Check out the new design

আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী * - অনুবাদসমূহৰ সূচীপত্ৰ


অৰ্থানুবাদ ছুৰা: ফাতিৰ   আয়াত:
وَإِن يُكَذِّبُوكَ فَقَدۡ كُذِّبَتۡ رُسُلٞ مِّن قَبۡلِكَۚ وَإِلَى ٱللَّهِ تُرۡجَعُ ٱلۡأُمُورُ
4. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢያስተባብሉህም ካንተ በፊት የነበሩ ነብያትም ህዝቦቻቸው አስተባብለዋቸዋል:: የሁሉ ነገር መመለሻ ወደ አላህ ብቻ ነው::
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقّٞۖ فَلَا تَغُرَّنَّكُمُ ٱلۡحَيَوٰةُ ٱلدُّنۡيَا وَلَا يَغُرَّنَّكُم بِٱللَّهِ ٱلۡغَرُورُ
5. (እናንተ ሰዎች ሆይ!) የአላህ ቀጠሮ እውነት ነው:: እናም የቅርቢቱም ህይወት አታታላችሁ:: አታላዩም (ሰይጣን) በአላህ ላይ አያታላችሁ::
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
إِنَّ ٱلشَّيۡطَٰنَ لَكُمۡ عَدُوّٞ فَٱتَّخِذُوهُ عَدُوًّاۚ إِنَّمَا يَدۡعُواْ حِزۡبَهُۥ لِيَكُونُواْ مِنۡ أَصۡحَٰبِ ٱلسَّعِيرِ
6. ሰይጣን ለእናንተ የለየለት ጠላት ነውና ስለዚህ እሱን ጠላት አድርጋችሁ ያዙት:: ሰይጣን ተከታዮቹን የሚጠራው ከእሳት ጓዶች እንዲሆኑ ብቻ ነው::
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَهُمۡ عَذَابٞ شَدِيدٞۖ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَهُم مَّغۡفِرَةٞ وَأَجۡرٞ كَبِيرٌ
7. እነዚያ በአላህ የካዱት ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አለባቸው:: እነዚያም በአላህ ያመኑትና በጎ ስራዎችንም የሰሩት ሁሉ ለእነርሱ በአላህ ዘንድ ምህረትና ታላቅ ምንዳ አለላቸው።
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
أَفَمَن زُيِّنَ لَهُۥ سُوٓءُ عَمَلِهِۦ فَرَءَاهُ حَسَنٗاۖ فَإِنَّ ٱللَّهَ يُضِلُّ مَن يَشَآءُ وَيَهۡدِي مَن يَشَآءُۖ فَلَا تَذۡهَبۡ نَفۡسُكَ عَلَيۡهِمۡ حَسَرَٰتٍۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمُۢ بِمَا يَصۡنَعُونَ
8. መጥፎ ሥራው የተሸለመለትና መልካም አድርጎ ያየው ሰው (አላህ እንዳቀናው ሰው ነውን?) አላህም የሚሻውን ሰው ያጠምማል፡፡ የሚሻውንም ያቀናል፡፡ ስለዚህ በእነርሱ ላይ (ባለመቅናታቸው) ስለመቆላጨት ነፍስህ አትጥፋ፡፡ አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
وَٱللَّهُ ٱلَّذِيٓ أَرۡسَلَ ٱلرِّيَٰحَ فَتُثِيرُ سَحَابٗا فَسُقۡنَٰهُ إِلَىٰ بَلَدٖ مَّيِّتٖ فَأَحۡيَيۡنَا بِهِ ٱلۡأَرۡضَ بَعۡدَ مَوۡتِهَاۚ كَذَٰلِكَ ٱلنُّشُورُ
9. አላህም ያ ንፋሶችን የላከ ነው:: ከዚያም ዳመናዎችን ትቀሰቅሳለች። ወደ ሙት (ድርቅ) አገርም እንነዳዋለን:: በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ህያው እናደርጋታለን:: ሙታንንም መቀስቀስ ልክ እነደዚሁ ነው::
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
مَن كَانَ يُرِيدُ ٱلۡعِزَّةَ فَلِلَّهِ ٱلۡعِزَّةُ جَمِيعًاۚ إِلَيۡهِ يَصۡعَدُ ٱلۡكَلِمُ ٱلطَّيِّبُ وَٱلۡعَمَلُ ٱلصَّٰلِحُ يَرۡفَعُهُۥۚ وَٱلَّذِينَ يَمۡكُرُونَ ٱلسَّيِّـَٔاتِ لَهُمۡ عَذَابٞ شَدِيدٞۖ وَمَكۡرُ أُوْلَٰٓئِكَ هُوَ يَبُورُ
10. ማሸነፍን የሚፈልግ ሰው አሸናፊነት ለአላህ ብቻ ነው። (እርሱን በመገዛት ይፈልገው):: መልካም ንግግር ወደ እርሱ (ወደ አላህ) ይወጣል:: በጎ ስራም ከፍ ያደርገዋል:: እነዚያ መጥፎ ስራዎችን የሚዶልቱ ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አለባቸው :: የእነዚያም ተንኮል እርሱ ይጠፋል::
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
وَٱللَّهُ خَلَقَكُم مِّن تُرَابٖ ثُمَّ مِن نُّطۡفَةٖ ثُمَّ جَعَلَكُمۡ أَزۡوَٰجٗاۚ وَمَا تَحۡمِلُ مِنۡ أُنثَىٰ وَلَا تَضَعُ إِلَّا بِعِلۡمِهِۦۚ وَمَا يُعَمَّرُ مِن مُّعَمَّرٖ وَلَا يُنقَصُ مِنۡ عُمُرِهِۦٓ إِلَّا فِي كِتَٰبٍۚ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٞ
11. አላህም ከአፈር ከዚያም ከፍትወት ጠብታ ፈጠራችሁ:: ከዚያም ዓይነቶች አደረጋችሁ:: የትኛዋም ሴት አታረግዝም አትወልድምም በእውቀቱ ቢሆን አንጂ:: እድሜው ከሚረዝምለትም አንድም አይረዘምለትም ከእድሜዉም አይጎድልበትም በመጽሀፉ ውስጥ ያለ ቢሆን እንጂ:: ይህ በአላህ ላይ ገር ነው::
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
 
অৰ্থানুবাদ ছুৰা: ফাতিৰ
ছুৰাৰ তালিকা পৃষ্ঠা নং
 
আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ - আফ্ৰিকা একাডেমী - অনুবাদসমূহৰ সূচীপত্ৰ

মুহাম্মদ ঝাইন জহৰুদ্দিনৰ অনুবাদ। আফ্ৰিকা একাডেমীৰ পৰা প্ৰকাশিত।

বন্ধ