Check out the new design

የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ * - የትርጉሞች ማዉጫ


የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: አል ፉርቃን   አንቀጽ:
أَمۡ تَحۡسَبُ أَنَّ أَكۡثَرَهُمۡ يَسۡمَعُونَ أَوۡ يَعۡقِلُونَۚ إِنۡ هُمۡ إِلَّا كَٱلۡأَنۡعَٰمِ بَلۡ هُمۡ أَضَلُّ سَبِيلًا
44. ይልቁንም አብዛኛዎቻቸው የሚሰሙ ወይም የሚያውቁ መሆናቸውን ታስባለህን? እነርሱ እንደ እንስሳዎች እንጂ ሌላ አይደሉም:: ከቶውንም እነርሱ ከእንስሳዎች በባሰ መንገድን የተሳሳቱ ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
أَلَمۡ تَرَ إِلَىٰ رَبِّكَ كَيۡفَ مَدَّ ٱلظِّلَّ وَلَوۡ شَآءَ لَجَعَلَهُۥ سَاكِنٗا ثُمَّ جَعَلۡنَا ٱلشَّمۡسَ عَلَيۡهِ دَلِيلٗا
45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ጥላን እንዴት እንደ ዘረጋ አላየህምን? በሻም ኖሮ የረጋ ባደረገው ነበር:: ከዚያ ጸሐይን በእርሱ ላይ ምልክት አደረግን።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
ثُمَّ قَبَضۡنَٰهُ إِلَيۡنَا قَبۡضٗا يَسِيرٗا
46. ከዚያም ቀስ በቀስ ወደ እኛ ሰበሰብነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَهُوَ ٱلَّذِي جَعَلَ لَكُمُ ٱلَّيۡلَ لِبَاسٗا وَٱلنَّوۡمَ سُبَاتٗا وَجَعَلَ ٱلنَّهَارَ نُشُورٗا
47. እርሱም ያ ለእናንተ ሌሊትን ልብስ እንቅልፍንም ማረፊያ ያደረገ:: ቀንንም መተኛ ያደረገላችሁ አምላክ ነው።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَهُوَ ٱلَّذِيٓ أَرۡسَلَ ٱلرِّيَٰحَ بُشۡرَۢا بَيۡنَ يَدَيۡ رَحۡمَتِهِۦۚ وَأَنزَلۡنَا مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ طَهُورٗا
48. እርሱ (አላህ) ያ ንፋሶችን አብሳሪዎች ሲሆኑ ከዝናቡ በስተፊት የላከ ነው:: ከሰማይም አጥሪ ውሃን አወረድን::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
لِّنُحۡـِۧيَ بِهِۦ بَلۡدَةٗ مَّيۡتٗا وَنُسۡقِيَهُۥ مِمَّا خَلَقۡنَآ أَنۡعَٰمٗا وَأَنَاسِيَّ كَثِيرٗا
49. በእርሱ የሞተችን ሀገር ህያው ልናደርግበት፤ ከፈጠርነዉም ፍጡር እንስሳዎችንና ብዙ ሰዎችንም ልናጠጣበት አወረድነው።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلَقَدۡ صَرَّفۡنَٰهُ بَيۡنَهُمۡ لِيَذَّكَّرُواْ فَأَبَىٰٓ أَكۡثَرُ ٱلنَّاسِ إِلَّا كُفُورٗا
50. ጸጋችንን ይገነዘቡም ዘንድ በመካከላቸው ከፋፈልነው አበላለጥነዉም:: ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች ክህደትን እንጂ እንቢ አሉ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلَوۡ شِئۡنَا لَبَعَثۡنَا فِي كُلِّ قَرۡيَةٖ نَّذِيرٗا
51. በሻንም ኖሮ በየከተማይቱ አስፈራሪን በላክን ነበር::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
فَلَا تُطِعِ ٱلۡكَٰفِرِينَ وَجَٰهِدۡهُم بِهِۦ جِهَادٗا كَبِيرٗا
52. ከሓዲያንን አትታዘዛቸው:: በእርሱም (በቁርኣን) ታላቅን ትግል ታገላቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
۞ وَهُوَ ٱلَّذِي مَرَجَ ٱلۡبَحۡرَيۡنِ هَٰذَا عَذۡبٞ فُرَاتٞ وَهَٰذَا مِلۡحٌ أُجَاجٞ وَجَعَلَ بَيۡنَهُمَا بَرۡزَخٗا وَحِجۡرٗا مَّحۡجُورٗا
53. እርሱ ያ ሁለትን ባህሮች አጎራብቶ የለቀቀ ነው:: አንዱ ጥም የሚቆርጥና ጣፋጭ ነው:: ሌላኛው ደግሞ የሚመረግግ ጨው ነው:: በመካከላቸዉም ከመቀላቀል መለያንና የተከለለን ክልል ያደረገ ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَهُوَ ٱلَّذِي خَلَقَ مِنَ ٱلۡمَآءِ بَشَرٗا فَجَعَلَهُۥ نَسَبٗا وَصِهۡرٗاۗ وَكَانَ رَبُّكَ قَدِيرٗا
54. እርሱም ያ ከውሃ ሰውን የፈጠረ የዝምድናና የአማችም ባለቤት ያደረገው ነው:: ጌታህም ሁሉን ነገር ቻይ ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَيَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَنفَعُهُمۡ وَلَا يَضُرُّهُمۡۗ وَكَانَ ٱلۡكَافِرُ عَلَىٰ رَبِّهِۦ ظَهِيرٗا
55. ከአላህ ሌላ የማይጠቅማቸውንና የማይጎዳቸውን አካል ይገዛሉ:: ከሓዲ በጌታው ላይ (በማመጽ ለሰይጣን) ረዳት ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
 
የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: አል ፉርቃን
የምዕራፎች ማውጫ የገፅ ቁጥር
 
የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ - የትርጉሞች ማዉጫ

ተርጓሙ በመሐመድ ዘይን ዘህር ዲን። የተሰኘ በአፍሪካ አካዳሚ።

መዝጋት