Check out the new design

আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী * - অনুবাদসমূহৰ সূচীপত্ৰ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

অৰ্থানুবাদ ছুৰা: হূদ   আয়াত:
أُوْلَٰٓئِكَ لَمۡ يَكُونُواْ مُعۡجِزِينَ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَا كَانَ لَهُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ مِنۡ أَوۡلِيَآءَۘ يُضَٰعَفُ لَهُمُ ٱلۡعَذَابُۚ مَا كَانُواْ يَسۡتَطِيعُونَ ٱلسَّمۡعَ وَمَا كَانُواْ يُبۡصِرُونَ
20. እነዚያም በምድር ውስጥ ከአላህ የሚያመልጡ አልነበሩም:: ከአላህ ሌላ ለእነርሱ ረዳቶች አልነበሯቸዉም:: ለእነርሱ ቅጣቱ ይደራረብላቸዋል:: እውነትን መስማትን የሚችሉ አልነበሩም:: የሚያዩም አልነበሩም::
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ وَضَلَّ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَفۡتَرُونَ
21. እነዚያ እነርሱ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩና ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር የጠፋባቸው ናቸው::
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
لَا جَرَمَ أَنَّهُمۡ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ هُمُ ٱلۡأَخۡسَرُونَ
22. እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም በጣም ከሳሪዎቹ ለመሆናቸው ጥርጥር የለዉም።
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَأَخۡبَتُوٓاْ إِلَىٰ رَبِّهِمۡ أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡجَنَّةِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ
23. እነዚያ ያመኑትና በጎ ሥራዎችን የሠሩት ወደ ጌታቸዉም የተዋረዱት እነዚያ የገነት ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው::
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
۞ مَثَلُ ٱلۡفَرِيقَيۡنِ كَٱلۡأَعۡمَىٰ وَٱلۡأَصَمِّ وَٱلۡبَصِيرِ وَٱلسَّمِيعِۚ هَلۡ يَسۡتَوِيَانِ مَثَلًاۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ
24. የሁለቱ ክፍሎች ምሳሌ አይኑ የማያይ አይነ ስውር፤ ጆሮው የማይሰማ ደንቆሮ ሰውና አይኑ የሚያይ ጆሮው የሚሰማ ሰው ብጤ ነው:: ሁለቱ በምሳሌነት ይስተካከላሉን? አትገሰጹንም?
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوۡمِهِۦٓ إِنِّي لَكُمۡ نَذِيرٞ مُّبِينٌ
25. ኑሕን ወደ ህዝቦቹ ላክንና አላቸዉም: «እኔ ለእናንተ ግልጽ አስፈራሪ ነኝ።
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
أَن لَّا تَعۡبُدُوٓاْ إِلَّا ٱللَّهَۖ إِنِّيٓ أَخَافُ عَلَيۡكُمۡ عَذَابَ يَوۡمٍ أَلِيمٖ
26. «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ። እኔ ለእናንተ የአሳማሚን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁና።»
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
فَقَالَ ٱلۡمَلَأُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِن قَوۡمِهِۦ مَا نَرَىٰكَ إِلَّا بَشَرٗا مِّثۡلَنَا وَمَا نَرَىٰكَ ٱتَّبَعَكَ إِلَّا ٱلَّذِينَ هُمۡ أَرَاذِلُنَا بَادِيَ ٱلرَّأۡيِ وَمَا نَرَىٰ لَكُمۡ عَلَيۡنَا مِن فَضۡلِۭ بَلۡ نَظُنُّكُمۡ كَٰذِبِينَ
27. ከህዝቦቹም መካከል እነዚያ የካዱት መሪዎች «ብጤያችን ሰው ሆነህ እንጂ አናይህም:: እነዚያም እነርሱ ሐሳበ ጥሬዎች የሆኑት ወራዶቻችን እንጂ ሌላ ተከትሎህ አናይህም:: ለእናንተም በእኛ ላይ ምንም ብልጫን አናይም:: ከቶውንም ውሸታሞች መሆናችሁን እንጠረጥራችኋለን።» አሉ።
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
قَالَ يَٰقَوۡمِ أَرَءَيۡتُمۡ إِن كُنتُ عَلَىٰ بَيِّنَةٖ مِّن رَّبِّي وَءَاتَىٰنِي رَحۡمَةٗ مِّنۡ عِندِهِۦ فَعُمِّيَتۡ عَلَيۡكُمۡ أَنُلۡزِمُكُمُوهَا وَأَنتُمۡ لَهَا كَٰرِهُونَ
28. እርሱም አላቸው: «ህዝቦቼ ሆይ! እስቲ ንገሩኝ ከጌታዬ በግልጽ ማስረጃ ላይ ሆኜ ከእርሱም ዘንድ የሆነን ችሮታ ነብይነት ቢሰጠኝና በእናንተ ላይ ግን ይህች እውነታ ብትደበቅባችሁ እናንተ ለእርሷ ጠይዎች ስትሆኑ እርሷን በመቀበል እናስገድዳችኋለንን?
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
 
অৰ্থানুবাদ ছুৰা: হূদ
ছুৰাৰ তালিকা পৃষ্ঠা নং
 
আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী - অনুবাদসমূহৰ সূচীপত্ৰ

মুহাম্মদ ঝাইন জহৰুদ্দিনৰ অনুবাদ। আফ্ৰিকা একাডেমীৰ পৰা প্ৰকাশিত।

বন্ধ