للإطلاع على الموقع بحلته الجديدة

ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا * - فهرس التراجم


ترجمة معاني سورة: الإسراء   آية:
وَمَن يَهۡدِ ٱللَّهُ فَهُوَ ٱلۡمُهۡتَدِۖ وَمَن يُضۡلِلۡ فَلَن تَجِدَ لَهُمۡ أَوۡلِيَآءَ مِن دُونِهِۦۖ وَنَحۡشُرُهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ عَلَىٰ وُجُوهِهِمۡ عُمۡيٗا وَبُكۡمٗا وَصُمّٗاۖ مَّأۡوَىٰهُمۡ جَهَنَّمُۖ كُلَّمَا خَبَتۡ زِدۡنَٰهُمۡ سَعِيرٗا
97. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ያቀናው በእርግጥም የተቀና ማለት እርሱው ነው:: እርሱ ያጠመማቸውን ግን ከቅጣቱ የሚያድናቸው ማንም ወዳጅ አታገኝላቸዉም:: የትንሳኤ ቀንም እውር፤ ዲዳና፤ ደንቆሮ አድርገን በፊቶቻቸው እየተጎተቱ እንሰበስባቸዋለን:: መኖሪያቸዉም ገሀነም ናት:: ሀይሏ በደከመ ጊዜም ግለትን እንጨምርላቸዋለን::
التفاسير العربية:
ذَٰلِكَ جَزَآؤُهُم بِأَنَّهُمۡ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَقَالُوٓاْ أَءِذَا كُنَّا عِظَٰمٗا وَرُفَٰتًا أَءِنَّا لَمَبۡعُوثُونَ خَلۡقٗا جَدِيدًا
98. ይህ ቅጣት የሚጠብቃቸው ቅጣታቸው ነው:: ምክንያቱም በመልዕክተኞቻችን ክደው «የበሰበሰ አጥንት ከሆንና (ወደ አቧራነት) ከተቀየርን በኋላ እንደ አዲስ እንቀሰቀሳለን?» በማለታቸውም ነው።
التفاسير العربية:
۞ أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ أَنَّ ٱللَّهَ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ قَادِرٌ عَلَىٰٓ أَن يَخۡلُقَ مِثۡلَهُمۡ وَجَعَلَ لَهُمۡ أَجَلٗا لَّا رَيۡبَ فِيهِ فَأَبَى ٱلظَّٰلِمُونَ إِلَّا كُفُورٗا
99. ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ አላህ ብጤያቸውን በመፍጠር ላይ ቻይ መሆኑን በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበትንም ጊዜ ለሞትም ለትንሳኤም ለእነርሱ የወሰነ መሆኑን አላወቁምን? በደለኞችም ከክህደት በስተቀር እምቢ አሉ::
التفاسير العربية:
قُل لَّوۡ أَنتُمۡ تَمۡلِكُونَ خَزَآئِنَ رَحۡمَةِ رَبِّيٓ إِذٗا لَّأَمۡسَكۡتُمۡ خَشۡيَةَ ٱلۡإِنفَاقِۚ وَكَانَ ٱلۡإِنسَٰنُ قَتُورٗا
100. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ የጌታዬን የችሮታ መካዚኖች ብትይዙ ኖሮ ያን ጊዜ በማውጣታችሁ ማለቋን በመፍራት በጨበጣችሁ ነበር:: ሰው በጣም ንፉግ ነውና።» በላቸው።
التفاسير العربية:
وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَىٰ تِسۡعَ ءَايَٰتِۭ بَيِّنَٰتٖۖ فَسۡـَٔلۡ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ إِذۡ جَآءَهُمۡ فَقَالَ لَهُۥ فِرۡعَوۡنُ إِنِّي لَأَظُنُّكَ يَٰمُوسَىٰ مَسۡحُورٗا
101. ለሙሳ ግልጽ የሆኑን ዘጠኝ ተዓምራት በእርግጥ ሰጠነው:: በመጣቸዉም ጊዜ የኢስራኢልን ልጆች ከፈርዖን እንዲለቀቁ ጠይቅ አልነው:: ፈርዖንም፡- «ሙሳ ሆይ! እኔ የተደገመብህ መሆንህን በእርግጥ እጠረጥርሃለሁ።» አለው።
التفاسير العربية:
قَالَ لَقَدۡ عَلِمۡتَ مَآ أَنزَلَ هَٰٓؤُلَآءِ إِلَّا رَبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ بَصَآئِرَ وَإِنِّي لَأَظُنُّكَ يَٰفِرۡعَوۡنُ مَثۡبُورٗا
102. ሙሳም፡- «እነዚህን ተዓምራት መግሰጫዎች ሲሆኑ የሰማያትና የምድር ጌታ እንጂ ሌላ እንዳላወረዳቸው በእርግጥ አውቀሀል:: እኔም ፈርዖን ሆይ! የምትጠፋ መሆንህን በእርግጥ እጠረጥርሃለሁ።» አለው።
التفاسير العربية:
فَأَرَادَ أَن يَسۡتَفِزَّهُم مِّنَ ٱلۡأَرۡضِ فَأَغۡرَقۡنَٰهُ وَمَن مَّعَهُۥ جَمِيعٗا
103. ከምድርም ሊያባርራቸው አሰበ:: እርሱንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች ሁሉንም አሰመጥናቸው::
التفاسير العربية:
وَقُلۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِۦ لِبَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ ٱسۡكُنُواْ ٱلۡأَرۡضَ فَإِذَا جَآءَ وَعۡدُ ٱلۡأٓخِرَةِ جِئۡنَا بِكُمۡ لَفِيفٗا
104. ከእርሱም በኋላ ለኢስራኢል ልጆች «ምድሪቱን ተቀመጡባት:: የኋለኛይቱም ሰዓት ቀጠሮ በመጣ ጊዜ እናንተን የተከማቻችሁ ስትሆኑ እናመጣችኋለን።» አልናቸው።
التفاسير العربية:
 
ترجمة معاني سورة: الإسراء
فهرس السور رقم الصفحة
 
ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا - فهرس التراجم

ترجمها محمد زين زهر الدين. صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

إغلاق