራሳቸው ይፈጠራሉ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَمۡوَٰتٌ غَيۡرُ أَحۡيَآءٖۖ وَمَا يَشۡعُرُونَ أَيَّانَ يُبۡعَثُونَ
21. እነርሱ ሕያው ያልሆኑ ሙታን ናቸው:: እራሳቸው እንኳን መቼ እንደሚቀሰቀሱ አያውቁም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِلَٰهُكُمۡ إِلَٰهٞ وَٰحِدٞۚ فَٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ قُلُوبُهُم مُّنكِرَةٞ وَهُم مُّسۡتَكۡبِرُونَ
22. አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ልቦቻቸው ከሓዲያን ናቸው:: እነርሱም የኮሩ ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لَا جَرَمَ أَنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ مَا يُسِرُّونَ وَمَا يُعۡلِنُونَۚ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلۡمُسۡتَكۡبِرِينَ
23. አላህ የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ሁሉ የሚያውቅ ለመሆኑ ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ የለበትም:: እርሱ ኩሩዎችን አይወድም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَإِذَا قِيلَ لَهُم مَّاذَآ أَنزَلَ رَبُّكُمۡ قَالُوٓاْ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ
24. ጌታችሁ በሙሐመድ ላይ ምን አወረደ በተባሉ ጊዜም: «የመጀመሪያዎቹ ሕዝቦች ተረቶችን ነው።» ይላሉ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لِيَحۡمِلُوٓاْ أَوۡزَارَهُمۡ كَامِلَةٗ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ وَمِنۡ أَوۡزَارِ ٱلَّذِينَ يُضِلُّونَهُم بِغَيۡرِ عِلۡمٍۗ أَلَا سَآءَ مَا يَزِرُونَ
25. ይህንን የሚሉት በትንሣኤ ቀን ኃጢአቶቻቸውን በሙሉና ከነዚያም ያለ ዕውቀት ሆነው ከሚያጣምሟቸው ሰዎች ኃጢአቶች ከፊሉን ሊሸከሙ ነው:: ንቁ የሚሸከሙት ኃጢአት ምንኛ ከፋ!
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
قَدۡ مَكَرَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ فَأَتَى ٱللَّهُ بُنۡيَٰنَهُم مِّنَ ٱلۡقَوَاعِدِ فَخَرَّ عَلَيۡهِمُ ٱلسَّقۡفُ مِن فَوۡقِهِمۡ وَأَتَىٰهُمُ ٱلۡعَذَابُ مِنۡ حَيۡثُ لَا يَشۡعُرُونَ
26. እነዚያ ከእነርሱ (ከቁረይሾች) በፊት የነበሩት ከሓዲያን አሴሩ:: ከዚያም አላህ ሕንጻዎቻቸውን ከመሠረቶቻቸው አፈረሰ:: እናም ጣሪያው በላያቸው ላይ ወደቀባቸው:: ቅጣቱም ከማያውቁት ስፍራ መጣባቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ثُمَّ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ يُخۡزِيهِمۡ وَيَقُولُ أَيۡنَ شُرَكَآءِيَ ٱلَّذِينَ كُنتُمۡ تُشَٰٓقُّونَ فِيهِمۡۚ قَالَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡعِلۡمَ إِنَّ ٱلۡخِزۡيَ ٱلۡيَوۡمَ وَٱلسُّوٓءَ عَلَى ٱلۡكَٰفِرِينَ
27. ከዚያም በትንሣኤ ቀን ያዋርዳቸዋል:: «እነዚያም በእነርሱ ጉዳይ ትከራከሩኝ የነበራችሁት ተጋሪዎቼ የት ናቸው?» ይላቸዋል። እነዚያ እውቀትን የተሰጡት ክፍሎች «ዛሬ ሐፍረቱና ቅጣቱ በከሓዲያን ላይ ነው።» ይላሉ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ٱلَّذِينَ تَتَوَفَّىٰهُمُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ ظَالِمِيٓ أَنفُسِهِمۡۖ فَأَلۡقَوُاْ ٱلسَّلَمَ مَا كُنَّا نَعۡمَلُ مِن سُوٓءِۭۚ بَلَىٰٓۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمُۢ بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
28. እነዚያ ነፍሶቻችውን በዳይ ሆነው መላዕክት የሚገድሏቸው «ከክፉ ሥራ ምንም ነገር የምንሠራም አልነበርንም» ሲሉ ታዛዥነታቸውን ይገልፃሉ:: «በእውነት አላህ ትሠሩት የነበራችሁትን ነገር አዋቂ ነው።» ይባላሉ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَٱدۡخُلُوٓاْ أَبۡوَٰبَ جَهَنَّمَ خَٰلِدِينَ فِيهَاۖ فَلَبِئۡسَ مَثۡوَى ٱلۡمُتَكَبِّرِينَ
29. «የገሀነምንም ደጃፎች በውስጧ ዘውታሪዎች ስትሆኑ ግቡ።» ይባላሉ:: የኩሩ ሰዎች ሁሉ መኖሪያ የሆነችው ገሀነምም በእርግጥ ከፋች!
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
۞ وَقِيلَ لِلَّذِينَ ٱتَّقَوۡاْ مَاذَآ أَنزَلَ رَبُّكُمۡۚ قَالُواْ خَيۡرٗاۗ لِّلَّذِينَ أَحۡسَنُواْ فِي هَٰذِهِ ٱلدُّنۡيَا حَسَنَةٞۚ وَلَدَارُ ٱلۡأٓخِرَةِ خَيۡرٞۚ وَلَنِعۡمَ دَارُ ٱلۡمُتَّقِينَ
30. ለእነዚያም ለተጠነቀቁት ሰዎች «ጌታችሁ ምንን ነገር አወረደ?» ተባሉ:: «መልካምን ነገር አወረደ» አሉ:: ለእነዚያ ደግ ለሠሩት ህዝቦች ሁሉ በዚህች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ኑሮ አለላቸው:: የመጨረሻይቱም አገር በእርግጥ በላጭ ናት:: የጥንቁቆቹም አገር ገነት ምን ታምር!
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
جَنَّٰتُ عَدۡنٖ يَدۡخُلُونَهَا تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُۖ لَهُمۡ فِيهَا مَا يَشَآءُونَۚ كَذَٰلِكَ يَجۡزِي ٱللَّهُ ٱلۡمُتَّقِينَ
31. እርሷም የሚገቧትና በሥርዋ ወንዞች የሚፈሱባት ስትሆን የመኖሪያ አትክልቶች (ጀነት) ናት:: ለእነርሱም በውስጧ የሚሹት ነገር ሁሉ አለላቸው:: ልክ እንደዚሁም አላህ ጥንቁቆችን ይመነዳል::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ٱلَّذِينَ تَتَوَفَّىٰهُمُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ طَيِّبِينَ يَقُولُونَ سَلَٰمٌ عَلَيۡكُمُ ٱدۡخُلُواْ ٱلۡجَنَّةَ بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
32. እነዚያ ጥሩ ሆነው መላዕክት «ሰላም ለእናንተ ይሁን" እያሉ የሚገድሏቸው "ትሠሩት በነበራችሁት ሥራ ምክንያትም ወደ ገነት ግቡ።» ይባላሉ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
هَلۡ يَنظُرُونَ إِلَّآ أَن تَأۡتِيَهُمُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ أَوۡ يَأۡتِيَ أَمۡرُ رَبِّكَۚ كَذَٰلِكَ فَعَلَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ وَمَا ظَلَمَهُمُ ٱللَّهُ وَلَٰكِن كَانُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ يَظۡلِمُونَ
33. ከሓዲያን የመላዕክትን ወደ እነርሱ መምጣት ወይም የጌታህ ትዕዛዝ መምጣቱን እንጂ ሌላን ይጠባበቃሉን? ከእነርሱ በፊት የነበሩትም ልክ እንደዚህ ሠርተዋል:: አላህም አልበደላቸዉም:: ግን እነርሱ ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَأَصَابَهُمۡ سَيِّـَٔاتُ مَا عَمِلُواْ وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ
34. እናም የሠሯቸዉም ኃጢአቶች ቅጣት አገኛቸው:: ይሳለቁበት የነበሩት ነገር ሁሉ በእነርሱ ላይ ወረደባቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَقَالَ ٱلَّذِينَ أَشۡرَكُواْ لَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ مَا عَبَدۡنَا مِن دُونِهِۦ مِن شَيۡءٖ نَّحۡنُ وَلَآ ءَابَآؤُنَا وَلَا حَرَّمۡنَا مِن دُونِهِۦ مِن شَيۡءٖۚ كَذَٰلِكَ فَعَلَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ فَهَلۡ عَلَى ٱلرُّسُلِ إِلَّا ٱلۡبَلَٰغُ ٱلۡمُبِينُ
35. እነዚያም ጣዖታትን በአላህ ያጋሩ ህዝቦች «አላህ በሻ ኖሮ ከእርሱ ሌላ እኛም ሆንን አባቶቻችን ምንንም ባልተገዛን ነበር:: ያለ እርሱም ትዕዛዝ ምንንም እርም ባላደረግን ነበር።» አሉ:: እነዚያም ከእነርሱ በፊት የነበሩት ህዝቦች ልክ እንደዚሁ ሠሩ:: በመልዕክተኞቹም ላይ ግልጽ ማድረስ ብቻ እንጂ ሌላ የለባቸዉም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلَقَدۡ بَعَثۡنَا فِي كُلِّ أُمَّةٖ رَّسُولًا أَنِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ وَٱجۡتَنِبُواْ ٱلطَّٰغُوتَۖ فَمِنۡهُم مَّنۡ هَدَى ٱللَّهُ وَمِنۡهُم مَّنۡ حَقَّتۡ عَلَيۡهِ ٱلضَّلَٰلَةُۚ فَسِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَٱنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُكَذِّبِينَ
36. በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ ጣዖትን ራቁ በማለት የሚያስተምር መልዕክተኛን ልከናል:: ከእነርሱም ውስጥ አላህ ያቀናው አለ:: ከእነርሱም ውስጥ በእርሱ ላይ ጥመት የተረጋገጠበት አለ:: እናም በምድር ላይ ሂዱ:: የአስተባባዮችም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበር ተመልከቱ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِن تَحۡرِصۡ عَلَىٰ هُدَىٰهُمۡ فَإِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي مَن يُضِلُّۖ وَمَا لَهُم مِّن نَّٰصِرِينَ
37. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመቅናታቸው ላይ ብትጓጓ (ምንም ልታደርግ አትችልም):: ምክንያቱም አላህ የሚያጠመውን አያቀናዉምና:: ለእነርሱም ከረዳቶች ምንም የላቸዉም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَقۡسَمُواْ بِٱللَّهِ جَهۡدَ أَيۡمَٰنِهِمۡ لَا يَبۡعَثُ ٱللَّهُ مَن يَمُوتُۚ بَلَىٰ وَعۡدًا عَلَيۡهِ حَقّٗا وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعۡلَمُونَ
38. ጥብቅ መሐሎቻቸውንም «አላህ የሚሞትን ሰው አያስነሳም።» ሲሉ በአላህ ስም ማሉ:: አባባላቸው ሐሰት ነው። ያስነሳቸዋል:: በእርሱ ላይ ቃል ኪዳን ገብቷል:: አረጋግጧልም:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لِيُبَيِّنَ لَهُمُ ٱلَّذِي يَخۡتَلِفُونَ فِيهِ وَلِيَعۡلَمَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ أَنَّهُمۡ كَانُواْ كَٰذِبِينَ
39. የሚቀሰቅሳቸዉም ለእነርሱ ያንን የሚለያዩበትን ሊገልጽላቸውና እነዚያ የካዱትም እነርሱ ውሸታሞች የነበሩ መሆናቸውን እንዲያውቁ ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّمَا قَوۡلُنَا لِشَيۡءٍ إِذَآ أَرَدۡنَٰهُ أَن نَّقُولَ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ
40. ለማንኛዉም ነገር መሆኑን በፈለግን ጊዜ ቃላችን ለእርሱ "ሁን" ማለት ብቻ ነው:: ወዲያዉም ይሆናል::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَٱلَّذِينَ هَاجَرُواْ فِي ٱللَّهِ مِنۢ بَعۡدِ مَا ظُلِمُواْ لَنُبَوِّئَنَّهُمۡ فِي ٱلدُّنۡيَا حَسَنَةٗۖ وَلَأَجۡرُ ٱلۡأٓخِرَةِ أَكۡبَرُۚ لَوۡ كَانُواْ يَعۡلَمُونَ
41. እነዚያም ከተበደሉ በኋላ በአላህ መንገድ ላይ የተሰደዱ በቅርቢቱ ዓለም መልካሚቱን አገር (መዲናን) እናሰፍራቸዋለን:: የመጨረሻይቱም ዓለም ምንዳ ታላቅ ነው:: (ከሓዲያን) ቢያውቁ ኖሮ (በተከተሏቸው ነበር)::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ٱلَّذِينَ صَبَرُواْ وَعَلَىٰ رَبِّهِمۡ يَتَوَكَّلُونَ
42. እነርሱ እነዚያ የታገሡና በጌታቸዉም ላይ የሚጠጉ ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَمَآ أَرۡسَلۡنَا مِن قَبۡلِكَ إِلَّا رِجَالٗا نُّوحِيٓ إِلَيۡهِمۡۖ فَسۡـَٔلُوٓاْ أَهۡلَ ٱلذِّكۡرِ إِن كُنتُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ
43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተም በፊት ወደ እነርሱ ወሕይን የምናወርድላቸውን ሰዎችን እንጂ ሌላን አልላክንም:: (ሰዎች ሆይ! ) የማታውቁም ከሆናችሁ የዕውቀትን ባለቤቶችን ጠይቁ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
بِٱلۡبَيِّنَٰتِ وَٱلزُّبُرِۗ وَأَنزَلۡنَآ إِلَيۡكَ ٱلذِّكۡرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيۡهِمۡ وَلَعَلَّهُمۡ يَتَفَكَّرُونَ
44. በግልጽ ማስረጃዎችና በመጽሐፍ ላክናቸው። ለሰዎችም ወደ እነርሱ የተወረደላቸውን ፍች ትገልጽላቸውና ያስተነትኑም ዘንድ ወደ አንተ ቁርኣንን አወረድን::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَفَأَمِنَ ٱلَّذِينَ مَكَرُواْ ٱلسَّيِّـَٔاتِ أَن يَخۡسِفَ ٱللَّهُ بِهِمُ ٱلۡأَرۡضَ أَوۡ يَأۡتِيَهُمُ ٱلۡعَذَابُ مِنۡ حَيۡثُ لَا يَشۡعُرُونَ
45. እነዚያን መጥፎዎችን የዶለቱ ሰዎች አላህ በእነርሱ ምድርን የሚያስዉጣቸው ወይም ከማያውቁት ሥፍራ ቅጣት የሚመጣባቸው መሆኑን ተማመኑን? አይፈሩምን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَوۡ يَأۡخُذَهُمۡ فِي تَقَلُّبِهِمۡ فَمَا هُم بِمُعۡجِزِينَ
46. ወይም ከአገር ወደ አገር በሚዛወሩበት ጊዜ በእንቅስቃሴ ላይ እያሉ የሚይዛቸው መሆኑን አይፈሩምን? እነርሱም አሸናፊዎች አይደሉም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَوۡ يَأۡخُذَهُمۡ عَلَىٰ تَخَوُّفٖ فَإِنَّ رَبَّكُمۡ لَرَءُوفٞ رَّحِيمٌ
47. ወይም ቀስ በቀስ በማጉደል ላይ የሚይዛቸው መሆኑን ተማመኑን? አይፈሩምን? ጌታችሁም ሩሕሩህና አዛኝ ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ إِلَىٰ مَا خَلَقَ ٱللَّهُ مِن شَيۡءٖ يَتَفَيَّؤُاْ ظِلَٰلُهُۥ عَنِ ٱلۡيَمِينِ وَٱلشَّمَآئِلِ سُجَّدٗا لِّلَّهِ وَهُمۡ دَٰخِرُونَ
48. ወደዚያ ከማንኛዉም ነገር አላህ ወደ ፈጠረው ጥላዎቹ እነርሱም የተዋረዱ ሲሆኑ ለአላህ ሰጋጆች ሆነው ከቀኝ እና ከግራዎች ወደ ሚዛወሩት አላዩምን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلِلَّهِۤ يَسۡجُدُۤ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ مِن دَآبَّةٖ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ وَهُمۡ لَا يَسۡتَكۡبِرُونَ
49. በሰማያትና በምድር ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ መላዕክትም ለአላህ ብቻ ይሰግዳሉ:: እነርሱም አይኮሩም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
يَخَافُونَ رَبَّهُم مِّن فَوۡقِهِمۡ وَيَفۡعَلُونَ مَا يُؤۡمَرُونَ۩
50. ጌታቸውን ከበላያቸው ሲሆን ይፈሩታል:: የታዘዙትንም ሁሉ ይሰራሉ (ይፈጽማሉ):: {1}
{1} አዚህ የንባብ ሱጁድ (ሱጁድ አትላዋ) ይደረጋል።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
۞ وَقَالَ ٱللَّهُ لَا تَتَّخِذُوٓاْ إِلَٰهَيۡنِ ٱثۡنَيۡنِۖ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٞ وَٰحِدٞ فَإِيَّٰيَ فَٱرۡهَبُونِ
51. አላህም አለ: «ሁለት አማልክት አትያዙ እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: እኔን ብቻ ፍሩኝ።»
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلَهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَلَهُ ٱلدِّينُ وَاصِبًاۚ أَفَغَيۡرَ ٱللَّهِ تَتَّقُونَ
52. በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: አምልኮም ዘወትር ለርሱ ብቻ ነው:: ከአላህ ሌላ ያለን ትፈራላችሁን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَمَا بِكُم مِّن نِّعۡمَةٖ فَمِنَ ٱللَّهِۖ ثُمَّ إِذَا مَسَّكُمُ ٱلضُّرُّ فَإِلَيۡهِ تَجۡـَٔرُونَ
53. ማንኛዉም በናንተ ላይ ያለው ጸጋ ከአላህ ብቻ ነው። ከዚያም ችግር በደረሰባችሁ ጊዜ ወደ እርሱ ብቻ ትጮሀላችሁ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ثُمَّ إِذَا كَشَفَ ٱلضُّرَّ عَنكُمۡ إِذَا فَرِيقٞ مِّنكُم بِرَبِّهِمۡ يُشۡرِكُونَ
54. ከዚያም ከናንተ ላይ ችግርን ባነሳላችሁ ጊዜ ከናንተ የሆኑ ቡድኖች ወዲያውኑ በጌታችሁ ጣዖትን ያጋራሉ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لِيَكۡفُرُواْ بِمَآ ءَاتَيۡنَٰهُمۡۚ فَتَمَتَّعُواْ فَسَوۡفَ تَعۡلَمُونَ
55. የሚያጋሩትም በሰጠናቸው ሊክዱ ነው:: ተጠቀሙም ወደፊትም የሚደርስባቸውን ታውቃላችሁ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَيَجۡعَلُونَ لِمَا لَا يَعۡلَمُونَ نَصِيبٗا مِّمَّا رَزَقۡنَٰهُمۡۗ تَٱللَّهِ لَتُسۡـَٔلُنَّ عَمَّا كُنتُمۡ تَفۡتَرُونَ
56. ለማያውቁት ጣዖታትም ከሰጠናቸው ሲሳይ ድርሻን ያደርጋሉ:: በአላህ እምላለሁ ትቀጣጥፉት ከነበራችሁት ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَيَجۡعَلُونَ لِلَّهِ ٱلۡبَنَٰتِ سُبۡحَٰنَهُۥ وَلَهُم مَّا يَشۡتَهُونَ
57. ለአላህ ሴቶች ልጆችን ያደርጋሉ። ጥራት ይገባው። ለእነርሱ ግን የሚፈልጉትን ያደርጋሉ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَإِذَا بُشِّرَ أَحَدُهُم بِٱلۡأُنثَىٰ ظَلَّ وَجۡهُهُۥ مُسۡوَدّٗا وَهُوَ كَظِيمٞ
58. ከመሀከላቸው አንዱ በሴት ልጅ (መወለድ) በተበሰረ ጊዜ እርሱ የተቆጨ ሆኖ ፊቱ ጠቁሮ ቅስሙ ይሰበራል።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
يَتَوَٰرَىٰ مِنَ ٱلۡقَوۡمِ مِن سُوٓءِ مَا بُشِّرَ بِهِۦٓۚ أَيُمۡسِكُهُۥ عَلَىٰ هُونٍ أَمۡ يَدُسُّهُۥ فِي ٱلتُّرَابِۗ أَلَا سَآءَ مَا يَحۡكُمُونَ
59. ከተበሰረበት ነገር መጥፎነት በውርደት ላይ ሆኖም ቢሆን ይያዘውን? ወይስ በአፈር ውስጥ ይደብቀውን? በማለት እያምታታ ከሰዎች ይደበቃል:: የሚፈርዱት ፍርድ ምንኛ ከፋ!
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لِلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ مَثَلُ ٱلسَّوۡءِۖ وَلِلَّهِ ٱلۡمَثَلُ ٱلۡأَعۡلَىٰۚ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ
60. ለእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም ለማያምኑት ሰዎች ሁሉ መጥፎ መገለጫ አላቸው:: ለአላህ ግን ታላቅ መገለጫ አለው:: እርሱም ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلَوۡ يُؤَاخِذُ ٱللَّهُ ٱلنَّاسَ بِظُلۡمِهِم مَّا تَرَكَ عَلَيۡهَا مِن دَآبَّةٖ وَلَٰكِن يُؤَخِّرُهُمۡ إِلَىٰٓ أَجَلٖ مُّسَمّٗىۖ فَإِذَا جَآءَ أَجَلُهُمۡ لَا يَسۡتَـٔۡخِرُونَ سَاعَةٗ وَلَا يَسۡتَقۡدِمُونَ
61. አላህም ሰዎችን በበደላቸው ሁሉ በቀጣቸው ኖሮ በምድር ላይ ከተንቀሳቃሽ ምንንም ባላስቀረ ነበር:: ግን እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ ያቆያቸዋል:: ጊዜያቸዉም በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይዘገዩም፤ አይቀድሙም።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَيَجۡعَلُونَ لِلَّهِ مَا يَكۡرَهُونَۚ وَتَصِفُ أَلۡسِنَتُهُمُ ٱلۡكَذِبَ أَنَّ لَهُمُ ٱلۡحُسۡنَىٰۚ لَا جَرَمَ أَنَّ لَهُمُ ٱلنَّارَ وَأَنَّهُم مُّفۡرَطُونَ
62. ለአላህም የሚጠሉትን ነገር ያደርጋሉ:: ለእነርሱም መልካሚቱ (ሀገር) እንዳለቻቸው በምላሶቻቸው ውሸትን ይናገራሉ:: ለእነርሱም እሳት ያለቻቸው መሆናቸውና እነርሱም ወደ እርሷ በቅድሚያ የሚነዱ መሆናቸው ጥርጥር የለበትም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
تَٱللَّهِ لَقَدۡ أَرۡسَلۡنَآ إِلَىٰٓ أُمَمٖ مِّن قَبۡلِكَ فَزَيَّنَ لَهُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ أَعۡمَٰلَهُمۡ فَهُوَ وَلِيُّهُمُ ٱلۡيَوۡمَ وَلَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ
63. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ እንምላለን ካንተ በፊት ወደ ነበሩት ሕዝቦች በእርግጥ ብዙ መልዕክተኞችን ልከናል:: ሰይጣንም ለእነርሱ ስራዎቻቸውን ሸለመላቸው:: ረዳታቸው ዛሬም እርሱ ነው:: ለእነርሱም ኋላ አሳማሚ ቅጣት አላቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَمَآ أَنزَلۡنَا عَلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ إِلَّا لِتُبَيِّنَ لَهُمُ ٱلَّذِي ٱخۡتَلَفُواْ فِيهِ وَهُدٗى وَرَحۡمَةٗ لِّقَوۡمٖ يُؤۡمِنُونَ
64. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንን በእርሱ የተለያዩበትን ለእነርሱ ልታብራራላቸውና ለሚያምኑትም ህዝቦች መሪና እዝነት ሊሆን እንጂ ባንተ ላይ መፅሀፉን አላወረድንም።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَٱللَّهُ أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَأَحۡيَا بِهِ ٱلۡأَرۡضَ بَعۡدَ مَوۡتِهَآۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗ لِّقَوۡمٖ يَسۡمَعُونَ
65. አላህ ከሰማይ ውሃን አወረደ:: በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ህያው አደረገ:: በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ህዝቦች በእርግጥ ተዓምር አለ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَإِنَّ لَكُمۡ فِي ٱلۡأَنۡعَٰمِ لَعِبۡرَةٗۖ نُّسۡقِيكُم مِّمَّا فِي بُطُونِهِۦ مِنۢ بَيۡنِ فَرۡثٖ وَدَمٖ لَّبَنًا خَالِصٗا سَآئِغٗا لِّلشَّٰرِبِينَ
66. (ሰዎች ሆይ!) ለእናንተ በግመል በከብት በፍየል አፈጣጠር አያሌ ምክር ሰጪ ትምህርት አለላችሁ:: በሆዶች ውስጥ ካለው ከፈርስና ከደም መካከል ጥሩ ወተትን ለጠጪዎች ጣፋጭ ሲሆን እናጠጣችኋለን::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَمِن ثَمَرَٰتِ ٱلنَّخِيلِ وَٱلۡأَعۡنَٰبِ تَتَّخِذُونَ مِنۡهُ سَكَرٗا وَرِزۡقًا حَسَنًاۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗ لِّقَوۡمٖ يَعۡقِلُونَ
67. ከዘንባባዎች ከወይኖችም ፍሬዎች እንመግባችኋለን፤ ከእርሱ ጠጅንና መልካም ምግብንም ትሰራላችሁ (ታዘጋጃላችሁ):: በዚህም ውስጥ ለሚያስቡ ህዝቦች በእርግጥ ተዓምር አለ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَوۡحَىٰ رَبُّكَ إِلَى ٱلنَّحۡلِ أَنِ ٱتَّخِذِي مِنَ ٱلۡجِبَالِ بُيُوتٗا وَمِنَ ٱلشَّجَرِ وَمِمَّا يَعۡرِشُونَ
68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም ወደ ንብ እንዲህ ሲል (አስታወቀ) አስተማረ፡ «ከተራራዎች ከዛፍና ሰዎች ከሚሠሩት ቀፎ ቤቶችን ያዢ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ثُمَّ كُلِي مِن كُلِّ ٱلثَّمَرَٰتِ فَٱسۡلُكِي سُبُلَ رَبِّكِ ذُلُلٗاۚ يَخۡرُجُ مِنۢ بُطُونِهَا شَرَابٞ مُّخۡتَلِفٌ أَلۡوَٰنُهُۥ فِيهِ شِفَآءٞ لِّلنَّاسِۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗ لِّقَوۡمٖ يَتَفَكَّرُونَ
69. «ከዚያም ከፍሬዎች ሁሉ ብይ የጌታሽንም መንገዶች ለአንቺ የተገሩ ሲሆኑ ግቢ።» ከሆዶቿ መልኮቹ የተለያዩ መጠጥ ይወጣል:: በእርሱ ውስጥ ለሰዎች ፍቱን መድሀኒት አለበት። በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ህዝቦች ተዓምር አለበት::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَٱللَّهُ خَلَقَكُمۡ ثُمَّ يَتَوَفَّىٰكُمۡۚ وَمِنكُم مَّن يُرَدُّ إِلَىٰٓ أَرۡذَلِ ٱلۡعُمُرِ لِكَيۡ لَا يَعۡلَمَ بَعۡدَ عِلۡمٖ شَيۡـًٔاۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٞ قَدِيرٞ
70. አላህም ፈጠራችሁ ከዚያ ይገድላችኋል:: ከናንተም መካከል ከእውቀት በኋላ ምንንም ነገር የማያውቅ ወደሚሆንበት የጃጀ እድሜ የሚመለስም ሰው አለ:: አላህ ሁሉን አዋቂ፤ በሁሉም ነገር ላይ ቻይም ነው።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَٱللَّهُ فَضَّلَ بَعۡضَكُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖ فِي ٱلرِّزۡقِۚ فَمَا ٱلَّذِينَ فُضِّلُواْ بِرَآدِّي رِزۡقِهِمۡ عَلَىٰ مَا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُهُمۡ فَهُمۡ فِيهِ سَوَآءٌۚ أَفَبِنِعۡمَةِ ٱللَّهِ يَجۡحَدُونَ
71. አላህ ከፊላችሁን በከፊሉ ላይ በሲሳይ አበለጠ:: እነዚያም በላጭ የተደረጉት ሲሳያቸውን እጆቻቸው በያዟቸው ባሮች ላይ እነርሱ በእርሱ ይስተካከሉ ዘንድ መላሾች አይደሉም:: ታዲያ በአላህ ጸጋ ለእርሱ ተጋሪ በማድረግ ይክዳሉን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَٱللَّهُ جَعَلَ لَكُم مِّنۡ أَنفُسِكُمۡ أَزۡوَٰجٗا وَجَعَلَ لَكُم مِّنۡ أَزۡوَٰجِكُم بَنِينَ وَحَفَدَةٗ وَرَزَقَكُم مِّنَ ٱلطَّيِّبَٰتِۚ أَفَبِٱلۡبَٰطِلِ يُؤۡمِنُونَ وَبِنِعۡمَتِ ٱللَّهِ هُمۡ يَكۡفُرُونَ
72. አላህ ከነፍሶቻችሁ (ከጎሳዎቻችሁ) ለእናንተ ሚስቶችን አደረገ (የትዳር አጋሮችን ፈጠረ)፤ ለእናንተም ከሚስቶቻችሁ ወንዶች ልጆችን የልጅ ልጆችንም አደረገላችሁ:: ከመልካሞችም ጸጋዎች ሰጣችሁ:: ታዲያ በውሸት በጣኦት አምነው በአላህ ጸጋ ይክዳሉን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَيَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَمۡلِكُ لَهُمۡ رِزۡقٗا مِّنَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ شَيۡـٔٗا وَلَا يَسۡتَطِيعُونَ
73. ከአላህም ሌላ ከሰማያትና ከምድር ምንንም ሲሳይ የማይሰጧቸውንና ምንንም የማይችሉትን እነርሱ ያመልካሉን::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَلَا تَضۡرِبُواْ لِلَّهِ ٱلۡأَمۡثَالَۚ إِنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ وَأَنتُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ
74. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለአላህ አምሳያዎችን አታድርጉ:: አላህ ያውቃል፤ እናንተ ግን አታውቁም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
۞ ضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلًا عَبۡدٗا مَّمۡلُوكٗا لَّا يَقۡدِرُ عَلَىٰ شَيۡءٖ وَمَن رَّزَقۡنَٰهُ مِنَّا رِزۡقًا حَسَنٗا فَهُوَ يُنفِقُ مِنۡهُ سِرّٗا وَجَهۡرًاۖ هَلۡ يَسۡتَوُۥنَۚ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِۚ بَلۡ أَكۡثَرُهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ
75. በምንም ላይ የማይችል ሆኖ በይዞታ (አለቃ ያለበት) የሆነውን ባሪያና መልካም ሲሳይን ሰጥተነው እርሱም ከእርሱ ከሰጠነው በሚስጥርና በግልጽ የሚለግሰውን ነፃ ሰው አላህ ለጣኦትና ለእርሱ ምሳሌ አደረገ:: ሁለቱ ይስተካከላሉን? ምስጋና ሁሉ ለአላህ ይሁን:: በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلٗا رَّجُلَيۡنِ أَحَدُهُمَآ أَبۡكَمُ لَا يَقۡدِرُ عَلَىٰ شَيۡءٖ وَهُوَ كَلٌّ عَلَىٰ مَوۡلَىٰهُ أَيۡنَمَا يُوَجِّههُّ لَا يَأۡتِ بِخَيۡرٍ هَلۡ يَسۡتَوِي هُوَ وَمَن يَأۡمُرُ بِٱلۡعَدۡلِ وَهُوَ عَلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ
76. አላህ ሁለትን ወንዶች (ለከሓዲያንና ለአማኞች) ምሳሌ አደረገ:: አንደኛቸው በምንም ነገር ላይ የማይችል ዲዳ ነው:: እርሱም በጌታው ላይ ሸክም ነው:: ወደ የትም ቢያዞረው ደግ ነገር አያመጣም:: እርሱና ያ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ሆኖ በማስተካከል (ፍትህ) የሚያዘው ሰው ይስተካከላሉን?
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلِلَّهِ غَيۡبُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَمَآ أَمۡرُ ٱلسَّاعَةِ إِلَّا كَلَمۡحِ ٱلۡبَصَرِ أَوۡ هُوَ أَقۡرَبُۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ
77. በሰማያትና በምድር ያለው ሩቅ ምስጢር የአላህ ብቻ ነው:: የሰዓቲቱም ነገር መምጣቷ እንደ ዓይን ቅጽበት እንጂ አይደለም:: ወይም ይበልጥ የቀረበ ነው:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَٱللَّهُ أَخۡرَجَكُم مِّنۢ بُطُونِ أُمَّهَٰتِكُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ شَيۡـٔٗا وَجَعَلَ لَكُمُ ٱلسَّمۡعَ وَٱلۡأَبۡصَٰرَ وَٱلۡأَفۡـِٔدَةَ لَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ
78. አላህ ከእናቶቻችሁ ሆዶች ምንም የማታውቁ ሆናችሁ አወጣችሁ:: ታመሰግኑ ዘንድም ለእናንተ መስሚያንና ማያዎችን ልቦችንም አደረገላችሁ (ፈጠረላችሁ)::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَلَمۡ يَرَوۡاْ إِلَى ٱلطَّيۡرِ مُسَخَّرَٰتٖ فِي جَوِّ ٱلسَّمَآءِ مَا يُمۡسِكُهُنَّ إِلَّا ٱللَّهُۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يُؤۡمِنُونَ
79. ወደ በራሪዎችም በሰማይ አየር ውስጥ ለመብረር የተገሩ ሲሆኑ ከመውደቅ አላህ እንጂ ሌላ የማይዛቸው መሆናቸውን አይመለከቱምን? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ተዓምራት አሉ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَٱللَّهُ جَعَلَ لَكُم مِّنۢ بُيُوتِكُمۡ سَكَنٗا وَجَعَلَ لَكُم مِّن جُلُودِ ٱلۡأَنۡعَٰمِ بُيُوتٗا تَسۡتَخِفُّونَهَا يَوۡمَ ظَعۡنِكُمۡ وَيَوۡمَ إِقَامَتِكُمۡ وَمِنۡ أَصۡوَافِهَا وَأَوۡبَارِهَا وَأَشۡعَارِهَآ أَثَٰثٗا وَمَتَٰعًا إِلَىٰ حِينٖ
80. አላህም ከቤቶቻችሁ ለእናንተ መርጊያን (ማረፊያን) አደረገላችሁ (ፈጠረላችሁ):: ከእንስሳዎችም ቆዳዎችን በጉዟችሁ ቀንም ሆነ በመቀመጫችሁ ቀን የምታቀሏቸውን ቤቶች (ዳሶች) ለእናንተ ፈጠረላችሁ:: ከበጓ ሱፎች፣ ከግመሏም ጠጉሮች፣ ከፍየሏም ጠጉሮች የቤት እቃዎችን እስከ ጊዜም ድረስ መጠቃቀሚያን አደረገላችሁ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَٱللَّهُ جَعَلَ لَكُم مِّمَّا خَلَقَ ظِلَٰلٗا وَجَعَلَ لَكُم مِّنَ ٱلۡجِبَالِ أَكۡنَٰنٗا وَجَعَلَ لَكُمۡ سَرَٰبِيلَ تَقِيكُمُ ٱلۡحَرَّ وَسَرَٰبِيلَ تَقِيكُم بَأۡسَكُمۡۚ كَذَٰلِكَ يُتِمُّ نِعۡمَتَهُۥ عَلَيۡكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تُسۡلِمُونَ
81. አላህ ከፈጠረው ነገር ለእናንተ ጥላዎችን ፈጠረላችሁ:: ከጋራዎችም መከለያዎችን ፈጠረላችሁ:: ሐሩርንም ብርድንም የሚጠብቋችሁን ልብሶች፤ የጦራችሁንም አደጋ የሚጠብቋችሁን ጥሩሮች ፈጠረላችሁ:: ልክ እንደዚሁ ትሰልሙ ዘንድ ጸጋውን በእናንተ ላይ ይሞላል::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَإِن تَوَلَّوۡاْ فَإِنَّمَا عَلَيۡكَ ٱلۡبَلَٰغُ ٱلۡمُبِينُ
82. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከኢስላም ቢሸሹም ባንተ ላይ ያለብህ ግልጽ ማድረስ ብቻ ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
يَعۡرِفُونَ نِعۡمَتَ ٱللَّهِ ثُمَّ يُنكِرُونَهَا وَأَكۡثَرُهُمُ ٱلۡكَٰفِرُونَ
83. የአላህን ጸጋ ያውቃሉ:: ሆኖም ከዚያ ይክዷታል:: አብዛኞቻቸዉም ከሓዲያን ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَيَوۡمَ نَبۡعَثُ مِن كُلِّ أُمَّةٖ شَهِيدٗا ثُمَّ لَا يُؤۡذَنُ لِلَّذِينَ كَفَرُواْ وَلَا هُمۡ يُسۡتَعۡتَبُونَ
84. ከየህዝቡም ሁሉ መስካሪን የምንቀሰቅስበትን ቀን አስታውስ:: ከዚያ ለእነዚያ ለካዱት ንግግር አይፈቀድላቸዉም:: እነርሱም በወቀሳ አይታለፉም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَإِذَا رَءَا ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ ٱلۡعَذَابَ فَلَا يُخَفَّفُ عَنۡهُمۡ وَلَا هُمۡ يُنظَرُونَ
85. እነዚያ የበደሉ ሰዎች ቅጣትን ባዩ ጊዜ ለእነርሱ አይቃለልላቸዉም:: ጊዜም አይሰጣቸዉም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَإِذَا رَءَا ٱلَّذِينَ أَشۡرَكُواْ شُرَكَآءَهُمۡ قَالُواْ رَبَّنَا هَٰٓؤُلَآءِ شُرَكَآؤُنَا ٱلَّذِينَ كُنَّا نَدۡعُواْ مِن دُونِكَۖ فَأَلۡقَوۡاْ إِلَيۡهِمُ ٱلۡقَوۡلَ إِنَّكُمۡ لَكَٰذِبُونَ
86. እነዚያ በአላህ ያጋሩት ሰዎች ተጋሪዎቻቸውን ባዩ ጊዜ «ጌታችን ሆይ! እነዚህ ካንተ ሌላ እናመልካቸው የነበሩ ተጋሪዎቻችን ናቸው።» ይላሉ። አማልክቶችም «ውሸታሞች ናችሁ።» በማለት ቃሉን ወደ እነርሱው መልሰው ይወረውራሉ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَلۡقَوۡاْ إِلَى ٱللَّهِ يَوۡمَئِذٍ ٱلسَّلَمَۖ وَضَلَّ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَفۡتَرُونَ
87. አጋሪዎቹ በዚያ ቀንም ታዛዥነታቸውን ወደ አላህ ያቀርባሉ:: ይቀጣጥፉት የነበሩትም ሁሉ ከእነርሱ ይጠፋባቸዋል::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَصَدُّواْ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ زِدۡنَٰهُمۡ عَذَابٗا فَوۡقَ ٱلۡعَذَابِ بِمَا كَانُواْ يُفۡسِدُونَ
88. እነዚያ በአላህ የካዱና ከአላህ መንገድ የከለከሉ ያጠፉ በነበሩት ምክንያት ቅጣትን በቅጣት ላይ ጨመርንባቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَيَوۡمَ نَبۡعَثُ فِي كُلِّ أُمَّةٖ شَهِيدًا عَلَيۡهِم مِّنۡ أَنفُسِهِمۡۖ وَجِئۡنَا بِكَ شَهِيدًا عَلَىٰ هَٰٓؤُلَآءِۚ وَنَزَّلۡنَا عَلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ تِبۡيَٰنٗا لِّكُلِّ شَيۡءٖ وَهُدٗى وَرَحۡمَةٗ وَبُشۡرَىٰ لِلۡمُسۡلِمِينَ
89. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በየህዝቡ ሁሉ ውስጥ ከጎሳቸው በራሳቸው ላይ መስካሪን የምንቀሰቅስበትንና አንተንም በእነዚህ ሕዝቦች ላይ መስካሪ አድርገን የምናመጣብህን ቀን አስታውስ:: መጽሐፉንም ለሁሉም ነገር አብራሪ፤ መመሪያ፣ እዝነትና ለሙስሊሞች አብሳሪ ሆኖ ባንተ ላይ አወረድነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
۞ إِنَّ ٱللَّهَ يَأۡمُرُ بِٱلۡعَدۡلِ وَٱلۡإِحۡسَٰنِ وَإِيتَآيِٕ ذِي ٱلۡقُرۡبَىٰ وَيَنۡهَىٰ عَنِ ٱلۡفَحۡشَآءِ وَٱلۡمُنكَرِ وَٱلۡبَغۡيِۚ يَعِظُكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تَذَكَّرُونَ
90. አላህ በማስተካከል (በፍትህ) ፤ በማሳመር (በመልካም ሥራ) እና ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል። ከአስከፊ (ጸያፍ ነገር) ከማመንዘር፤ ከሚጠላ ነገር ሁሉ ከመበደልም ይከለክላል:: ትገነዘቡ ዘንድ ይገሥጻችኋል::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَوۡفُواْ بِعَهۡدِ ٱللَّهِ إِذَا عَٰهَدتُّمۡ وَلَا تَنقُضُواْ ٱلۡأَيۡمَٰنَ بَعۡدَ تَوۡكِيدِهَا وَقَدۡ جَعَلۡتُمُ ٱللَّهَ عَلَيۡكُمۡ كَفِيلًاۚ إِنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ مَا تَفۡعَلُونَ
91. (ሙስሊሞች ሆይ!) ቃል ኪዳን በገባችሁ ጊዜ በአላህ ቃል ኪዳን ሙሉ:: መሓሎቻችሁንም ከአጠነከራችኋት በኋላና አላህን በእናንተ ላይ መስካሪ ያደረጋችሁ ስትሆኑ አታፍርሱ:: አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ያውቃልና::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلَا تَكُونُواْ كَٱلَّتِي نَقَضَتۡ غَزۡلَهَا مِنۢ بَعۡدِ قُوَّةٍ أَنكَٰثٗا تَتَّخِذُونَ أَيۡمَٰنَكُمۡ دَخَلَۢا بَيۡنَكُمۡ أَن تَكُونَ أُمَّةٌ هِيَ أَرۡبَىٰ مِنۡ أُمَّةٍۚ إِنَّمَا يَبۡلُوكُمُ ٱللَّهُ بِهِۦۚ وَلَيُبَيِّنَنَّ لَكُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ مَا كُنتُمۡ فِيهِ تَخۡتَلِفُونَ
92. ቃል ኪዳናችሁን በማፍረስ አንዲቱ ሕዝብ ከሌላይቱ ሕዝብ የበዛች ለመሆንዋ በመካከላችሁ መሓሎቻችሁን ለክዳት መግቢያ አድርጋችሁ የምትይዙ ስትሆኑ እንደዚያች ፈትሏን ከጠነከረ በኋላ ትርትሮች አድርጋ እንዳፈረሰችው ሴት አትሁኑ:: አላህ በእርሱ ይሞክራችኋል፤ በትንሣኤ ቀንም ትለያዩበት የነበራችሁትን ነገር በእርግጥ ያብራራላችኋል::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ لَجَعَلَكُمۡ أُمَّةٗ وَٰحِدَةٗ وَلَٰكِن يُضِلُّ مَن يَشَآءُ وَيَهۡدِي مَن يَشَآءُۚ وَلَتُسۡـَٔلُنَّ عَمَّا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
93. አላህ በፈለገ ኖሮ አንዲት ሕዝብ ባደረጋችሁ ነበር:: ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያጠማል:: የሚሻውን ሰው ያቀናል:: ትሠሩት ከነበራችሁት ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلَا تَتَّخِذُوٓاْ أَيۡمَٰنَكُمۡ دَخَلَۢا بَيۡنَكُمۡ فَتَزِلَّ قَدَمُۢ بَعۡدَ ثُبُوتِهَا وَتَذُوقُواْ ٱلسُّوٓءَ بِمَا صَدَدتُّمۡ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ وَلَكُمۡ عَذَابٌ عَظِيمٞ
94. ጫማዎች ከተደላደሉ በኋላ እንዳያንዳልጡ ከአላህ መንገድ በመከልከላችሁ ምክንያት ቅጣትንም እንዳትቀምሱ መሓሎቻችሁን በመካከላችሁ ለክዳት መግቢያ አታድርጉት:: ለእናንተም ያን ጊዜ ታላቅ ቅጣት አላችሁ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلَا تَشۡتَرُواْ بِعَهۡدِ ٱللَّهِ ثَمَنٗا قَلِيلًاۚ إِنَّمَا عِندَ ٱللَّهِ هُوَ خَيۡرٞ لَّكُمۡ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ
95. በአላህ ቃል ኪዳን ጥቂትን ዋጋ አትግዙ። የምታውቁ ብትሆኑ አላህ ዘንድ ያለው ምንዳ እርሱ ለእናንተ በላጭ ነውና::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
مَا عِندَكُمۡ يَنفَدُ وَمَا عِندَ ٱللَّهِ بَاقٖۗ وَلَنَجۡزِيَنَّ ٱلَّذِينَ صَبَرُوٓاْ أَجۡرَهُم بِأَحۡسَنِ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
96. እናንተ ዘንድ ያለው ሁሉ ያልቃል:: አላህ ዘንድ ያለው ግን ለዘለዓለም ቀሪ ነው (አያልቅም):: እነዚያንም የታገሡትን ይሠሩት በነበሩት በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
مَنۡ عَمِلَ صَٰلِحٗا مِّن ذَكَرٍ أَوۡ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤۡمِنٞ فَلَنُحۡيِيَنَّهُۥ حَيَوٰةٗ طَيِّبَةٗۖ وَلَنَجۡزِيَنَّهُمۡ أَجۡرَهُم بِأَحۡسَنِ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
97. ከወንድም ይሁን ከሴት እርሱ አማኝ ሆኖ በጎን የሠራ ሁሉ መልካም ኑሮን እናኖረዋለን:: ይሠሩት ከነበሩት ነገር በመልካሙም ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَإِذَا قَرَأۡتَ ٱلۡقُرۡءَانَ فَٱسۡتَعِذۡ بِٱللَّهِ مِنَ ٱلشَّيۡطَٰنِ ٱلرَّجِيمِ
98. ቁርኣንንም ለማንበብ ባሰብክ ጊዜ እርጉም ከሆነው ሰይጣን በአላህ ተጠበቅ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّهُۥ لَيۡسَ لَهُۥ سُلۡطَٰنٌ عَلَى ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَلَىٰ رَبِّهِمۡ يَتَوَكَّلُونَ
99. እርሱ በእነዚያ በትክክል ባመኑትና በጌታቸው ላይ በሚጠጉት ላይ ለእርሱ ሥልጣን የለዉምና::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّمَا سُلۡطَٰنُهُۥ عَلَى ٱلَّذِينَ يَتَوَلَّوۡنَهُۥ وَٱلَّذِينَ هُم بِهِۦ مُشۡرِكُونَ
100. ሥልጣኑ በእነዚያ በሚታዘዙት ላይና በእነዚያም እነርሱ በእርሱ ምክንያት አጋሪዎች በሆኑት ላይ ብቻ ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَإِذَا بَدَّلۡنَآ ءَايَةٗ مَّكَانَ ءَايَةٖ وَٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِمَا يُنَزِّلُ قَالُوٓاْ إِنَّمَآ أَنتَ مُفۡتَرِۭۚ بَلۡ أَكۡثَرُهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ
101. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአንቀጽም ስፍራ ሌላ አንቀጽን በለወጥን ጊዜ አላህም የሚያወርደውን ነገር አዋቂ ነው:: «አንተ ቀጣፊ እንጂ ሌላ አይደለህም።» ይላሉ:: በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
قُلۡ نَزَّلَهُۥ رُوحُ ٱلۡقُدُسِ مِن رَّبِّكَ بِٱلۡحَقِّ لِيُثَبِّتَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَهُدٗى وَبُشۡرَىٰ لِلۡمُسۡلِمِينَ
102. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያን ያመኑትን ሰዎች ለማረጋጋት ሙስሊሞቹንም ለመምራትና ለማብሰር ቁርኣንን ጂብሪል እውነተኛ ሲሆን ከጌታህ አወረደው።» በላቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلَقَدۡ نَعۡلَمُ أَنَّهُمۡ يَقُولُونَ إِنَّمَا يُعَلِّمُهُۥ بَشَرٞۗ لِّسَانُ ٱلَّذِي يُلۡحِدُونَ إِلَيۡهِ أَعۡجَمِيّٞ وَهَٰذَا لِسَانٌ عَرَبِيّٞ مُّبِينٌ
103. እነርሱም «እርሱን ቁርኣንን የሚያስተምረው ሰው ብቻ ነው።» ማለታቸውን በእርግጥ እናውቃለን:: የዚያ ወደ እርሱ የሚያስጠጉበት ሰው ቋንቋ ዐረበኛ ያልሆነ ዐጀምኛ ነው:: ይህ ቁርኣን ግን በግልጽ በዐረብኛ ቋንቋ የተነገረ ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ لَا يَهۡدِيهِمُ ٱللَّهُ وَلَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٌ
104. እነዚያን በአላህ አናቅጽ የማያምኑትን አላህ አይመራቸዉም:: ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّمَا يَفۡتَرِي ٱلۡكَذِبَ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡكَٰذِبُونَ
105. ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አናቅጽ የማያምኑት ብቻ ናቸው:: እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
مَن كَفَرَ بِٱللَّهِ مِنۢ بَعۡدِ إِيمَٰنِهِۦٓ إِلَّا مَنۡ أُكۡرِهَ وَقَلۡبُهُۥ مُطۡمَئِنُّۢ بِٱلۡإِيمَٰنِ وَلَٰكِن مَّن شَرَحَ بِٱلۡكُفۡرِ صَدۡرٗا فَعَلَيۡهِمۡ غَضَبٞ مِّنَ ٱللَّهِ وَلَهُمۡ عَذَابٌ عَظِيمٞ
106. ከእምነቱ በኋላ በአላህ የካደ ሰው ብርቱ ቅጣት አለው። ልቡ በእምነት የረካ ሆኖ በክሕደት ቃል ለመናገር የተገደደ ሰው ብቻ ሲቀር:: ግን ልባቸውን በክሕደት የከፈቱ ሰዎች ከአላህ ቁጣ አለባቸው:: ለእነርሱም ታላቅ ቅጣት አላቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمُ ٱسۡتَحَبُّواْ ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَا عَلَى ٱلۡأٓخِرَةِ وَأَنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلۡكَٰفِرِينَ
107. ይህ ቅጣት እነርሱ ቅርቢቱን ሕይወት ከመጨረሻይቱ በመምረጣቸው ምክንያትና አላህም ከሓዲያንን ሕዝቦች የማያቀና በመሆኑ ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ طَبَعَ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ وَسَمۡعِهِمۡ وَأَبۡصَٰرِهِمۡۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡغَٰفِلُونَ
108. እነዚያ እነርሱ በልቦቻቸው፤ በዓይኖቻቸውና በጆሮቻቸዉም ላይ አላህ ያተመባቸው ናቸው:: እነዚያም ዝንጉዎቹ እነርሱ ብቻ ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لَا جَرَمَ أَنَّهُمۡ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ هُمُ ٱلۡخَٰسِرُونَ
109. እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ከሳሪዎቹ እነርሱ ለመሆናቸው ጥርጥር የለም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ثُمَّ إِنَّ رَبَّكَ لِلَّذِينَ هَاجَرُواْ مِنۢ بَعۡدِ مَا فُتِنُواْ ثُمَّ جَٰهَدُواْ وَصَبَرُوٓاْ إِنَّ رَبَّكَ مِنۢ بَعۡدِهَا لَغَفُورٞ رَّحِيمٞ
110. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዚያም ጌታህ ለእነዚያ ከተፈተኑ በኋላ ለተሰደዱት ከዚያም ለታገሉትና ለታገሡት ሁሉ ጌታህም ከፈተናዋ በኋላ በእርግጥ መሐሪና አዛኝ ነው።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
۞ يَوۡمَ تَأۡتِي كُلُّ نَفۡسٖ تُجَٰدِلُ عَن نَّفۡسِهَا وَتُوَفَّىٰ كُلُّ نَفۡسٖ مَّا عَمِلَتۡ وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ
111. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነፍስ ሁሉ ከራሷ ላይ የምትከራከር ሆና የምትመጣበትን ነፍስም ሁሉ የሠራችውን ዋጋ የምትቀበልበትን ቀን (አስታውስ):: እነርሱም ፈጹሞ አይበደሉም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلٗا قَرۡيَةٗ كَانَتۡ ءَامِنَةٗ مُّطۡمَئِنَّةٗ يَأۡتِيهَا رِزۡقُهَا رَغَدٗا مِّن كُلِّ مَكَانٖ فَكَفَرَتۡ بِأَنۡعُمِ ٱللَّهِ فَأَذَٰقَهَا ٱللَّهُ لِبَاسَ ٱلۡجُوعِ وَٱلۡخَوۡفِ بِمَا كَانُواْ يَصۡنَعُونَ
112. አላህ ጸጥተኛ የረካች ሲሳይዋ ሰፊ ሆኖ ከየስፍራው ይመጣላት የነበረችውንና ከዚያም በአላህ ጸጋዎች የካደችውን አላህም ይሠሩት በነበሩት ኃጢአት የረሀብንና የፍርሀትን ቅጣቶች ያቀመሳትን ከተማ ምሳሌ አደረገ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلَقَدۡ جَآءَهُمۡ رَسُولٞ مِّنۡهُمۡ فَكَذَّبُوهُ فَأَخَذَهُمُ ٱلۡعَذَابُ وَهُمۡ ظَٰلِمُونَ
113. ከእነርሱም ውስጥ የሆነ መልዕክተኛም በእርግጥ መጣላቸው:: አስተባበሉትም እነርሱም በዳዬች ሆነው ቅጣቱ ያዛቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَكُلُواْ مِمَّا رَزَقَكُمُ ٱللَّهُ حَلَٰلٗا طَيِّبٗا وَٱشۡكُرُواْ نِعۡمَتَ ٱللَّهِ إِن كُنتُمۡ إِيَّاهُ تَعۡبُدُونَ
114. አላህም ከሰጣችሁ ሲሳይ የተፈቀደና ንጹሕ ሲሆን ብሉ:: የአላህንም ጸጋ እርሱን የምትገዙት ከሆናችሁ አመስግኑት::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيۡكُمُ ٱلۡمَيۡتَةَ وَٱلدَّمَ وَلَحۡمَ ٱلۡخِنزِيرِ وَمَآ أُهِلَّ لِغَيۡرِ ٱللَّهِ بِهِۦۖ فَمَنِ ٱضۡطُرَّ غَيۡرَ بَاغٖ وَلَا عَادٖ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٞ
115. በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የአሳማን ሥጋ፣ ያንንም በሚታረድ ጊዜ በእርሱ ላይ ከአላህ ስም ሌላ የተወሳበትን ብቻ ነው:: አመጸኛና ወሰን አላፊም ሳይሆን ከእነዚህ አንዱን ለመብላት የተገደደ ሰው ይፈቀድለታል:: አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلَا تَقُولُواْ لِمَا تَصِفُ أَلۡسِنَتُكُمُ ٱلۡكَذِبَ هَٰذَا حَلَٰلٞ وَهَٰذَا حَرَامٞ لِّتَفۡتَرُواْ عَلَى ٱللَّهِ ٱلۡكَذِبَۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَفۡتَرُونَ عَلَى ٱللَّهِ ٱلۡكَذِبَ لَا يُفۡلِحُونَ
116. (ሰዎች ሆይ) በአላህ ላይ ውሸትን ልትቀጣጥፉ ምላሶቻችሁ በሚመጥኑት ውሸት «ይህ የተፈቀደ ነው፤ ይህ ደግሞ እርም ነው» አትበሉ:: እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ ክፍሎች በፍጹም አይድኑም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
مَتَٰعٞ قَلِيلٞ وَلَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ
117. ጥቂት መጣቀም ብቻ አለላቸው:: ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَعَلَى ٱلَّذِينَ هَادُواْ حَرَّمۡنَا مَا قَصَصۡنَا عَلَيۡكَ مِن قَبۡلُۖ وَمَا ظَلَمۡنَٰهُمۡ وَلَٰكِن كَانُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ يَظۡلِمُونَ
118. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነዚያ አይሁድ በሆኑት ሰዎች ላይ ከአሁን በፊት ባንተ ላይ የተረክነውን ነገር እርም አድርገንባቸዋል:: እኛም አልበደልናቸዉም:: ግን ራሳቸው ነፍሶቻቸውን ይበድሉ ነበሩ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ثُمَّ إِنَّ رَبَّكَ لِلَّذِينَ عَمِلُواْ ٱلسُّوٓءَ بِجَهَٰلَةٖ ثُمَّ تَابُواْ مِنۢ بَعۡدِ ذَٰلِكَ وَأَصۡلَحُوٓاْ إِنَّ رَبَّكَ مِنۢ بَعۡدِهَا لَغَفُورٞ رَّحِيمٌ
119. ከዚያም ጌታህ ለእነዚያ በስህተት መጥፎን ለሠሩትና ከዚያም ከዚህ በኋላ ለተጸጸቱ ሥራቸውንም ላበጁ ጌታህ ከእርሷ በኋላ በእርግጥ መሓሪና አዛኝ ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّ إِبۡرَٰهِيمَ كَانَ أُمَّةٗ قَانِتٗا لِّلَّهِ حَنِيفٗا وَلَمۡ يَكُ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ
120. ኢብራሂም ለአላህ ታዛዥ፤ ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ተዘንባይ ህዝብ ነበር:: ከአጋሪዎችም አልነበረም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
شَاكِرٗا لِّأَنۡعُمِهِۚ ٱجۡتَبَىٰهُ وَهَدَىٰهُ إِلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ
121. ለጸጋዎቹ አመስጋኝ ነበር:: መረጠው:: ወደ ቀጥተኛዉም መንገድ መራው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَءَاتَيۡنَٰهُ فِي ٱلدُّنۡيَا حَسَنَةٗۖ وَإِنَّهُۥ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ لَمِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
122. በቅርቢቱም ዓለም በጎ ነገርን ሰጠነው:: እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም በእርግጥ ከመልካሞቹ ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ثُمَّ أَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡكَ أَنِ ٱتَّبِعۡ مِلَّةَ إِبۡرَٰهِيمَ حَنِيفٗاۖ وَمَا كَانَ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ
123. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዚያም የኢብራሂምን ሃይማኖት ቀጥተኛ ሲሆን ተከተል:: ከአጋሪዎቹም አልነበረም ማለትን ወደ አንተ አወረድን::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّمَا جُعِلَ ٱلسَّبۡتُ عَلَى ٱلَّذِينَ ٱخۡتَلَفُواْ فِيهِۚ وَإِنَّ رَبَّكَ لَيَحۡكُمُ بَيۡنَهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ فِيمَا كَانُواْ فِيهِ يَخۡتَلِفُونَ
124. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በቅዳሜ ቀን መስራት ክልክል የተደረገው በእነዚያ በእርሱ በተለያዩበት ሰዎች ላይ ብቻ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም በትንሳኤ ቀን ይለያዩበት በነበሩት ነገር በመካከላቸው በእርግጥ ይፈርዳል::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ٱدۡعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِٱلۡحِكۡمَةِ وَٱلۡمَوۡعِظَةِ ٱلۡحَسَنَةِۖ وَجَٰدِلۡهُم بِٱلَّتِي هِيَ أَحۡسَنُۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعۡلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦ وَهُوَ أَعۡلَمُ بِٱلۡمُهۡتَدِينَ
125. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ በለዘብተኛ ቃልም ሰዎችን ጥራ:: በዚያችም እርሷ መልካም በሆነችው ዘዴ ተከራከራቸው:: ጌታህ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው አዋቂ ነው:: እንደዚሁም እርሱ ቅን የሆኑትን ሰዎች አዋቂ ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَإِنۡ عَاقَبۡتُمۡ فَعَاقِبُواْ بِمِثۡلِ مَا عُوقِبۡتُم بِهِۦۖ وَلَئِن صَبَرۡتُمۡ لَهُوَ خَيۡرٞ لِّلصَّٰبِرِينَ
126. (ሙስሊሞች ሆይ!) ብትበቀሉም በእርሱ በተቀጣችሁበት ብጤ ተበቀሉ:: ብትታገሱ ግን እርሱ ለታጋሾች በእርግጥ በላጭ ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَٱصۡبِرۡ وَمَا صَبۡرُكَ إِلَّا بِٱللَّهِۚ وَلَا تَحۡزَنۡ عَلَيۡهِمۡ وَلَا تَكُ فِي ضَيۡقٖ مِّمَّا يَمۡكُرُونَ
127. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ታገስ:: መታገስህ በአላህ ማስቻል ብቻ እንጂ አይደለም:: በእነርሱም ላይ ባያምኑ አትተክዝ:: ባንተ ላይ በሚመክሩት ተንኮልም በጭንቀት ውስጥ አትሁን::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلَّذِينَ ٱتَّقَواْ وَّٱلَّذِينَ هُم مُّحۡسِنُونَ
128. አላህ ከእነዚያ እነርሱ ከሚፈሩትና ከእነዚያም እነርሱ ከመልካም ሠሪ ከሆኑት ሰዎች ጋር ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
 
የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: ሱረቱ አን-ነሕል
የምዕራፎች ማውጫ የገፅ ቁጥር
 
የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - አማርኛ ትርጉም ‐ ዘይን - የትርጉሞች ማዉጫ

አማርኛ ትርጉም

መዝጋት