للإطلاع على الموقع بحلته الجديدة

ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا * - فهرس التراجم


ترجمة معاني سورة: الروم   آية:
وَأَمَّا ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَكَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَلِقَآيِٕ ٱلۡأٓخِرَةِ فَأُوْلَٰٓئِكَ فِي ٱلۡعَذَابِ مُحۡضَرُونَ
16. እነዚያም በአላህ የካዱትማ በአናቅጻችንና በኋለኛይቱም ዓለም መገናኘት ያስተባበሉት እነዚያ በቅጣት ውስጥ የሚጣዱ ናቸው::
التفاسير العربية:
فَسُبۡحَٰنَ ٱللَّهِ حِينَ تُمۡسُونَ وَحِينَ تُصۡبِحُونَ
17. አላህንም በምታመሹና በምታነጉም ጊዜ አጥሩት::
التفاسير العربية:
وَلَهُ ٱلۡحَمۡدُ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَعَشِيّٗا وَحِينَ تُظۡهِرُونَ
18. ምስጋናም በሰማያትና በምድር ውስጥ ለእርሱ ብቻ የተገባው ነው:: በሰርክም በቀትር ውስጥ በምትገቡም ጊዜ አጥሩት::
التفاسير العربية:
يُخۡرِجُ ٱلۡحَيَّ مِنَ ٱلۡمَيِّتِ وَيُخۡرِجُ ٱلۡمَيِّتَ مِنَ ٱلۡحَيِّ وَيُحۡيِ ٱلۡأَرۡضَ بَعۡدَ مَوۡتِهَاۚ وَكَذَٰلِكَ تُخۡرَجُونَ
19. ህያውን ከሙት ያወጣል:: ሙትንም ከህያው ያወጣል:: ምድርንም ከሞተች በኋላ ህያው ያደርጋታል:: ልክ እንደዚሁም (ከመቃብር) ትወጣላችሁ::
التفاسير العربية:
وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦٓ أَنۡ خَلَقَكُم مِّن تُرَابٖ ثُمَّ إِذَآ أَنتُم بَشَرٞ تَنتَشِرُونَ
20. እናንተንም ከአፈር መፍጠሩ ከዚያም እናንተ ወዲያውኑ የምትበታተኑ ሰዎች መሆናችሁ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው::
التفاسير العربية:
وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦٓ أَنۡ خَلَقَ لَكُم مِّنۡ أَنفُسِكُمۡ أَزۡوَٰجٗا لِّتَسۡكُنُوٓاْ إِلَيۡهَا وَجَعَلَ بَيۡنَكُم مَّوَدَّةٗ وَرَحۡمَةًۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يَتَفَكَّرُونَ
21. ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ ሚስቶችን ወደ እነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው:: በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ተዐምራት አሉበት::
التفاسير العربية:
وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦ خَلۡقُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَٱخۡتِلَٰفُ أَلۡسِنَتِكُمۡ وَأَلۡوَٰنِكُمۡۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّلۡعَٰلِمِينَ
22. ሰማያትንና ምድርን መፍጠሩ የቋንቋዎቻችሁና የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው:: በዚህ ውስጥ ለአዋቂዎች አያሌ ታዐምራት አሉበት::
التفاسير العربية:
وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦ مَنَامُكُم بِٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِ وَٱبۡتِغَآؤُكُم مِّن فَضۡلِهِۦٓۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يَسۡمَعُونَ
23. በሌሊትም ሆነ በቀን መተኛታችሁ ከችሮታዉም መፈለጋችሁም ከምልክቶቹ ነው:: በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ህዝቦች ሁሉ ብዙ ታዐምራት አሉበት::
التفاسير العربية:
وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦ يُرِيكُمُ ٱلۡبَرۡقَ خَوۡفٗا وَطَمَعٗا وَيُنَزِّلُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَيُحۡيِۦ بِهِ ٱلۡأَرۡضَ بَعۡدَ مَوۡتِهَآۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يَعۡقِلُونَ
24. ብልጭታንም ፈሪዎችና ከጃዮች ስትሆኑ ለእናንተ ማሳየቱ ከሰማይም ውሃን ማውረዱ በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ህያው ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው:: በዚህ ውስጥ ለሚያስቡ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ታዐምራት አሉበት::
التفاسير العربية:
 
ترجمة معاني سورة: الروم
فهرس السور رقم الصفحة
 
ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا - فهرس التراجم

ترجمها محمد زين زهر الدين. صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

إغلاق