Check out the new design

Qurani Kərimin mənaca tərcüməsi - Amhar dilinə tərcümə - Afrika Akademiyası. * - Tərcumənin mündəricatı

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

Mənaların tərcüməsi Surə: əl-Ənam   Ayə:
وَهُوَ ٱلَّذِي يَتَوَفَّىٰكُم بِٱلَّيۡلِ وَيَعۡلَمُ مَا جَرَحۡتُم بِٱلنَّهَارِ ثُمَّ يَبۡعَثُكُمۡ فِيهِ لِيُقۡضَىٰٓ أَجَلٞ مُّسَمّٗىۖ ثُمَّ إِلَيۡهِ مَرۡجِعُكُمۡ ثُمَّ يُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
60. እርሱ (አላህ) ያ በሌሊት የሚያስተኛችሁ በቀን የሰራችሁትንም ሁሉ የሚያውቅ ከዚያም የተወሰነው ጊዜ ይፈጸም ዘንድ በቀን ውስጥ የሚቀሰቅሳችሁ ነው:: ከዚያም መመለሻችሁ ወደ እርሱ ብቻ ነው:: ከዚያም ትሰሩት የነበራችሁትን ነገር ሁሉ ይነግራችኋል::
Ərəbcə təfsirlər:
وَهُوَ ٱلۡقَاهِرُ فَوۡقَ عِبَادِهِۦۖ وَيُرۡسِلُ عَلَيۡكُمۡ حَفَظَةً حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَ أَحَدَكُمُ ٱلۡمَوۡتُ تَوَفَّتۡهُ رُسُلُنَا وَهُمۡ لَا يُفَرِّطُونَ
61. እርሱ ከባሮቹ በላይ ሲሆን ሁሉን አሸናፊ ነው:: በእናንተ ላይም ተጠባባቂዎች መላዕክትን ይልካል:: አንዳችሁንም የሞት ሰዓቱ በመጣበት ጊዜ የሞት መልዕክተኞቻችን ትዕዛዛትን የማያጓድሉ ሲሆኑ ይገድሉታል::
Ərəbcə təfsirlər:
ثُمَّ رُدُّوٓاْ إِلَى ٱللَّهِ مَوۡلَىٰهُمُ ٱلۡحَقِّۚ أَلَا لَهُ ٱلۡحُكۡمُ وَهُوَ أَسۡرَعُ ٱلۡحَٰسِبِينَ
62. ከዚያም እውነተኛ ወደ ሆነው ጌታቸው ወደ አላህ ይመለሳሉ:: (ሰዎች ሆይ!) አስትዉሉ! አዋጅ ፍርዱ ለእርሱ ብቻ ነው:: እርሱም ከተቆጣጣሪዎች ሁሉ ይበልጥ ፈጣን ነው::
Ərəbcə təfsirlər:
قُلۡ مَن يُنَجِّيكُم مِّن ظُلُمَٰتِ ٱلۡبَرِّ وَٱلۡبَحۡرِ تَدۡعُونَهُۥ تَضَرُّعٗا وَخُفۡيَةٗ لَّئِنۡ أَنجَىٰنَا مِنۡ هَٰذِهِۦ لَنَكُونَنَّ مِنَ ٱلشَّٰكِرِينَ
63. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያ ከየብስና ከባህር ጨለማዎች በግልጽና በሚስጢር ‹ከዚህ ቢያድነን ከአመስጋኞች እንሆናለን› ስትሉ የምትጠሩት ስትሆኑ የሚያድናችሁ ማን ነው?» በላቸው።
Ərəbcə təfsirlər:
قُلِ ٱللَّهُ يُنَجِّيكُم مِّنۡهَا وَمِن كُلِّ كَرۡبٖ ثُمَّ أَنتُمۡ تُشۡرِكُونَ
64. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ከእርሷና ከጭንቅም ሁሉ ያድናችኋል:: ከዚያ እናንተ በእሱ ባዕድ አምላክን ታጋራላችሁ።» በላቸው።
Ərəbcə təfsirlər:
قُلۡ هُوَ ٱلۡقَادِرُ عَلَىٰٓ أَن يَبۡعَثَ عَلَيۡكُمۡ عَذَابٗا مِّن فَوۡقِكُمۡ أَوۡ مِن تَحۡتِ أَرۡجُلِكُمۡ أَوۡ يَلۡبِسَكُمۡ شِيَعٗا وَيُذِيقَ بَعۡضَكُم بَأۡسَ بَعۡضٍۗ ٱنظُرۡ كَيۡفَ نُصَرِّفُ ٱلۡأٓيَٰتِ لَعَلَّهُمۡ يَفۡقَهُونَ
65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እርሱ (አላህ) ከበላያችሁ ወይም ከእግሮቻችሁ በታች ቅጣትን በእናንተ ላይ ሊልክ ወይም የተለያዩ ሕዝቦች ስትሆኑ ሊያደባልቃችሁና ከፊላችሁን የከፊሉን ጭካኔ ሊያቀምስ ቻይ ነው።» በላቸው። ይገነዘቡ ዘንድ አናቅጽን እንዴት እንደምናብራራ ተመልከት።
Ərəbcə təfsirlər:
وَكَذَّبَ بِهِۦ قَوۡمُكَ وَهُوَ ٱلۡحَقُّۚ قُل لَّسۡتُ عَلَيۡكُم بِوَكِيلٖ
66. እርሱ(ቁርኣን) ከአላህ የመጣ እውነት ሲሆን ህዝቦችህ ግን አስተባበሉት:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በናንተ ላይ ጠባቂ አይደለሁም።» በላቸው::
Ərəbcə təfsirlər:
لِّكُلِّ نَبَإٖ مُّسۡتَقَرّٞۚ وَسَوۡفَ تَعۡلَمُونَ
67. ለየወሬ ሁሉ የሚደርስበት መፈጸሚያ ጊዜ አለው:: ወደ ፊትም በትክክል ታውቁታላችሁ::
Ərəbcə təfsirlər:
وَإِذَا رَأَيۡتَ ٱلَّذِينَ يَخُوضُونَ فِيٓ ءَايَٰتِنَا فَأَعۡرِضۡ عَنۡهُمۡ حَتَّىٰ يَخُوضُواْ فِي حَدِيثٍ غَيۡرِهِۦۚ وَإِمَّا يُنسِيَنَّكَ ٱلشَّيۡطَٰنُ فَلَا تَقۡعُدۡ بَعۡدَ ٱلذِّكۡرَىٰ مَعَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ
68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ አናቅጻችንን ለማስተባበል ወደ ክርክር የሚገቡትን ሰዎች በምታይ ጊዜ በሌላ ወሬ እስከሚገቡ ድረስ ተዋቸው:: ሰይጣንም መከልከልህን ቢያስረሳህና አብረሀቸው ሆነህ እንኳን ካስታወስክ በኋላ ከበደለኞች ሕዝቦች ጋር አትቀመጥ::
Ərəbcə təfsirlər:
 
Mənaların tərcüməsi Surə: əl-Ənam
Surələrin mündəricatı Səhifənin rəqəmi
 
Qurani Kərimin mənaca tərcüməsi - Amhar dilinə tərcümə - Afrika Akademiyası. - Tərcumənin mündəricatı

Tərcüməsi Məhəmməd Zeyn Zöhrəddin. Afrika Akademiyası tərəfindən nəşr olunub.

Bağlamaq