Check out the new design

Übersetzung der Bedeutungen von dem heiligen Quran - Amharische Übersetzung - Akademie Afrika * - Übersetzungen


Übersetzung der Bedeutungen Surah / Kapitel: Al-Baqarah   Vers:
أُحِلَّ لَكُمۡ لَيۡلَةَ ٱلصِّيَامِ ٱلرَّفَثُ إِلَىٰ نِسَآئِكُمۡۚ هُنَّ لِبَاسٞ لَّكُمۡ وَأَنتُمۡ لِبَاسٞ لَّهُنَّۗ عَلِمَ ٱللَّهُ أَنَّكُمۡ كُنتُمۡ تَخۡتَانُونَ أَنفُسَكُمۡ فَتَابَ عَلَيۡكُمۡ وَعَفَا عَنكُمۡۖ فَٱلۡـَٰٔنَ بَٰشِرُوهُنَّ وَٱبۡتَغُواْ مَا كَتَبَ ٱللَّهُ لَكُمۡۚ وَكُلُواْ وَٱشۡرَبُواْ حَتَّىٰ يَتَبَيَّنَ لَكُمُ ٱلۡخَيۡطُ ٱلۡأَبۡيَضُ مِنَ ٱلۡخَيۡطِ ٱلۡأَسۡوَدِ مِنَ ٱلۡفَجۡرِۖ ثُمَّ أَتِمُّواْ ٱلصِّيَامَ إِلَى ٱلَّيۡلِۚ وَلَا تُبَٰشِرُوهُنَّ وَأَنتُمۡ عَٰكِفُونَ فِي ٱلۡمَسَٰجِدِۗ تِلۡكَ حُدُودُ ٱللَّهِ فَلَا تَقۡرَبُوهَاۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ ءَايَٰتِهِۦ لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمۡ يَتَّقُونَ
187. (ሙስሊሞች ሆይ!) በፆም ሌሊት ከሚስቶቻችሁ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ተፈቀደላችሁ:: እነርሱ ለእናንተ ልብሶች ናቸው:: እናንተም ለእነርሱ ልብሶች ናችሁና:: አላህ በዚህ ረገድ ነፍሶቻችሁን በማታለል ላይ መሆናችሁን ያውቃል::በእናንተም ላይ ተመለሰላችሁ፡፡ ከእናንተም ይቅርታ አደረገ፡፡ አሁን ተገናኙዋቸው፡፡ አላህም ለናንተ የጻፈላችሁን ነገር (ልጅን) ፈልጉ፡፡ ነጩ የንጋት ገመድ ከጥቁሩ የሌሊት ገመድ ለእናንተ እስከሚገለጽላችሁ ድረስ ብሉ:: ጠጡም:: ከዚያም ፆምን እስከ ሌሊቱ ድረስ ሙሉ:: እናንተ በመስጊዶች ተቀማጮች ኢዕቲካፍ ላይ ስትሆኑ ግን ሚስቶቻችሁን አትገናኙዋቸው:: ይህች የአላህ ህግጋት ናትና ለመተላለፍ አትቅረቧት:: ልክ እንደዚሁ አላህ አናቅጽን ለሰዎች ያብራራል:: እነርሱ የተከለከሉትን ሊጠነቀቁ ይከጅላልና::
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
وَلَا تَأۡكُلُوٓاْ أَمۡوَٰلَكُم بَيۡنَكُم بِٱلۡبَٰطِلِ وَتُدۡلُواْ بِهَآ إِلَى ٱلۡحُكَّامِ لِتَأۡكُلُواْ فَرِيقٗا مِّنۡ أَمۡوَٰلِ ٱلنَّاسِ بِٱلۡإِثۡمِ وَأَنتُمۡ تَعۡلَمُونَ
188. ገንዘቦቻችሁንም በመካከላችሁ በከንቱ (ያለ አግባብ) አትብሉ፡፡ እናንተም የምታውቁ ስትኾኑ ከሰዎች ገንዘቦች ከፊልን በኃጢኣት ትበሉ ዘንድ ወደ ዳኞች አትጣሏት፡፡
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
۞ يَسۡـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلۡأَهِلَّةِۖ قُلۡ هِيَ مَوَٰقِيتُ لِلنَّاسِ وَٱلۡحَجِّۗ وَلَيۡسَ ٱلۡبِرُّ بِأَن تَأۡتُواْ ٱلۡبُيُوتَ مِن ظُهُورِهَا وَلَٰكِنَّ ٱلۡبِرَّ مَنِ ٱتَّقَىٰۗ وَأۡتُواْ ٱلۡبُيُوتَ مِنۡ أَبۡوَٰبِهَاۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ لَعَلَّكُمۡ تُفۡلِحُونَ
189. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ስለለጋ ጨረቃ መለዋወጥ ይጠይቁሃል። «ይህ ክስተት ሰዎች ጊዜን ለመለካት የሚጠቀሙበትና የሐጅንም ወቅት ለማወቅ የሚረዳ ምልክት ነው:: መልካም ስራ ቤቶችን ከጀርባዎቻቸው መግባታችሁ አይደለም:: ይልቁንም የመልካም ስራ ባለቤት አላህን የሚፈራው ነው:: ቤቶችንም በፊት በሮቻቸው በኩል ግቡ:: አላህንም ፍሩ ከጀሀነም ቅጣት ልትድኑ ዘንድ።» በላቸው።
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
وَقَٰتِلُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ ٱلَّذِينَ يُقَٰتِلُونَكُمۡ وَلَا تَعۡتَدُوٓاْۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ ٱلۡمُعۡتَدِينَ
190. (ትክክለኛ አማኞች ሆይ!) እነዚያን የሚጋደሏችሁን ከሓዲያን በአላህ መንገድ ተጋደሉ:: ነገር ግን ድንበር አትለፉ :: አላህ ድንበር አላፊዎችን አይወድምና፡፡
Arabische Interpretationen von dem heiligen Quran:
 
Übersetzung der Bedeutungen Surah / Kapitel: Al-Baqarah
Suren/ Kapiteln Liste Nummer der Seite
 
Übersetzung der Bedeutungen von dem heiligen Quran - Amharische Übersetzung - Akademie Afrika - Übersetzungen

Übersetzt von Muhammad Zain Zaher Al-Din. Herausgegeben von der Afrika-Akademie.

Schließen