للإطلاع على الموقع بحلته الجديدة

ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا * - فهرس التراجم

PDF XML CSV Excel API
تنزيل الملفات يتضمن الموافقة على هذه الشروط والسياسات

ترجمة معاني سورة: الأنبياء   آية:
وَمَآ أَرۡسَلۡنَا مِن قَبۡلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِيٓ إِلَيۡهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعۡبُدُونِ
25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢሆን እንጂ ከመልዕክተኛ አንድንም አላክንም::
التفاسير العربية:
وَقَالُواْ ٱتَّخَذَ ٱلرَّحۡمَٰنُ وَلَدٗاۗ سُبۡحَٰنَهُۥۚ بَلۡ عِبَادٞ مُّكۡرَمُونَ
26. «አር-ረሕማንም ከመላእክት መካከል ልጅን ያዘ።» አሉ። ጥራት ተገባው። አይደለም መላእክት የተከበሩ ባሮች ብቻ ናቸው።
التفاسير العربية:
لَا يَسۡبِقُونَهُۥ بِٱلۡقَوۡلِ وَهُم بِأَمۡرِهِۦ يَعۡمَلُونَ
27. በንግግር አይቀድሙትም፤ ያዘዘውንም ይፈጽማሉ።
التفاسير العربية:
يَعۡلَمُ مَا بَيۡنَ أَيۡدِيهِمۡ وَمَا خَلۡفَهُمۡ وَلَا يَشۡفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ٱرۡتَضَىٰ وَهُم مِّنۡ خَشۡيَتِهِۦ مُشۡفِقُونَ
28.በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ያውቃል:: ለወደደውም እንጂ ለሌላው አያማልዱም:: እነርሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው::
التفاسير العربية:
۞ وَمَن يَقُلۡ مِنۡهُمۡ إِنِّيٓ إِلَٰهٞ مِّن دُونِهِۦ فَذَٰلِكَ نَجۡزِيهِ جَهَنَّمَۚ كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلظَّٰلِمِينَ
29. ከእነርሱም «እኔ ከእርሱ ሌላ አምላክ ነኝ።» የሚል ያንን ገሀነምን እንመነዳዋለን፤ በዳዮችን እንደዚሁ እንመነዳለን።
التفاسير العربية:
أَوَلَمۡ يَرَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ أَنَّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ كَانَتَا رَتۡقٗا فَفَتَقۡنَٰهُمَاۖ وَجَعَلۡنَا مِنَ ٱلۡمَآءِ كُلَّ شَيۡءٍ حَيٍّۚ أَفَلَا يُؤۡمِنُونَ
30. እነዚያም በአላህ የካዱ ሰዎች ሰማያትና ምድር የተጣበቁ የነበሩና የለያየናቸው መሆናችንን አያውቁምን? ህያው የሆነንም ነገር ሁሉ ከውሃ ፈጠርን። አያምኑምን?
التفاسير العربية:
وَجَعَلۡنَا فِي ٱلۡأَرۡضِ رَوَٰسِيَ أَن تَمِيدَ بِهِمۡ وَجَعَلۡنَا فِيهَا فِجَاجٗا سُبُلٗا لَّعَلَّهُمۡ يَهۡتَدُونَ
31. በምድርም ውስጥ በእነርሱ እንዳታረገርግ ጋራዎችን አደረግን። ይመሩም ዘንድ በእርሷ ውስጥ ሰፋፊ መንገዶችን አደረግን።
التفاسير العربية:
وَجَعَلۡنَا ٱلسَّمَآءَ سَقۡفٗا مَّحۡفُوظٗاۖ وَهُمۡ عَنۡ ءَايَٰتِهَا مُعۡرِضُونَ
32. ሰማይንም ከመውደቅ የተጠበቀ ጣራ አደረግን:: እነርሱ ግን ከተዓምራቱ ዘንጊዎች ናቸው::
التفاسير العربية:
وَهُوَ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلَّيۡلَ وَٱلنَّهَارَ وَٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَۖ كُلّٞ فِي فَلَكٖ يَسۡبَحُونَ
33.እርሱም ሌሊትንና ቀንን ጸሐይንና ጨረቃንም የፈጠረ ነው:: ሁሉም በየ ምህዋራቸው (ፈለካቸው) ውስጥ ይዋኛሉ::
التفاسير العربية:
وَمَا جَعَلۡنَا لِبَشَرٖ مِّن قَبۡلِكَ ٱلۡخُلۡدَۖ أَفَإِيْن مِّتَّ فَهُمُ ٱلۡخَٰلِدُونَ
34. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ለማንም ሰው ዘለዓለም መኖርን አላደረግንም:: ታዲያ ብትሞት እነርሱ ዘውታሪዎች ናቸውን?
التفاسير العربية:
كُلُّ نَفۡسٖ ذَآئِقَةُ ٱلۡمَوۡتِۗ وَنَبۡلُوكُم بِٱلشَّرِّ وَٱلۡخَيۡرِ فِتۡنَةٗۖ وَإِلَيۡنَا تُرۡجَعُونَ
35.(ሰዎች ሆይ!) ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት:: ለመፈተንም በክፉም በበጎም እንሞክራችኋለን:: ወደ እኛም ትመለሳላችሁ::
التفاسير العربية:
 
ترجمة معاني سورة: الأنبياء
فهرس السور رقم الصفحة
 
ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا - فهرس التراجم

ترجمها محمد زين زهر الدين. صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

إغلاق