Check out the new design

የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ * - የትርጉሞች ማዉጫ


የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: ፋጢር   አንቀጽ:
وَمَا يَسۡتَوِي ٱلۡبَحۡرَانِ هَٰذَا عَذۡبٞ فُرَاتٞ سَآئِغٞ شَرَابُهُۥ وَهَٰذَا مِلۡحٌ أُجَاجٞۖ وَمِن كُلّٖ تَأۡكُلُونَ لَحۡمٗا طَرِيّٗا وَتَسۡتَخۡرِجُونَ حِلۡيَةٗ تَلۡبَسُونَهَاۖ وَتَرَى ٱلۡفُلۡكَ فِيهِ مَوَاخِرَ لِتَبۡتَغُواْ مِن فَضۡلِهِۦ وَلَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ
12. ሁለቱ ባህሮች አይስተካከሉም ይህ ጣፋጭ፤ ጥምን ቆራጭ መጠጡ በገር ተዋጭ ነው:: ይህኛው ደግሞ ጨው መርጋጋ ነው:: ከሁሉም እርጥብ ስጋን ትበላላችሁ:: የምትለብሷትንም ጌጥ ታወጣላችሁ። ከችሮታው ልትፈልጉና ልታመሰግኑትም መርከቦችን በእርሱ ውስጥ ውሃውን ቀዳጆች ሆነው ሲንሻለሉ ታያለህ::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
يُولِجُ ٱلَّيۡلَ فِي ٱلنَّهَارِ وَيُولِجُ ٱلنَّهَارَ فِي ٱلَّيۡلِ وَسَخَّرَ ٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَۖ كُلّٞ يَجۡرِي لِأَجَلٖ مُّسَمّٗىۚ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمۡ لَهُ ٱلۡمُلۡكُۚ وَٱلَّذِينَ تَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦ مَا يَمۡلِكُونَ مِن قِطۡمِيرٍ
13. ሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል:: ቀንንም በሌሊት ውስጥ ያስገባል:: ጸሀይንና ጨረቃንም ገራ:: ሁሉም እስከ ተወሰነለት ጊዜ ድረስ ይሮጣል :: ይህን የሚያደርገው ጌታችሁ አላህ ብቻ ነው :: ንግስናው የእሱ ብቻ ነው:: እነዚያም ከእርሱ ሌላ የምትገዟቸው የተምር ፍሬ ሽፋን ያህል እንኳን አይኖራቸዉም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِن تَدۡعُوهُمۡ لَا يَسۡمَعُواْ دُعَآءَكُمۡ وَلَوۡ سَمِعُواْ مَا ٱسۡتَجَابُواْ لَكُمۡۖ وَيَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ يَكۡفُرُونَ بِشِرۡكِكُمۡۚ وَلَا يُنَبِّئُكَ مِثۡلُ خَبِيرٖ
14. ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም:: ቢሰሙም ኖሮ ለእናንተ አይመልሱላችሁም:: በትንሳኤም ቀን እነርሱን በአላህ ማጋራታችሁን ይክዳሉ። እንደ ውስጠ አዋቂው አላህ ማንም አይነግርህም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
۞ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ أَنتُمُ ٱلۡفُقَرَآءُ إِلَى ٱللَّهِۖ وَٱللَّهُ هُوَ ٱلۡغَنِيُّ ٱلۡحَمِيدُ
15. እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ ሁል ጊዜ ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ:: አላህም እርሱ ተብቃቂውና ምስጉኑ ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
إِن يَشَأۡ يُذۡهِبۡكُمۡ وَيَأۡتِ بِخَلۡقٖ جَدِيدٖ
16. (አላህ) ቢሻ ያስወግዳችሁና አዲስን ፍጡር ያመጣል (ይፈጥራል)::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَمَا ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ بِعَزِيزٖ
17. ይህም በአላህ ላይ ምንም አስቸጋሪ አይደለም::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٞ وِزۡرَ أُخۡرَىٰۚ وَإِن تَدۡعُ مُثۡقَلَةٌ إِلَىٰ حِمۡلِهَا لَا يُحۡمَلۡ مِنۡهُ شَيۡءٞ وَلَوۡ كَانَ ذَا قُرۡبَىٰٓۗ إِنَّمَا تُنذِرُ ٱلَّذِينَ يَخۡشَوۡنَ رَبَّهُم بِٱلۡغَيۡبِ وَأَقَامُواْ ٱلصَّلَوٰةَۚ وَمَن تَزَكَّىٰ فَإِنَّمَا يَتَزَكَّىٰ لِنَفۡسِهِۦۚ وَإِلَى ٱللَّهِ ٱلۡمَصِيرُ
18. ኃጢአትን ተሸካሚም ነፍስ የሌላውን ሸክም አትሸከምም:: የራሷ ወንጀል የከበዳትም ነፍስ እርዳታ እንዲደረግላት ብትጠራ ተጠሪው የቅርብ ዝምድና ባለቤት ቢሆንም እንኳን ከእርሷ አንድን ነገር የሚሸከምላት አታገኝም:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የምታስጠነቅቀው እነዚያን ጌታቸውን፤ በሩቅ የሚፈሩትን ሶላትንም አስተካክለው የሚሰገዱትን ብቻ ነው:: ከወንጀልም የተጥራራ ሁሉ የሚጥራራው ለራሱ ብቻ ነው:: መመለሻዉም ወደ አላህ ብቻ ነው::
የአረብኛ ቁርኣን ማብራሪያ:
 
የይዘት ትርጉም ምዕራፍ: ፋጢር
የምዕራፎች ማውጫ የገፅ ቁጥር
 
የቅዱስ ቁርዓን ይዘት ትርጉም - የአማርኛ ትርጉም ‐ አፍሪቃ አካዳሚ - የትርጉሞች ማዉጫ

ከአፍሪካ አካዳሚ የተገኘ ‐ ተርጓሚ መሐመድ ዘይን ዘህረዲን

መዝጋት