Check out the new design

የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ * - የትርጉሞች ማዉጫ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: አል አንቢያ   አንቀጽ:
وَٱلَّتِيٓ أَحۡصَنَتۡ فَرۡجَهَا فَنَفَخۡنَا فِيهَا مِن رُّوحِنَا وَجَعَلۡنَٰهَا وَٱبۡنَهَآ ءَايَةٗ لِّلۡعَٰلَمِينَ
91.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያችንም ብልቷን (ከዝሙት) የጠበቀችውንና በእርሷም ውስጥ ከመንፈሳችን የነፋንባትን እርሷንም ሆነ ልጇን ለዓለማት ተዓምር ያደረግናትን መርየምን አስታውስ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمۡ أُمَّةٗ وَٰحِدَةٗ وَأَنَا۠ رَبُّكُمۡ فَٱعۡبُدُونِ
92. እነዚህ ህግጋት አንድ መንገድ ሲሆኑ በእርግጥ የሃይማኖታችሁ ህግጋት ናቸው:: እኔም ጌታችሁ ነኝና ተገዙኝ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَتَقَطَّعُوٓاْ أَمۡرَهُم بَيۡنَهُمۡۖ كُلٌّ إِلَيۡنَا رَٰجِعُونَ
93.በሃይማኖታቸዉም ነገር በመካከላቸው ተለያዩ:: ሁሉም ወደ እኛ ተመላሾች ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَمَن يَعۡمَلۡ مِنَ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَهُوَ مُؤۡمِنٞ فَلَا كُفۡرَانَ لِسَعۡيِهِۦ وَإِنَّا لَهُۥ كَٰتِبُونَ
94. እርሱ ያመነ ሆኖ ከበጎ ስራዎች ማንኛውንም የሚሰራም ምንዳውን አይነፍግም፤ እኛም ለእርሱ መዝጋቢዎች ነን::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَحَرَٰمٌ عَلَىٰ قَرۡيَةٍ أَهۡلَكۡنَٰهَآ أَنَّهُمۡ لَا يَرۡجِعُونَ
95. ባጠፋናትም ከተማ ላይ ዘበት ነው፤ (ወደ ዱኒያ) አይመለሱምና።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
حَتَّىٰٓ إِذَا فُتِحَتۡ يَأۡجُوجُ وَمَأۡجُوجُ وَهُم مِّن كُلِّ حَدَبٖ يَنسِلُونَ
96.የዕጁጅና መዕጁጅም እነርሱ ከየሸንተረሩ የሚንደረደሩ ሲሆኑ ግድባቸው በተከፈተች ጊዜ ፤
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَٱقۡتَرَبَ ٱلۡوَعۡدُ ٱلۡحَقُّ فَإِذَا هِيَ شَٰخِصَةٌ أَبۡصَٰرُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ يَٰوَيۡلَنَا قَدۡ كُنَّا فِي غَفۡلَةٖ مِّنۡ هَٰذَا بَلۡ كُنَّا ظَٰلِمِينَ
97. እውነተኛዉም ቀጠሮ በቀረበ ጊዜ ያንን ጊዜ እነሆ የእነዚያ ከሀዲያን ዓይኖች ይፈጥጣሉ:: «ዋ ጥፍታችን! ከዚያ ቀን በእርግጥ በዝንጋቴ ላይ ነበርን:: በእውነትም በዳዮች ነበርን።» ይላሉ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّكُمۡ وَمَا تَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ حَصَبُ جَهَنَّمَ أَنتُمۡ لَهَا وَٰرِدُونَ
98. (ከሓዲያን ሆይ!) እናንተና ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ጣዖታት የገሀነም ማገዶዎች ናችሁ:: እናንተ ለእርሷ ወራጆች ናችሁ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لَوۡ كَانَ هَٰٓؤُلَآءِ ءَالِهَةٗ مَّا وَرَدُوهَاۖ وَكُلّٞ فِيهَا خَٰلِدُونَ
99.እነዚህ ጣዖታት አማልክት በነበሩ ኖሮ ገሀነምን አይገቧትም ነበር:: ግን ሁሉም በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لَهُمۡ فِيهَا زَفِيرٞ وَهُمۡ فِيهَا لَا يَسۡمَعُونَ
100.እነርሱ በእርሷ ውስጥ ይንሰቀሰቃሉ:: እነርሱም በውስጧ ምንንም አይሰሙም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّ ٱلَّذِينَ سَبَقَتۡ لَهُم مِّنَّا ٱلۡحُسۡنَىٰٓ أُوْلَٰٓئِكَ عَنۡهَا مُبۡعَدُونَ
101. እነዚያ ከእኛ መልካሟ ቃል ለእነርሱ ያለፈችላቸው እነዚያ ከእርሷ የተራቁ ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
 
የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: አል አንቢያ
የምዕራፎች ማውጫ የገፅ ቁጥር
 
የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ - የትርጉሞች ማዉጫ

ከአፍሪካ አካዳሚ የተገኘ ‐ ተርጓሚ መሐመድ ዘይን ዘህረዲን

መዝጋት