للإطلاع على الموقع بحلته الجديدة

ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا * - فهرس التراجم

PDF XML CSV Excel API
تنزيل الملفات يتضمن الموافقة على هذه الشروط والسياسات

ترجمة معاني سورة: الأنعام   آية:
۞ وَإِذۡ قَالَ إِبۡرَٰهِيمُ لِأَبِيهِ ءَازَرَ أَتَتَّخِذُ أَصۡنَامًا ءَالِهَةً إِنِّيٓ أَرَىٰكَ وَقَوۡمَكَ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ
74. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂም ለአባቱ ለአዘር፡- «ጣኦትን አማልክት ታደርጋለህን? እኔ አንተንም ወገኖችህንም ግልጽ ጥመት ውስጥ ሆናችሁ አየኋችሁ።» ባለው ጊዜ የሆነውን አስታውስ::
التفاسير العربية:
وَكَذَٰلِكَ نُرِيٓ إِبۡرَٰهِيمَ مَلَكُوتَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَلِيَكُونَ مِنَ ٱلۡمُوقِنِينَ
75. ልክ በዚህ አኳኋን ኢብራሂም ጽኑ እምነት ይኖረው ዘንድ የሰማያትንና የምድርን ግዛት አሳየነው::
التفاسير العربية:
فَلَمَّا جَنَّ عَلَيۡهِ ٱلَّيۡلُ رَءَا كَوۡكَبٗاۖ قَالَ هَٰذَا رَبِّيۖ فَلَمَّآ أَفَلَ قَالَ لَآ أُحِبُّ ٱلۡأٓفِلِينَ
76. ሌሊቱ በጽልመቱ በሸፈነው ጊዜ አንድ ኮከብ አየ። «ይህ ጌታዬ ነው» አለም:: ኮከቡ በጠለቀ ጊዜም፡- «ጠላቂዎችን አልወድም» አለ::
التفاسير العربية:
فَلَمَّا رَءَا ٱلۡقَمَرَ بَازِغٗا قَالَ هَٰذَا رَبِّيۖ فَلَمَّآ أَفَلَ قَالَ لَئِن لَّمۡ يَهۡدِنِي رَبِّي لَأَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلضَّآلِّينَ
77. ጨረቃውን ደምቆ ባየ ጊዜም፡- «ይህ ጌታዬ ነው።» አለ:: ጨረቃውም በጠለቀ ጊዜ፡- «ጌታዬ ቅኑን ጎዳና ካልመራኝ መንገድ ከተሳሳቱ ሰዎች እሆናለሁ።» አለ።
التفاسير العربية:
فَلَمَّا رَءَا ٱلشَّمۡسَ بَازِغَةٗ قَالَ هَٰذَا رَبِّي هَٰذَآ أَكۡبَرُۖ فَلَمَّآ أَفَلَتۡ قَالَ يَٰقَوۡمِ إِنِّي بَرِيٓءٞ مِّمَّا تُشۡرِكُونَ
78. ጸሐይዋንም ደምቃ ጮራዋን ባየ ጊዜ፡- «ይህ ጌታዬ ነው። ይህ በጣም ትልቅ ነው።» አለ:: በጠለቀችም ጊዜ (አንዲህ) አለ፡- «ወገኖቼ ሆይ! እኔ ከምታጋሩት ሁሉ የጠራሁ ነኝ።
التفاسير العربية:
إِنِّي وَجَّهۡتُ وَجۡهِيَ لِلَّذِي فَطَرَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ حَنِيفٗاۖ وَمَآ أَنَا۠ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ
79. «እኔ ወደ ቀጥተኛው ሃይማኖት የተዘነበልኩ ስሆን ፊቴን ሰማያትንና ምድርን ወደ ፈጠረው አምላክ አላህ አዙሬያለሁ:: እናም ከአጋሪዎችም አይደለሁም።» (አለ)።
التفاسير العربية:
وَحَآجَّهُۥ قَوۡمُهُۥۚ قَالَ أَتُحَٰٓجُّوٓنِّي فِي ٱللَّهِ وَقَدۡ هَدَىٰنِۚ وَلَآ أَخَافُ مَا تُشۡرِكُونَ بِهِۦٓ إِلَّآ أَن يَشَآءَ رَبِّي شَيۡـٔٗاۚ وَسِعَ رَبِّي كُلَّ شَيۡءٍ عِلۡمًاۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُونَ
80. ወገኖቹም ተከራከሩት። (እርሱም) አላቸው: «በእርግጥ የመራኝ ስሆን በአላህ ጉዳይ ትከራከሩኛላችሁን? በእርሱም የምታጋሩትን ነገር አልፈራም:: ግን ጌታዬ ቢሻ (ያገኘኛል):: ጌታዬም ሁሉንም ነገር በእውቀቱ ሰፋ። አትገነዘቡምን?
التفاسير العربية:
وَكَيۡفَ أَخَافُ مَآ أَشۡرَكۡتُمۡ وَلَا تَخَافُونَ أَنَّكُمۡ أَشۡرَكۡتُم بِٱللَّهِ مَا لَمۡ يُنَزِّلۡ بِهِۦ عَلَيۡكُمۡ سُلۡطَٰنٗاۚ فَأَيُّ ٱلۡفَرِيقَيۡنِ أَحَقُّ بِٱلۡأَمۡنِۖ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ
81. «በእናንተ ላይ በእርሱ ማስረጃ ያላወረደበትን እናንተ ማጋራታችሁን የማትፈሩ ስትሆኑ የምታጋሩትን ጣዖት እንዴት እኔ እፈራለሁ?! የምታውቁም ብትሆኑ ከሁለቱ ክፍሎች ደህና ለመሆን ይበልጥ ተገቢው ማንኛው ነው?» አለ።
التفاسير العربية:
 
ترجمة معاني سورة: الأنعام
فهرس السور رقم الصفحة
 
ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا - فهرس التراجم

ترجمها محمد زين زهر الدين. صادرة عن أكاديمية أفريقيا.

إغلاق