Check out the new design

የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ * - የትርጉሞች ማዉጫ


የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: አን ነምል   አንቀጽ:
مَن جَآءَ بِٱلۡحَسَنَةِ فَلَهُۥ خَيۡرٞ مِّنۡهَا وَهُم مِّن فَزَعٖ يَوۡمَئِذٍ ءَامِنُونَ
89. መልካም ሥራን የሰራ ለእርሱ ከእርሷ የበለጠ ምንዳ አለው:: እነርሱም በዚያ ቀን ከድንጋጤ ነፃ ናቸው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَمَن جَآءَ بِٱلسَّيِّئَةِ فَكُبَّتۡ وُجُوهُهُمۡ فِي ٱلنَّارِ هَلۡ تُجۡزَوۡنَ إِلَّا مَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
90. መጥፎንም የሰሩ ፊቶቻቸው በእሳት ውስጥ ይደፋሉ። «ትሠሩት የነበራችሁትን እንጂ አትመነዱም» ይበላሉ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِنَّمَآ أُمِرۡتُ أَنۡ أَعۡبُدَ رَبَّ هَٰذِهِ ٱلۡبَلۡدَةِ ٱلَّذِي حَرَّمَهَا وَلَهُۥ كُلُّ شَيۡءٖۖ وَأُمِرۡتُ أَنۡ أَكُونَ مِنَ ٱلۡمُسۡلِمِينَ
91. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! በላቸው:) «የታዘዝኩት የዚህችን አገር የመካን ጌታ ያንን ክልክል ያደረጋትንም አላህን እንድገዛ ብቻ ነው:: ነገሩም ሁሉ የእርሱ ነው:: ከሙስሊሞችም እንድሆን ታዝዣለሁ።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَأَنۡ أَتۡلُوَاْ ٱلۡقُرۡءَانَۖ فَمَنِ ٱهۡتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهۡتَدِي لِنَفۡسِهِۦۖ وَمَن ضَلَّ فَقُلۡ إِنَّمَآ أَنَا۠ مِنَ ٱلۡمُنذِرِينَ
92. «ቁርኣንንም እንዳነብ ታዝዣለሁ:: በቀጥተኛው መንገድ የተመራ ሁሉ የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው:: የተሳሳተም እኔ ከአስፈራሪዎች ነኝ እንጂ ሌላ አይደለሁም።» በላቸው።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَقُلِ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ سَيُرِيكُمۡ ءَايَٰتِهِۦ فَتَعۡرِفُونَهَاۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَٰفِلٍ عَمَّا تَعۡمَلُونَ
93. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ምስጋናም ሁሉ ለአላህ ብቻ ነው:: ተአምራቱን ወደ ፊት ያሳያችኋል:: ታውቋታላችሁም።» በላቸው:: ጌታህ ከምትሠሩት ነገር ሁሉ ዘንጊ አይደለም።
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
 
የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: አን ነምል
የምዕራፎች ማውጫ የገፅ ቁጥር
 
የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ - የትርጉሞች ማዉጫ

ተርጓሙ በመሐመድ ዘይን ዘህር ዲን። የተሰኘ በአፍሪካ አካዳሚ።

መዝጋት