Check out the new design

Qurani Kərimin mənaca tərcüməsi - Amhar dilinə tərcümə - Afrika Akademiyası. * - Tərcumənin mündəricatı

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Mənaların tərcüməsi Surə: əl-Ənam   Ayə:
وَكَذَٰلِكَ فَتَنَّا بَعۡضَهُم بِبَعۡضٖ لِّيَقُولُوٓاْ أَهَٰٓؤُلَآءِ مَنَّ ٱللَّهُ عَلَيۡهِم مِّنۢ بَيۡنِنَآۗ أَلَيۡسَ ٱللَّهُ بِأَعۡلَمَ بِٱلشَّٰكِرِينَ
53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁም «ከመካከላችን አላህ በእነርሱ ላይ ችሮታውን የለገሳቸው እነዚህ ናቸውን?» ይሉ ዘንድ ከፊላቸውን በከፊሎች ሞከርን:: አላህ አመስጋኞቹን ከሁሉም በላይ አዋቂ አይደለምን?
Ərəbcə təfsirlər:
وَإِذَا جَآءَكَ ٱلَّذِينَ يُؤۡمِنُونَ بِـَٔايَٰتِنَا فَقُلۡ سَلَٰمٌ عَلَيۡكُمۡۖ كَتَبَ رَبُّكُمۡ عَلَىٰ نَفۡسِهِ ٱلرَّحۡمَةَ أَنَّهُۥ مَنۡ عَمِلَ مِنكُمۡ سُوٓءَۢا بِجَهَٰلَةٖ ثُمَّ تَابَ مِنۢ بَعۡدِهِۦ وَأَصۡلَحَ فَأَنَّهُۥ غَفُورٞ رَّحِيمٞ
54. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በተዐምራታችን የሚያምኑት ሰዎች ሁሉ ወደ አንተ በመጡ ጊዜ «ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን:: ጌታችን በራሱ ላይ እዝነትን ፃፈ:: እነሆ ከናንተ ውስጥ ስህተትን ስራ የሰራና ከዚያ ተጸጽቶ ወዲያውኑ ስራውን ላሳመረ እርሱ (አላህ) መሀሪና አዛኝ ነው።» በላቸው።
Ərəbcə təfsirlər:
وَكَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ ٱلۡأٓيَٰتِ وَلِتَسۡتَبِينَ سَبِيلُ ٱلۡمُجۡرِمِينَ
55. ልክ እንደዚሁም እውነቱ እንዲገለጽና የወንጀለኞችም መንገድ ትብራራ ዘንድ አናቅጽን እንገልፃለን::
Ərəbcə təfsirlər:
قُلۡ إِنِّي نُهِيتُ أَنۡ أَعۡبُدَ ٱلَّذِينَ تَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِۚ قُل لَّآ أَتَّبِعُ أَهۡوَآءَكُمۡ قَدۡ ضَلَلۡتُ إِذٗا وَمَآ أَنَا۠ مِنَ ٱلۡمُهۡتَدِينَ
56. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትጠሯቸውን (ባዕድ አማልክት) ከመገዛት ተከልክያለሁ።» በላቸው። «ዝንባሌያችሁንም አልከተልም:: ያን ካደረኩኝ በእርግጥ ተሳሳትኩ:: እኔም ከተመሪዎቹ አይደለሁም።» በላቸው።
Ərəbcə təfsirlər:
قُلۡ إِنِّي عَلَىٰ بَيِّنَةٖ مِّن رَّبِّي وَكَذَّبۡتُم بِهِۦۚ مَا عِندِي مَا تَسۡتَعۡجِلُونَ بِهِۦٓۚ إِنِ ٱلۡحُكۡمُ إِلَّا لِلَّهِۖ يَقُصُّ ٱلۡحَقَّۖ وَهُوَ خَيۡرُ ٱلۡفَٰصِلِينَ
57. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎች ሆይ! እኔ ከጌታዬ በመጣልኝ ግልጽ ማስረጃ ላይ ነኝ:: እናንተ ግን በእርሱ አስተባበላችሁ:: ያ የምትቻኮሉበት ቅጣት ውሳኔ እኔ ዘንድ አይደለም:: ፍርዱ ለአላህ ብቻ ነው:: አላህ እውነቱን ይፈርዳል:: እርሱም ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነውና።» በላቸው።
Ərəbcə təfsirlər:
قُل لَّوۡ أَنَّ عِندِي مَا تَسۡتَعۡجِلُونَ بِهِۦ لَقُضِيَ ٱلۡأَمۡرُ بَيۡنِي وَبَيۡنَكُمۡۗ وَٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِٱلظَّٰلِمِينَ
58. «ያ የምትቻኮሉበት ቅጣት እኔ ዘንድ በሆነ ኖሮ በእኔና በእናንተ መካከል ነገሩ (ቅጣታችሁ) በተፈጸመ ነበር:: አላህ በደለኞችን አዋቂ ነው።» በላቸው::
Ərəbcə təfsirlər:
۞ وَعِندَهُۥ مَفَاتِحُ ٱلۡغَيۡبِ لَا يَعۡلَمُهَآ إِلَّا هُوَۚ وَيَعۡلَمُ مَا فِي ٱلۡبَرِّ وَٱلۡبَحۡرِۚ وَمَا تَسۡقُطُ مِن وَرَقَةٍ إِلَّا يَعۡلَمُهَا وَلَا حَبَّةٖ فِي ظُلُمَٰتِ ٱلۡأَرۡضِ وَلَا رَطۡبٖ وَلَا يَابِسٍ إِلَّا فِي كِتَٰبٖ مُّبِينٖ
59. የሩቅ ሚስጥሮች መክፈቻዎች ሁሉ እርሱ ዘንድ ብቻ ናቸው:: ከእርሱ በስተቀር ማንም አያውቃቸዉም:: በየብስና በባህር ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል:: አንዲትም ቅጠል አትረግፍም አላህ የሚያውቃት ብትሆን እንጂ:: በመሬት ጨለማዎች ውስጥ ቅንጣት እርጥብም ሆነ ደረቅ አንድም ነገር የለም ግልጽ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ ቢሆን እንጂ::
Ərəbcə təfsirlər:
 
Mənaların tərcüməsi Surə: əl-Ənam
Surələrin mündəricatı Səhifənin rəqəmi
 
Qurani Kərimin mənaca tərcüməsi - Amhar dilinə tərcümə - Afrika Akademiyası. - Tərcumənin mündəricatı

Tərcüməsi Məhəmməd Zeyn Zöhrəddin. Afrika Akademiyası tərəfindən nəşr olunub.

Bağlamaq