للإطلاع على الموقع بحلته الجديدة

ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا * - فهرس التراجم


ترجمة معاني سورة: الصافات   آية:
مَا لَكُمۡ كَيۡفَ تَحۡكُمُونَ
154. ለእናንተ ምን አስረጂ አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ!
التفاسير العربية:
أَفَلَا تَذَكَّرُونَ
155. አትገነዘቡምን?
التفاسير العربية:
أَمۡ لَكُمۡ سُلۡطَٰنٞ مُّبِينٞ
156. ወይስ ለእናንተ ግልጽ አስረጂ አላችሁን?
التفاسير العربية:
فَأۡتُواْ بِكِتَٰبِكُمۡ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
157. «እውነተኞች እንደሆናችሁ መጽሐፋችሁን አምጡ» በላቸው።
التفاسير العربية:
وَجَعَلُواْ بَيۡنَهُۥ وَبَيۡنَ ٱلۡجِنَّةِ نَسَبٗاۚ وَلَقَدۡ عَلِمَتِ ٱلۡجِنَّةُ إِنَّهُمۡ لَمُحۡضَرُونَ
158. በአላህና በአጋንንት መካከልም ዝምድናን አደረጉ:: አጋንንትም ሆኑ ይህን ባዩች በእሳት የሚጣዱ መሆናቸውን በእርግጥ አውቀዋል::
التفاسير العربية:
سُبۡحَٰنَ ٱللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ
159. አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ::
التفاسير العربية:
إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ
160. ግን የተመረጡት የአላህ ባሮች በአላህ ላይ አይዋሹም::
التفاسير العربية:
فَإِنَّكُمۡ وَمَا تَعۡبُدُونَ
161. (ካሐዲያን ሆይ!) እናንተም የምትገዟቸዉም ሁሉ፤
التفاسير العربية:
مَآ أَنتُمۡ عَلَيۡهِ بِفَٰتِنِينَ
162. በእርሱ በአላህ ላይ አንድንም አጥማሚዎች አይደላችሁም
التفاسير العربية:
إِلَّا مَنۡ هُوَ صَالِ ٱلۡجَحِيمِ
163. ያንን እርሱ ገሀነም ገቢ የሆነውን ቢሆን እንጂ (አጥማሚዎች አይደላችሁም)።
التفاسير العربية:
وَمَا مِنَّآ إِلَّا لَهُۥ مَقَامٞ مَّعۡلُومٞ
164. (መላእክቶችም አሉ)? «ከእኛ አንድም የለም፤ ለእርሱ የታወቀ ደረጃ ያለው ቢሆን እንጅ።
التفاسير العربية:
وَإِنَّا لَنَحۡنُ ٱلصَّآفُّونَ
165. «እኛም ጌታን ለመገዛት ተሰላፊዎቹ እኛ ነን።
التفاسير العربية:
وَإِنَّا لَنَحۡنُ ٱلۡمُسَبِّحُونَ
166. «እኛም አላህን አጥሪዎቹ እኛው ነን።»
التفاسير العربية:
وَإِن كَانُواْ لَيَقُولُونَ
167. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱ (ከሓዲያን) በእርግጥ ይሉ ነበር:
التفاسير العربية:
لَوۡ أَنَّ عِندَنَا ذِكۡرٗا مِّنَ ٱلۡأَوَّلِينَ
168. «ከቀድሞዎቹ መጽሐፍ ገሳጭ መጽሐፍ እኛ ዘንድ በነበረ ኖሮ
التفاسير العربية:
لَكُنَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ
169. «የአላህ ምርጦች ባሮች በሆን ነበር።»
التفاسير العربية:
فَكَفَرُواْ بِهِۦۖ فَسَوۡفَ يَعۡلَمُونَ
170. ግን ቁርኣኑ በመጣላቸው ጊዜ በእርሱ ላይ ካዱ። ወደ ፊትም በእርግጥ ያውቃሉ::
التفاسير العربية:
وَلَقَدۡ سَبَقَتۡ كَلِمَتُنَا لِعِبَادِنَا ٱلۡمُرۡسَلِينَ
171. የእርዳታ ቃላችንም መልዕክተኞች ለሆኑት ባሮቻችን በእውነት አልፋለች::
التفاسير العربية:
إِنَّهُمۡ لَهُمُ ٱلۡمَنصُورُونَ
172. እነርሱ ተረጂዎቹ እነርሱ ብቻ ናቸው::
التفاسير العربية:
وَإِنَّ جُندَنَا لَهُمُ ٱلۡغَٰلِبُونَ
173. ሰራዊቶቻችንም በእርግጥ አሸናፊዎቹ እነርሱ ናቸው::
التفاسير العربية:
فَتَوَلَّ عَنۡهُمۡ حَتَّىٰ حِينٖ
174. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ከመካ ከሓዲያን እስከ ጥቂት ጊዜ ድረስ ዙር ተዋቸው::
التفاسير العربية:
وَأَبۡصِرۡهُمۡ فَسَوۡفَ يُبۡصِرُونَ
175. ተመልከታቸዉም ወደፊትም የሚደርስባቸውን ያያሉ::
التفاسير العربية:
أَفَبِعَذَابِنَا يَسۡتَعۡجِلُونَ
176. በቅጣታችንም ያቻኩሉናልን?
التفاسير العربية:
فَإِذَا نَزَلَ بِسَاحَتِهِمۡ فَسَآءَ صَبَاحُ ٱلۡمُنذَرِينَ
177. በቀያቸዉም በወረደ ጊዜ የተስፈራሪዎቹ ንጋት ከፋ!
التفاسير العربية:
وَتَوَلَّ عَنۡهُمۡ حَتَّىٰ حِينٖ
178. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን እስከ ጥቂት ጊዜ ድረስ ተዋቸው::
التفاسير العربية:
وَأَبۡصِرۡ فَسَوۡفَ يُبۡصِرُونَ
179. ተመልከትም በእርግጥም ያያሉ::
التفاسير العربية:
سُبۡحَٰنَ رَبِّكَ رَبِّ ٱلۡعِزَّةِ عَمَّا يَصِفُونَ
180. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ::
التفاسير العربية:
وَسَلَٰمٌ عَلَى ٱلۡمُرۡسَلِينَ
181. በመልዕክተኞቹም ላይ ሰላም ይሁን::
التفاسير العربية:
وَٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
182. ምስጋና ሁሉም ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይገባው::
التفاسير العربية:
 
ترجمة معاني سورة: الصافات
فهرس السور رقم الصفحة
 
ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا - فهرس التراجم

ترجمها محمد زين زهر الدين. صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

إغلاق