Check out the new design

Übersetzung der Bedeutungen von dem heiligen Quran - Amharische Übersetzung - Akademie Afrika * - Übersetzungen


Übersetzung der Bedeutungen Surah / Kapitel: Al-Baqarah   Vers:
۞ لَّيۡسَ ٱلۡبِرَّ أَن تُوَلُّواْ وُجُوهَكُمۡ قِبَلَ ٱلۡمَشۡرِقِ وَٱلۡمَغۡرِبِ وَلَٰكِنَّ ٱلۡبِرَّ مَنۡ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ وَٱلۡكِتَٰبِ وَٱلنَّبِيِّـۧنَ وَءَاتَى ٱلۡمَالَ عَلَىٰ حُبِّهِۦ ذَوِي ٱلۡقُرۡبَىٰ وَٱلۡيَتَٰمَىٰ وَٱلۡمَسَٰكِينَ وَٱبۡنَ ٱلسَّبِيلِ وَٱلسَّآئِلِينَ وَفِي ٱلرِّقَابِ وَأَقَامَ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتَى ٱلزَّكَوٰةَ وَٱلۡمُوفُونَ بِعَهۡدِهِمۡ إِذَا عَٰهَدُواْۖ وَٱلصَّٰبِرِينَ فِي ٱلۡبَأۡسَآءِ وَٱلضَّرَّآءِ وَحِينَ ٱلۡبَأۡسِۗ أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ صَدَقُواْۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُتَّقُونَ
177. መልካምነት ፊቶቻችሁን ወደ ምስራቅና ምዕራብ አቅጣጫ ማዞራችሁ አይደለም። መልካምነት በአላህ፣ በመጨረሻው ቀን፣ በመላዕክት፣ በመጸሐፍት በነብያት ያመነ፤ ገንዘብንም ምንም ያህል የነዋይ (ገንዘብ) ፍቅር ቢኖረዉም ለዝምድና ባለቤቶች፣ ለየቲሞች፣ ለሚስኪኖች፣ ለመንገደኞች፣ ለለማኞች፣ ባሪያዎችን ነፃ ለማውጣት የሰጠ፤ ሶላትን ደንቡን ጠብቆ የሰገደና ዘካንም ያወጣ ነው:: እንዲሁም ቃልኪዳን በገቡ ጊዜም ቃልኪዳናቸውን የሚሞሉ በችግር፣ በበሽታና በፍልሚያ ጊዜ ታጋሾች ናቸው። እነዚህ እነዚያ እውነትን የያዙ መሆናቸውን በተግባር አረጋግጠዋል:: አላህን የሚፈሩም ናቸው።
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ كُتِبَ عَلَيۡكُمُ ٱلۡقِصَاصُ فِي ٱلۡقَتۡلَىۖ ٱلۡحُرُّ بِٱلۡحُرِّ وَٱلۡعَبۡدُ بِٱلۡعَبۡدِ وَٱلۡأُنثَىٰ بِٱلۡأُنثَىٰۚ فَمَنۡ عُفِيَ لَهُۥ مِنۡ أَخِيهِ شَيۡءٞ فَٱتِّبَاعُۢ بِٱلۡمَعۡرُوفِ وَأَدَآءٌ إِلَيۡهِ بِإِحۡسَٰنٖۗ ذَٰلِكَ تَخۡفِيفٞ مِّن رَّبِّكُمۡ وَرَحۡمَةٞۗ فَمَنِ ٱعۡتَدَىٰ بَعۡدَ ذَٰلِكَ فَلَهُۥ عَذَابٌ أَلِيمٞ
178. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ግድያን በተመለከተ አጸፋዊ እርምጃ በእናንተ ላይ ተደንግጓል:: (እርሱም) ነፃ ሰውን በነፃ መግደል፤ ባሪያን በባሪያ መግደል፤ ሴትን በሴት መግደል::(ነው) ከሟች ወንድሙ ደም ትንሽ ነገር እንኳን ምህረት የተደረገለት ሰው በመሃሪው የሟች ወገን ላይ ካሳውን በመልካም መከታተል ሲኖርበት ምህረት የተደረገለት ገዳይም የነፍስ ዋጋውን ለእርሱ በመልካም አኳኋን መክፈል አለበት:: ይህ ከጌታችሁ የሆነ ማቃለልና እዝነት ነው:: ከዚህም በኋላ ህግን የተላለፈ ሰው እርሱ አሳማሚ ቅጣት ይጸናበታል::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
وَلَكُمۡ فِي ٱلۡقِصَاصِ حَيَوٰةٞ يَٰٓأُوْلِي ٱلۡأَلۡبَٰبِ لَعَلَّكُمۡ تَتَّقُونَ
179. እናንተ ባለ አእምሮዎች ሆይ! በአጸፋዊ እርምጃ ህግ ሕይወትን ትጎናጸፋላችሁ:: ይህም ግድያን ከመፈጸም ልትጠነቀቁ ዘንድ ነው።
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
كُتِبَ عَلَيۡكُمۡ إِذَا حَضَرَ أَحَدَكُمُ ٱلۡمَوۡتُ إِن تَرَكَ خَيۡرًا ٱلۡوَصِيَّةُ لِلۡوَٰلِدَيۡنِ وَٱلۡأَقۡرَبِينَ بِٱلۡمَعۡرُوفِۖ حَقًّا عَلَى ٱلۡمُتَّقِينَ
180. በማንኛዉም ላይ ሞት በመጣበት ጊዜና ቀሪ ሀብት ያለው እንደሆነ ለወላጆችና ለቅርብ ዘመዶች በአግባቡ መናዘዝ በእናንተ ላይ ተደንግጓል:: ይህ አላህን በሚፈሩ ላይ መፈጸም ያለበት ግዴታ ነው::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
فَمَنۢ بَدَّلَهُۥ بَعۡدَ مَا سَمِعَهُۥ فَإِنَّمَآ إِثۡمُهُۥ عَلَى ٱلَّذِينَ يُبَدِّلُونَهُۥٓۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٞ
181. (ኑዛዜውን) ከሰማው በኋላ የለወጠው ኃጢአቱ በእነዚያ በሚለውጡት ላይ ብቻ ነው:: አላህም ሁሉን ሰሚ ሁሉን አዋቂ ነውና::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
 
Übersetzung der Bedeutungen Surah / Kapitel: Al-Baqarah
Suren/ Kapiteln Liste Nummer der Seite
 
Übersetzung der Bedeutungen von dem heiligen Quran - Amharische Übersetzung - Akademie Afrika - Übersetzungen

Übersetzt von Muhammad Zain Zaher Al-Din. Herausgegeben von der Afrika-Akademie.

Schließen