Check out the new design

የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ * - የትርጉሞች ማዉጫ


የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: አል-በቀራህ   አንቀጽ:
۞ تِلۡكَ ٱلرُّسُلُ فَضَّلۡنَا بَعۡضَهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖۘ مِّنۡهُم مَّن كَلَّمَ ٱللَّهُۖ وَرَفَعَ بَعۡضَهُمۡ دَرَجَٰتٖۚ وَءَاتَيۡنَا عِيسَى ٱبۡنَ مَرۡيَمَ ٱلۡبَيِّنَٰتِ وَأَيَّدۡنَٰهُ بِرُوحِ ٱلۡقُدُسِۗ وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ مَا ٱقۡتَتَلَ ٱلَّذِينَ مِنۢ بَعۡدِهِم مِّنۢ بَعۡدِ مَا جَآءَتۡهُمُ ٱلۡبَيِّنَٰتُ وَلَٰكِنِ ٱخۡتَلَفُواْ فَمِنۡهُم مَّنۡ ءَامَنَ وَمِنۡهُم مَّن كَفَرَۚ وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ مَا ٱقۡتَتَلُواْ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ يَفۡعَلُ مَا يُرِيدُ
253. እነዚያን መልዕክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አበለጥን:: ከእነርሱ መካከልም አላህ ያነጋገረው አለ:: ከፊሎቻቸውንም በደረጃ ከሌሎች ከፍ አድርጓል:: የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ተዐምራት ሰጠነው:: በቅዱስ መንፈስም (በመላኩ ጂብሪል) አበረታነው:: አላህ በፈለገ ኖሮ እነዚያ ከእነርሱ በኋላ የነበሩት መረጃው ከመጣላቸው በኋላ እርስ በእርሳቸው ባልተዋጉ ነበር:: ግን ተለያዩ:: በመሆኑም ከመሀከላቸው ትክክለኛ አማኝ ክፍል አለ:: ከመሀከላቸዉም ከሃዲ አለ:: አላህ በፈለገ ኖሮ እርስ በእርሳቸው ባልተዋጉ ነበር:: አላህ ግን የሚሻውን ሁሉ ይሰራል::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَنفِقُواْ مِمَّا رَزَقۡنَٰكُم مِّن قَبۡلِ أَن يَأۡتِيَ يَوۡمٞ لَّا بَيۡعٞ فِيهِ وَلَا خُلَّةٞ وَلَا شَفَٰعَةٞۗ وَٱلۡكَٰفِرُونَ هُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ
254. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ያ ንግድ፤ ወዳጅነትም ሆነ ምልጃ የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ:: በዳዮች ማለት ከሓዲያን ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلۡحَيُّ ٱلۡقَيُّومُۚ لَا تَأۡخُذُهُۥ سِنَةٞ وَلَا نَوۡمٞۚ لَّهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۗ مَن ذَا ٱلَّذِي يَشۡفَعُ عِندَهُۥٓ إِلَّا بِإِذۡنِهِۦۚ يَعۡلَمُ مَا بَيۡنَ أَيۡدِيهِمۡ وَمَا خَلۡفَهُمۡۖ وَلَا يُحِيطُونَ بِشَيۡءٖ مِّنۡ عِلۡمِهِۦٓ إِلَّا بِمَا شَآءَۚ وَسِعَ كُرۡسِيُّهُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَۖ وَلَا يَـُٔودُهُۥ حِفۡظُهُمَاۚ وَهُوَ ٱلۡعَلِيُّ ٱلۡعَظِيمُ
255. አላህ ከእርሱ በስተቀር ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: አላህ ምንግዜም ሕያው፤ በራሱ የተብቃቃ ነው:: ማንጎላጀትም ሆነ እንቅልፍ አትይዘዉም:: በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: ያ እርሱ ዘንድ በፍቃዱ ቢሆን እንጂ የሚያማልድ ማን ነው? (ከፍጡራን) ሁሉ በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ጠንቅቆ ያውቃል:: በሻው ነገር እንጂ ከእውቀቱ (ፍጡራን) በምንም ነገር አያካብቡም:: መንበሩ የሰማያትንና የምድርን ስፋት ይበልጣል:: ጥበቃቸዉም አያቅተዉም:: እርሱ የሁሉ የበላይና ታላቅ ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لَآ إِكۡرَاهَ فِي ٱلدِّينِۖ قَد تَّبَيَّنَ ٱلرُّشۡدُ مِنَ ٱلۡغَيِّۚ فَمَن يَكۡفُرۡ بِٱلطَّٰغُوتِ وَيُؤۡمِنۢ بِٱللَّهِ فَقَدِ ٱسۡتَمۡسَكَ بِٱلۡعُرۡوَةِ ٱلۡوُثۡقَىٰ لَا ٱنفِصَامَ لَهَاۗ وَٱللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
256. በሃይማኖት ማስገደድ የለም:: ቅኑ መንገድ ከጠማማው መንገድ በእርግጥ ተገለጠ:: በጣኦት (ባዕድ አምልኮ) የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ሁሉ የማትበጠስ ጠንካራ ገመድን ጨብጧል:: አላህ ሁሉን ሰሚ ሁሉንም አዋቂ ነውና።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
 
የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: አል-በቀራህ
የምዕራፎች ማውጫ የገፅ ቁጥር
 
የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ - የትርጉሞች ማዉጫ

ተርጓሙ በመሐመድ ዘይን ዘህር ዲን። የተሰኘ በአፍሪካ አካዳሚ።

መዝጋት