Check out the new design

আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ- মুহাম্মদ ছাদিক * - অনুবাদসমূহৰ সূচীপত্ৰ

XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

অৰ্থানুবাদ ছুৰা: আল-ফাতাহ   আয়াত:
إِنَّ ٱلَّذِينَ يُبَايِعُونَكَ إِنَّمَا يُبَايِعُونَ ٱللَّهَ يَدُ ٱللَّهِ فَوۡقَ أَيۡدِيهِمۡۚ فَمَن نَّكَثَ فَإِنَّمَا يَنكُثُ عَلَىٰ نَفۡسِهِۦۖ وَمَنۡ أَوۡفَىٰ بِمَا عَٰهَدَ عَلَيۡهُ ٱللَّهَ فَسَيُؤۡتِيهِ أَجۡرًا عَظِيمٗا
እነዚያ ቃል ኪዳን የሚጋቡህ ቃል ኪዳን የሚጋቡት አላህን ብቻ ነው፡፡ የአላህ እጅ ከእጆቻቸው በላይ ነው፡፡ ያፈረሰም ሰው የሚያፈርሰው በነፍሱ ላይ ብቻ ነው፡፡ በእርሱ ላይ አላህን ቃል ኪዳን የተጋባበትን የሞላም ሰው ታላቅ ምንዳን በእርግጥ ይሰጠዋል፡፡
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
سَيَقُولُ لَكَ ٱلۡمُخَلَّفُونَ مِنَ ٱلۡأَعۡرَابِ شَغَلَتۡنَآ أَمۡوَٰلُنَا وَأَهۡلُونَا فَٱسۡتَغۡفِرۡ لَنَاۚ يَقُولُونَ بِأَلۡسِنَتِهِم مَّا لَيۡسَ فِي قُلُوبِهِمۡۚ قُلۡ فَمَن يَمۡلِكُ لَكُم مِّنَ ٱللَّهِ شَيۡـًٔا إِنۡ أَرَادَ بِكُمۡ ضَرًّا أَوۡ أَرَادَ بِكُمۡ نَفۡعَۢاۚ بَلۡ كَانَ ٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ خَبِيرَۢا
ከአዕራብ ሰዎች እነዚያ (ከዘመቻ) ወደ ኋላ የቀሩት ለአንተ «ገንዘቦቻችንና ቤተሰቦቻችን አስቸገሩን፤ ስለዚህ ምሕረትን ለምንልን፤» ይሉሃል፡፡ በልቦቻቸው ውስጥ የሌለውን ነገር በምላሶቻቸው ይናገራሉ፡፡ (አላህ) «በእናንተ ላይ ጉዳትን ቢሻ ወይም በእናንተ መጥቀምን ቢሻ ከአላህ (ለማገድ) ለእናንተ አንዳችን የሚችል ማነው? በእውነቱ አላህ፤በምትሠሰሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
بَلۡ ظَنَنتُمۡ أَن لَّن يَنقَلِبَ ٱلرَّسُولُ وَٱلۡمُؤۡمِنُونَ إِلَىٰٓ أَهۡلِيهِمۡ أَبَدٗا وَزُيِّنَ ذَٰلِكَ فِي قُلُوبِكُمۡ وَظَنَنتُمۡ ظَنَّ ٱلسَّوۡءِ وَكُنتُمۡ قَوۡمَۢا بُورٗا
ይልቁንም መልክተኛውና ምእመናኖቹ ወደ ቤተሰቦቻቸው ፈጽሞ አለመመለሳቸውን ጠረጠራችሁ፡፡ ይህም በልቦቻችሁ ውስጥ ተሸለመላችሁ፡፡ መጥፎንም መጠርጠር ጠረጠራችሁ፡፡ ጠፊዎች ሕዝቦችም ኾናችሁ፡፡
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
وَمَن لَّمۡ يُؤۡمِنۢ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ فَإِنَّآ أَعۡتَدۡنَا لِلۡكَٰفِرِينَ سَعِيرٗا
በአላህና በመልክተኛው ያላመነም ሰው እኛ ላከሓዲዎች እሳትን አዘጋጅተናል፡፡
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
وَلِلَّهِ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ يَغۡفِرُ لِمَن يَشَآءُ وَيُعَذِّبُ مَن يَشَآءُۚ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورٗا رَّحِيمٗا
የሰማያትና የምድር ንግሥናም የአላህ ነው፡፡ ለሚሻው ሰው ይምራል፤ የሚሻውንም ይቀጣል፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
سَيَقُولُ ٱلۡمُخَلَّفُونَ إِذَا ٱنطَلَقۡتُمۡ إِلَىٰ مَغَانِمَ لِتَأۡخُذُوهَا ذَرُونَا نَتَّبِعۡكُمۡۖ يُرِيدُونَ أَن يُبَدِّلُواْ كَلَٰمَ ٱللَّهِۚ قُل لَّن تَتَّبِعُونَا كَذَٰلِكُمۡ قَالَ ٱللَّهُ مِن قَبۡلُۖ فَسَيَقُولُونَ بَلۡ تَحۡسُدُونَنَاۚ بَلۡ كَانُواْ لَا يَفۡقَهُونَ إِلَّا قَلِيلٗا
ወደ ምርኮዎች ልትይዟት በኼዳችሁ ጊዜ እነዚያ ወደ ኋላ የቀሩት ሰዎች «ተዉን እንከተላችሁ» ይሏችኋል፡፡ (በዚህም) የአላህን ቃል ሊለውጡ ይፈልጋሉ፡፡ «ፈጽሞ አትከተሉንም፡፡ ይህን (ቃል) ከዚህ በፊት አላህ ብሏል» በላቸው፡፡ ይልቁንም «ትመቀኙናላችሁ» ይላሉም፡፡ በእውነት እነርሱ ጥቂትን እንጅ የማያውቁ ነበሩ፡፡
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
 
অৰ্থানুবাদ ছুৰা: আল-ফাতাহ
ছুৰাৰ তালিকা পৃষ্ঠা নং
 
আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ- মুহাম্মদ ছাদিক - অনুবাদসমূহৰ সূচীপত্ৰ

অনুবাদ কৰিছে শ্বাইখ মুহাম্মদ চাদিক্ব আৰু মুহাম্মদ ছানী হাবীব চাহাবে। মৰ্কজ ৰুৱাদুত তাৰ্জামাৰ তত্ত্বাৱধানত ইয়াক উন্নীত কৰা হৈছে। ধাৰাবাহিক উন্নীত কৰণ, মূল্যায়ন আৰু মতামত প্ৰকাশৰ উদ্দেশ্যে মূল অনুবাদটো উন্মুক্ত কৰা হ'ল।

বন্ধ