للإطلاع على الموقع بحلته الجديدة

ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا * - فهرس التراجم


ترجمة معاني سورة: النساء   آية:
۞ لَّا خَيۡرَ فِي كَثِيرٖ مِّن نَّجۡوَىٰهُمۡ إِلَّا مَنۡ أَمَرَ بِصَدَقَةٍ أَوۡ مَعۡرُوفٍ أَوۡ إِصۡلَٰحِۭ بَيۡنَ ٱلنَّاسِۚ وَمَن يَفۡعَلۡ ذَٰلِكَ ٱبۡتِغَآءَ مَرۡضَاتِ ٱللَّهِ فَسَوۡفَ نُؤۡتِيهِ أَجۡرًا عَظِيمٗا
114. ከውይይቶቻቸው መካከል በምጽዋት ወይም በበጎ ስራ ወይም በሰዎች መካከል በማስታረቅ ከሚያዙ ሰዎች ውይይት በስተቀር በብዙው ውይይት ውስጥ ደግ ነገር የለበትም:: ይህንንም የተባለውን የአላህን ውዴታ በመፈለግ ለሚሰራ ሁሉ ታላቅ ምንዳን እንሰጠዋለን::
التفاسير العربية:
وَمَن يُشَاقِقِ ٱلرَّسُولَ مِنۢ بَعۡدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ ٱلۡهُدَىٰ وَيَتَّبِعۡ غَيۡرَ سَبِيلِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ نُوَلِّهِۦ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصۡلِهِۦ جَهَنَّمَۖ وَسَآءَتۡ مَصِيرًا
115. ቅኑ መንገድ ለእርሱ ከተገለጸት በኋላ መልዕክተኛውን የሚቃረንና ከምዕመናኖቹ መንገድ ሌላ የሆነን የሚከተል ሁሉ በመረጠው ጥመት ላይ እንተወዋለን። ወደ ገሀነምም እናስገባዋለን:: መመለሻይቱም ገሀነም ከፋች።
التفاسير العربية:
إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَغۡفِرُ أَن يُشۡرَكَ بِهِۦ وَيَغۡفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَآءُۚ وَمَن يُشۡرِكۡ بِٱللَّهِ فَقَدۡ ضَلَّ ضَلَٰلَۢا بَعِيدًا
116. አላህ በእርሱ ማጋራትን ፈጽሞ አይምርም:: ከሽርክ በታች (ሌላ) ያለውን ጥፋት ግን ለሚሻው ይምራል:: በአላህ የሚያጋራም ከእውነት የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ::
التفاسير العربية:
إِن يَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦٓ إِلَّآ إِنَٰثٗا وَإِن يَدۡعُونَ إِلَّا شَيۡطَٰنٗا مَّرِيدٗا
117. ከእርሱ ሌላ እንስት ጣኦታትን እንጂ አይገዙም:: አመጸኞች ሰይጣንንም እንጂ ሌላን አይገዙም::
التفاسير العربية:
لَّعَنَهُ ٱللَّهُۘ وَقَالَ لَأَتَّخِذَنَّ مِنۡ عِبَادِكَ نَصِيبٗا مَّفۡرُوضٗا
118. አላህም የረገመውን (እንዲህ) ያለውንም ሰይጣን እንጂ አይከተሉም: «ከባሮችህ የተወሰነን ድርሻ በእርግጥ እይዛለሁ።
التفاسير العربية:
وَلَأُضِلَّنَّهُمۡ وَلَأُمَنِّيَنَّهُمۡ وَلَأٓمُرَنَّهُمۡ فَلَيُبَتِّكُنَّ ءَاذَانَ ٱلۡأَنۡعَٰمِ وَلَأٓمُرَنَّهُمۡ فَلَيُغَيِّرُنَّ خَلۡقَ ٱللَّهِۚ وَمَن يَتَّخِذِ ٱلشَّيۡطَٰنَ وَلِيّٗا مِّن دُونِ ٱللَّهِ فَقَدۡ خَسِرَ خُسۡرَانٗا مُّبِينٗا
119. «በእርግጥ አጠማቸዋለሁ:: ከንቱን ምኞትም አስመኛቸዋለሁ:: አዛቸዉምና የእንስሶችን ጀሮዎች ይተለትላሉ:: አዛቸዉምና የአላህን ፍጥረት ይለውጣሉ።» (ያለውን ይከተላሉ።) ከአላህ ሌላ ሰይጣንን ረዳት አድርጎ የሚይዝ ግልጽ ኪሳራን በእርግጥ ከሰረ።
التفاسير العربية:
يَعِدُهُمۡ وَيُمَنِّيهِمۡۖ وَمَا يَعِدُهُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ إِلَّا غُرُورًا
120. የማይፈጽመውን ከንቱ ተስፋ ይሰጣቸዋል:: ያስመኛቸዋልም:: ሰይጣን ለማታለል እንጂ ቃል አይገባላቸዉም::
التفاسير العربية:
أُوْلَٰٓئِكَ مَأۡوَىٰهُمۡ جَهَنَّمُ وَلَا يَجِدُونَ عَنۡهَا مَحِيصٗا
121. እነዚያ የመጨረሻ መኖሪያቸው ገሀነም ናት:: ከእርሷም መሸሻን አያገኙም::
التفاسير العربية:
 
ترجمة معاني سورة: النساء
فهرس السور رقم الصفحة
 
ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا - فهرس التراجم

ترجمها محمد زين زهر الدين. صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

إغلاق