للإطلاع على الموقع بحلته الجديدة

ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا * - فهرس التراجم


ترجمة معاني سورة: البقرة   آية:
وَلَا تَقُولُواْ لِمَن يُقۡتَلُ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ أَمۡوَٰتُۢۚ بَلۡ أَحۡيَآءٞ وَلَٰكِن لَّا تَشۡعُرُونَ
154. በአላህ መንገድ (ለሀይማኖቱ) የሚገደሉትን «ሙታን ናቸው።» አትበሉ:: በእውነቱ ሕያው ናቸውና:: እናንተ ግን አትገነዘቡትም::
التفاسير العربية:
وَلَنَبۡلُوَنَّكُم بِشَيۡءٖ مِّنَ ٱلۡخَوۡفِ وَٱلۡجُوعِ وَنَقۡصٖ مِّنَ ٱلۡأَمۡوَٰلِ وَٱلۡأَنفُسِ وَٱلثَّمَرَٰتِۗ وَبَشِّرِ ٱلصَّٰبِرِينَ
155. ከፍርሀትና ከርሀብም ከሀብት፣ ከሕይወትና ከአዝመራ በመቀነስም በእርግጥ እንሞክራችኋለን:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ታጋሾችንም (በገነት) አብስር::
التفاسير العربية:
ٱلَّذِينَ إِذَآ أَصَٰبَتۡهُم مُّصِيبَةٞ قَالُوٓاْ إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّآ إِلَيۡهِ رَٰجِعُونَ
156. እነዚያ መከራ በነካቸቻው ጊዜ «እኛ ለአላህ ነን። እኛም ወደ እርሱ ተመላሾች ነን።» የሚሉትን አብስር።
التفاسير العربية:
أُوْلَٰٓئِكَ عَلَيۡهِمۡ صَلَوَٰتٞ مِّن رَّبِّهِمۡ وَرَحۡمَةٞۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُهۡتَدُونَ
157. እነዚያ በእነርሱ ላይ ከጌታቸው የሆኑ ምህረቶችና ችሮታም አሉ:: እነርሱም ወደ ቀናው መንገድ እውነት ተመሪዎቹ እነርሱው ናቸው።
التفاسير العربية:
۞ إِنَّ ٱلصَّفَا وَٱلۡمَرۡوَةَ مِن شَعَآئِرِ ٱللَّهِۖ فَمَنۡ حَجَّ ٱلۡبَيۡتَ أَوِ ٱعۡتَمَرَ فَلَا جُنَاحَ عَلَيۡهِ أَن يَطَّوَّفَ بِهِمَاۚ وَمَن تَطَوَّعَ خَيۡرٗا فَإِنَّ ٱللَّهَ شَاكِرٌ عَلِيمٌ
158. የሶፋና የመርዋ (ጋራዎች) የአላህን ትዕዛዝ ከመፈጸሚያ ጉልህ ቦታዎች (ምልክቶች) ናቸው:: ካዕባን በሐጅ ወይም በዑምራ ስራ ምክኒያት የጎበኘ ሁሉ በሁለቱ ጋራዎች መካከል በመመላለሱ ምንም ኃጢአት የለበትም:: መልካምንም ስራ በፈቃደኝነት የሰራ (ሁሉ አላህ ይመነዳዋል):: አላህ አመሰጋኝና ሁሉን አዋቂ ነውና::
التفاسير العربية:
إِنَّ ٱلَّذِينَ يَكۡتُمُونَ مَآ أَنزَلۡنَا مِنَ ٱلۡبَيِّنَٰتِ وَٱلۡهُدَىٰ مِنۢ بَعۡدِ مَا بَيَّنَّٰهُ لِلنَّاسِ فِي ٱلۡكِتَٰبِ أُوْلَٰٓئِكَ يَلۡعَنُهُمُ ٱللَّهُ وَيَلۡعَنُهُمُ ٱللَّٰعِنُونَ
159. እነዚያ (ስለነብዩ ሙሐመድና ሌሎችም) ከአናቅጽና ቅን መመሪያዎች ያወረድነውን ለሰዎች በመጽሐፍ ከገለጽነው በኋላ የሚደብቁትን ሁሉ አላህ ይረግማቸዋል:: ረጋሚዎችም ሁሉ ይረግሟቸዋል::
التفاسير العربية:
إِلَّا ٱلَّذِينَ تَابُواْ وَأَصۡلَحُواْ وَبَيَّنُواْ فَأُوْلَٰٓئِكَ أَتُوبُ عَلَيۡهِمۡ وَأَنَا ٱلتَّوَّابُ ٱلرَّحِيمُ
160. እነዚያ የተጸጸቱ፤ (ያበላሹትን) ያስተካከሉና (የደበቁትንም) የገለጹ ሲቀሩ:: የእነርሱን ጸጸትንማ እቀበላለሁ:: እኔም ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነኝ::
التفاسير العربية:
إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَمَاتُواْ وَهُمۡ كُفَّارٌ أُوْلَٰٓئِكَ عَلَيۡهِمۡ لَعۡنَةُ ٱللَّهِ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ وَٱلنَّاسِ أَجۡمَعِينَ
161. እነዚያ በአላህ የካዱና በክህደታቸው ላይ እያሉ የሞቱ ሰዎች በእነርሱ ላይ የአላህ፤ የመላዕክትና የመላው የሰው ዘር ሁሉ እርግማን አለባቸው::
التفاسير العربية:
خَٰلِدِينَ فِيهَا لَا يُخَفَّفُ عَنۡهُمُ ٱلۡعَذَابُ وَلَا هُمۡ يُنظَرُونَ
162. በእርግማን ውስጥም ሁልጊዜ ዘውታሪዎች ይሆናሉ:: ቅጣቱ ከእነርሱ አይቃለልም። ጊዜም አይሰጡም::
التفاسير العربية:
وَإِلَٰهُكُمۡ إِلَٰهٞ وَٰحِدٞۖ لَّآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلرَّحۡمَٰنُ ٱلرَّحِيمُ
163. (ሰዎች ሆይ!) አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: ከእርሱም ሌላ (ትክክለኛ) አምላክ የለም:: እርሱም እጅግ በጣም ሩህሩህና በጣም አዛኝ ነው::
التفاسير العربية:
 
ترجمة معاني سورة: البقرة
فهرس السور رقم الصفحة
 
ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا - فهرس التراجم

ترجمها محمد زين زهر الدين. صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

إغلاق